28/03/2025
ኖማ
ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታ
____________
👉 ምንድን ነው?
ኖማ (Noma ) የአፍ እና የፊት አካላት ላይ ጉዳት የሚያስከትል በባክቴሪያ እና ሌሎች ማይክሮብዎች የሚከሰት ከባድ የጋንግሪን በሽታ ነው።
👉 ተፅእኖዎቹ
“ኖማ ከበሽታ በላይ ነው፤ የከፍተኛ ድህነት እና የምግብ አለመመጣጠን ምልክት ሲሆን የህም ለዚህ ተጋላጭ የሆኑ የህበረተሰብ ክፍልን የሚጎዳ ነው።” ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረኢየሱስ፥ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዳይሬክተር ጀኔራል።
👉 የሚያጠቃቸው የህብረተሰብ ክፍሎች
በተለምዶ ከ2-6 ዓመት ዕድሜ ያላቸው፥ የተመጣጠነ ምግብ የማያገኙ፥ የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ፥ እንዲሁም የአፍ ጤና ችግር ያለባቸው ህፃናትን ያጠቃል።
የሞት መጠን (Case-fatality rate) ከ90% በላይ የሚገመት ቢሆንም፥ በሽታው ከታወቀ በአፍጣኝ ህክምና ማድረግ የህንን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ እንደሚቻል ጥናቶች ያሳያሉ።
ከበሽታው የሚያገግሙ ህፃናት ብዙውን ጊዜ የፊት ላይ ቋሚ ጉዳት፥ የመተንፈስ ፥ የመብላት የመናገር እና የማየት ችግሮች ይኖራቸዋል፤ ይህም በማህበራዊ ሁኔታዎች መገፋት፥ መሰድብ እና የሰብዓዊ መብታቸው ጥሰት ያጋጥማቸዋል።
👉 ምልክቶች
• በመጀመሪያ የድድ እና የጉንጭ ላይ እብጠቶች ወይንም ቁስሎች ይከሰታሉ፣
• ቁስሎቹ መጥፎ ሽታ ወይም ጠረን ይኖራቸዋል፣
• ኢንፌክሽኑ ወደ ቆዳ ይዛመታል፣ እና በከንፈሮች እና ጉንጮዎች ውስጥ ያሉት ሕዋስ ይሞታሉ፣
👉 ህክምናዎቹ ምን ምን ናቸው?
• በሁሉም የኖማ ደረጃዎች ላይ አንቲባዮቲክስ , የቫይታሚን ኤ መድሃኒት እንዲሁም ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን ያለው አመጋገብ ያበረታታል፣
• የተሃድሶ ቀዶ ጥገና (Reconstructive surgery) ወይም የፊት ቅርጽ እና ተግባርን ለመመለስ ያለመ ነው፣
👉መከላከያ መንገዶቹ
• በቂ እና የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት፣
• ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት፣
• እንዲሁም ጤናማ የአፍ ጤና አጠባበቅ ልማዶችን እንዲተገብሩ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: https://t.me/M0H_EThiopia