Eftu Hospital

Eftu Hospital because we care...

አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መመዘኛ መሰረት መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁሉ የትምህርትና የስራ ልምዳችሁን ኦርጅናል እና የማይመለስ ፎቶ-ኮፒ በመያዝ ከላይ በተጠቀሱት...
11/04/2025

አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መመዘኛ መሰረት መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁሉ የትምህርትና የስራ ልምዳችሁን ኦርጅናል እና የማይመለስ ፎቶ-ኮፒ በመያዝ ከላይ በተጠቀሱት የመመዝገቢያ ቀናት በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁ.9 በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መመዘኛ መሰረት መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁሉ የትምህርትና የስራ ልምዳችሁን ኦርጅናል እና የማይመለስ ፎቶ-ኮፒ በመያዝ ከላይ በተጠቀሱት...
07/04/2025

አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መመዘኛ መሰረት መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁሉ የትምህርትና የስራ ልምዳችሁን ኦርጅናል እና የማይመለስ ፎቶ-ኮፒ በመያዝ ከላይ በተጠቀሱት የመመዝገቢያ ቀናት በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁ.9 በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

@ የረመዳን ፆምና የስኳር ህመም ህክምና • የጤና ባለሞያና የስኳር ህመም ታካሚ የስኳር ህመምን ባህሪን በአግባቡ በመረዳትና በመመካከር የረመዳ ፆምን በጡሩ ሁኔታ መፆምና እንድሁም  የስኳር ...
28/02/2025

@ የረመዳን ፆምና የስኳር ህመም ህክምና

• የጤና ባለሞያና የስኳር ህመም ታካሚ የስኳር ህመምን ባህሪን በአግባቡ በመረዳትና በመመካከር የረመዳ ፆምን በጡሩ ሁኔታ መፆምና እንድሁም የስኳር ህመም የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል።

@ መፆም የሚችሉ የስኳር ህመም ታካሚዎች

• ዓይነት 2 የስኳር ህመም ያላቸውና
1. በአመጋገብና በአኗኗር ዘይቤ ስኳር መጠናቸውን የተቆጣጠሩ
2. በሚዋጡ ፣ በአፍ በሚወሰዱ መድሃኒቶች የተቆጣጠሩ
3. በመሠረታዊነት ኢንሱሊን የሚጠቀሙና ቢያንስ ለ 2 ወር በጡሩ ሁኔታ የስኳር መጠናቸውን የተቆጣጠሩ

• ዓይነት 1 የስኳር ህመም ያላቸውና በጡሩ ሁኔታ የስኳር መጠናቸውን የተቆጣጠሩ፣ ከሀኪማቸው ጋር በመገናኘት አስፈላጊውን ማስተካከያ መውሰድ የሚችሉ።

@ የስኳር ህመም አመጋገብ በረመዳን ፆም

• ስሁር በአግባቡ መመገብ አለብዎት።
• በተቻለ መጠን ስሁርን አዘግይተው ይመገቡ።

• ከኢፍጣር አዛን በኋላ በፍጥነት ወዳውኑ ማፍጠር አለብዎት።
• ኢፍጣር ላይ የቴምር መጠን ይገድቡ ( 2 ወይም 3 ፍሬ ቴምር ብቻ ይጠቀሙ።

• ዝቅተኛ የስኳር መጠን ጠቋሚ ( low glyceamic index) ያላቸውን ምግቦች ይመገቡ :-
• ነጭ ጤፍ፣ ቀይ ጤፍ ፣ የገብስ ዳቦና እንጀራ
• ፍረሽ / ትኩስ ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶችና፣ ሰላጣዎች፣
• የአጃ ና የገብስ ሾርባ ፣
• ቅርፊት ያላቸው ጥራጥሬዎች:- ባቄላ፣ አተር፣ ምስር፣
• ከኢፍጣር እስከ ስሁር ድረስ ብዙ ውሃ ይጠጡ
• (ቢያንስ 8 ብርጭቆ ዉሃ) ይጠቀሙ።

@ አለመመግብ ወይም መቆጠብ ያለብዎት ምግቦች

1. ቅባት ወይም ጮማ የበዛብት ምግብ አይጠቀሙ።
2. ስኳር የተጨመረበ ምግብም ሆነ የታሸገ መጠጥ አይጠቀሙ
3. የተጠበሰ ምግብን ያስወግዱ ( ሳንቡሳ፣ ዶናት፣ ኩኪስ ) አይመገቡ።

@ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተመለከተ

• ፈጣን እርምጃ ወይም የእግር ጉዞ ማድረግ ይችላሉ።
• የተራዊህ ( የለይል ሰላት ) እንደ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይጠቀሙ።

• ከሰዓት በሗላ ወደ ማፍጠሪያ ሲቃረቡ
• ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይመከርም።
• አድካሚና ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ ስራ አይስሩ።

• እንቅስቃሴዎችን በመደበኛነት የሚያደርጉ ከሆነ ከእንቅስቃሴ በፊትና በሗላ የደም ውስጥ የስኳር መጠንዎን ይለኩ።
• የስኳር መጠንዎ ከ 70 በታች ከሆነ ፆምዎትን ይፍቱ፣ ያፍጥሩ።

@ የስኳር ህመም መድኃኒት አጠቃቀም

• በጾም ሰዓታት በዓፍ የሚዋጡ የስኳር መድኃኒቶች ጾምን ያበላሻሉ።
• በቀን አንድ ጊዜ የሚዎሰዱ የስኳር ህመም መድኃኒቶች ኢፍጣር ላይ ይውሰዱ።

• በቀን ሁለት ጊዜ የሚዎሰዱ የስኳር ህመም መድኃኒቶች ኢፍጣርና ስሁር ላይ ይውሰዱ።
• የተለያየ መጠን ያላቸው መድሃኒቶች ካሉዎት ትልቁ መድሃኒት ኢፍጣር ላይ ቢወሰድ ይመከራል።
• በረመዳን ወቅት ለዝቅተኛ የስኳር መጠን የማጋለጥ እድል ያላቸው መድሃኒቶች አይመከሩም።

• ኢንሱሊን እሚወስዱ ከሆነ ከረመዳን በፊት ጧት እሚዎስዱት የነበረውን ኢፍጣር ላይ እንድሁም ማታ እሚውስዱት የነበረውን ስሁር ላይ ማድረግና መጠኑን መቀነስም ሊያስፈልግ ይችላል።

@ የረመዳን ፆምና የስኳር ህመም ህክምና ግብ

• የስኳር መጠን ከኢፍጣርና ከስሁር በፊት ከ 90 - 130 ማድረግ ነው።

• የስኳር መጠን ከ 70 በታች ወይም ከ 300 በላይ ከሆነ ፆምዎትን መፍታትና ለቀጣይ ቀናት ከሐኪምዎት ጋር በመመካከር ለስኳር መጠንዎ በጣም ከፍ ማለትና ዝቅ ማለት መንስኤውን መለየትና መፍትሄ ማስቀመጥ።

@ ማሳሰቢያ :- የስኳር ህመም ካለብዎት የረመዳን ፆም መፆም ሲያስቡ ቅድሚያ ከሐኪምዌት ጋር ይምከሩ። እንድሁ የአመጋገብ ሁኔታ፣ የመድሃኒትዎን አወሳሰድ ማስተካከልና የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችን ከሐኪምዎት በቂ ግንዛቤ ይውሰዱ።

References
- IDF-DAR Guideline 2021
- American Diabetes Association 2025
- Australian Diabetes Society 2020

ዶ/ር ሙሃመድ የሱፍ ( የውስጥ ዴዌ ስፔሻሊስት)

አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር ግምት የሚያወጣ ነፃ የ " MRI " ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጋራ የውል ስምምነት ተደረገ።ኢፍቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከድሬዳዋ አስተ...
31/12/2024

አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር ግምት የሚያወጣ ነፃ የ " MRI " ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጋራ የውል ስምምነት ተደረገ።
ኢፍቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር ግምቱ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር የሚያወጣና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የ " MRI " ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጋራ የውል ስምምነት ተፈራርሟል።
የተደረገው ድጋፍ በ"MRI" የመመርመሪያ መሳሪያ እጥረት ምክኒያት በአስተዳደራችን አገልግሎቱን ለማግኘት አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ መኖሩን የተናገሩት የጋራ የውል ስምምነቱን ከኢፍቱ ሆስፒታል ባለቤቶች ጋር የተፈራረሙት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፅጌረዳ ክፍሌ ኢፍቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ይህንኑ ችግር ለመፍታት ያደረገው ድጋፍና የተፈራረምነው የጋራ የውል ስምምነት እጅግ የሚያስመሰግነው ሲሆን ሌሎችም የግል ጤና ተቋማት እንዲህ ያለውን አርዓያ በመከተል በጎ ሥራዎችን በመሥራት ህብረተሰባቸውን ተጠቃሚ ይገባቸዋል ብለዋል።
የኢፍቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለቤቶች ወ/ሮ ፎዚያ ሰኢድና ባለቤታቸው ዶ/ር ሱሌማን ኢሳ በበኩላቸው ሆስፒታላቸው በዝቅተኛኘ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተቻለው አቅም በሞያው ዘርፍ ለመደገፍ ከጤና ቢሮ ጋር የጋራ የስምምነት ውል በመፈራረማቸው ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረው በሆስፒታላቸው የሚሰጠው ይሄው ነፃ የ " MRI " ምርመራ አገልግሎት በአግባቡና በተገባው የጋራ የውል ስምምነት መሰረት መፈፀሙን በቅርበት እንከታተላለን ብለዋል።
ይሄው የጋራ የውል ስምምነት ለአምስት ዓመት የሚቆይ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ በየአምስት ዓመቱ የሚታደስ ይሆናል።

አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መመዘኛ መሰረት መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁሉ የትምህርትና የስራ ልምዳችሁን ኦርጅናል እና የማይመለስ ፎቶ-ኮፒ በመያዝ ከላይ በተጠቀሱት...
24/12/2024

አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መመዘኛ መሰረት መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁሉ የትምህርትና የስራ ልምዳችሁን ኦርጅናል እና የማይመለስ ፎቶ-ኮፒ በመያዝ ከላይ በተጠቀሱት የመመዝገቢያ ቀናት በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁ.10 በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ሆስፒታላችን በዶ/ር አቤል መልካሙ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹና ለስራ ባልደረቦቹ መጽናናትን ይመኛል።
10/12/2024

02/11/2024

አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መመዘኛ መሰረት መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁሉ የትምህርትና የስራ ልምዳችሁን ኦርጅናል እና የማይመለስ ፎቶ-ኮፒ በመያዝ ከላይ በተጠቀሱት የመመዝገቢያ ቀናት በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁ.10 በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

Address

Sabiyan, Circle
Dire Dawa
3000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eftu Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Eftu Hospital:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category