Gambella Town Primary Hospital

Gambella Town Primary  Hospital To provide Hope, Care and Cure. To provide compassionate, accessible, high quality, cost effective healthcare to one all.

To serve with a patient's first motto and to work towards a patient- centered care.

28/03/2026
With Gatbel Chamjock – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
19/02/2026

With Gatbel Chamjock – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

03/02/2026

ማስታወቂያ
ለጤና ባለሙያዎች በሙሉ:

ጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና ነክ ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደህንነትን እና ጥራት ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ የቁጥጥር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በዚህም መሰረት የጤናና ጤና ነክ ተቋማት እና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ የቁጥጥር ዘርፉን አቅምና ውጤታማነት ለማሻሻል ከሚሰሩ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች ውስጥ አንደኛው የጤና ቁጥጥር ስርዓትን በማጠናከር ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ የጤና አገልግሎት ለማህበረሠቡ መሠጠቱን ማረጋጥ አንደኛው ነው። ይህንንም እውን ለማድረግ ፍለጎቱ እና በዘርፉ ላይ ዝንባሌ ያላቸውን የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች እንዲሣተፉ እድሉን በማመቻቸት እንድም በዘርፉ ውስጥ የሚታየውን የሙያ ሥብጥር ክፍተት ለመሙላት በሁለተኛም እነዚህ ባለሙያዎች በቋሚነት በሚሠሩበት ተቋም ውስጥ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ባህል እንዲዳብር፣ የሁሌም ተግባራቸው እንዲሆንና አምባሣደር ለማድረግ በማሰብ ይህንን ማስታወቂያ አውጥተናል።

ስለሆነም በቁጥጥር ስራ ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለመሣፍ ፍላጎቱ ያላችሁ እና በአሁኑ ሠዓት በጤናው ዘርፍ ተሠማርታችሁ እየሠራችሁ የምትገኙ የጤና ባለሙያዎች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት ከዚህ በታች የተቀመጠዉን ማስፈንጠሪያ(link) በመጫን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንጠይቃለን።

https://forms.gle/fV4vKAJLtQ24M6x28

መስፈርት
▫️ በጤና ተቋማትና ባለሙያዎች የቁጥጥርና ሌሎች ስራዎችን በተመለከተ ዘርፉን ለማገዝ ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች
▫️ እውቅና ካለው የከፍተኛ የትምህርት ተቋም የተመረቀ እና የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያለው/ያላት
▫️ ከሚሰሩበት ተቋም በተመደቡበት ሙያ የስራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
▫️ ከሚሰሩበት ተቋም የእውቅና/የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
▫️ የመስመር ላይ (Online) ስልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች

ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት

1. ስፔሻሊስት ሃኪም
2. ጠቅላላ ሃኪም
3. ጤና መኮንን
4. ላቦራቶሪ
5. ፋርማሲ
6. አንስቴቲስት
7. ነርስ
8. ባዮሜዲካል ኢንጂነር
9. ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስት
10. ሚድዋይፈሪ
11. የኣካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ
12. ሌሎች የጤና የሙያ ዘርፎች

ማሳሰቢያ፡-
▫️ አመልካች የትምህርት ማስረጃ/ዲግሪ፣ የስራ ልምድ፤የሙያ ፈቃድ እና ከቁጥጥር ስራው ጋር ተያያዥነት ያለው የስልጠና ሰርተፊኬት ካለ በPDF ማያያዝ ይኖርበታል
▫️ በጤና ተቋማትና ባለሙያዎች የቁጥጥር፤ የክሊኒካል ኦዲት ስራ እና ጥራት/quality Improvement ላይ ተሳትፎ የነበረው ይበረታታል
▫️ ለበለጠ መረጃዎች semreselam.tsega@moh.gov.et, hiwot.abebe@moh.gov.et

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

11/12/2025

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
____________

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy, Optometry እና Human Nutrition ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም አዲስም ሆነ ነባር፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እና የኦንላይን ምዝገባው ከታህሳስ 02/2018 እስከ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ብቻ የሚቆይና ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦

ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሄድ የኢትዮጵያ ዲጅታል መታወቂያ- ፋይዳ (Ethiopian Digital ID Card) ግዴታ መሆኑን አውቃችሁ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው መጉላላት የጤና ሚኒስቴር ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑ እናሳውቃለን።

ለተጨማሪ መረጃ የጤና ሚኒስቴር ቴልግራም ቻናል ይመልከቱ t.me/M0H_EThiopia

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

09/12/2025
04/12/2025

‎በአዲስ አበባ ያለው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት ምጣኔ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው ተባለ

‎በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር 600 ሺሕ አልፏል

‎የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባካሄደው ጥናት፣ በአዲስ አበባ ያለው የስርጭት መጠን 3 ነጥብ 14 በመቶ ሆኖ ሲገኝ፤ የሀገር አቀፉ ምጣኔ ደግሞ 0 ነጥብ 83 በመቶ እንደሆነ አስቀምጧል።

‎የቫይረሱ ስርጭት ከ0 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሕጻናት 16 በመቶ፣ ከ15 እስከ 24 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች 34 በመቶ እንዲሁም፤ 25 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆኑ አዋቂዎች ደግሞ 51 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር ይሸፍናሉ።

‎እ.ኤ.አ በ2024/2025 በጀት ዓመት አዲስ በኤች አይ ቪ ተይዘዋል ተብለው የተገመቱ ዜጎች ቁጥር 7 ሺሕ 962 ሲሆን፤ በየዓመቱ በአማካይ 9 ሺሕ 560 ሰዎች በኤች አይ ቪ/ኤድስ ምክንያት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል።

‎በሀገር አቀፍ ደረጃ ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር እንደሚኖሩ ከሚገመተው ሰዎች መካከል 94 በመቶ የሚሆኑት ተመርምረው ራሳቸውን አውቀው መድኃኒት እንደጀመሩ በጥናቱ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
‎(ፊደል ፖስት)

04/12/2025

Marberg virus transmission methods and prevention methods:-

📌 What is the disease of Marberg virus?

o Marberg virus disease is an epidemic of bleeding and fever.
o Happens to humans and other animals.

📌 What are the symptoms of Marberg virus disease?

👉 Blood flow from mouth, nose or skin
👉 High fever, cold and headache;
👉 Muscle and back pain.
👉 Diarrhea, stomach pain and diarrhea.
👉 A bandit that is very visible on the chest, back and abdomen.
👉 The symptoms of the disease will appear within two to nine days of being exposed to the virus.

📌 What are the ways to pass Marberg virus disease?

• Direct contact with blood, urine, tears and other fluids of a person infected with the virus;
• Material contaminated with sick or expired body fluids, such as clothes, bed sheets, needle and other tools;
• If the night birds are infected with the disease, it will be transferred to humans.

📌 What are the ways to prevent Marberg virus disease?

o Going to a medical facility when you have the above symptoms;
o If you have a fever with a sick person, go to medical facilities immediately;
o Professional preparation and burial of the co**se at the time of death; avoiding unnecessary burial ceremonies and removing touch materials.

o Protect yourself from the touch of blood and fluid from a sick person.
o Use preventive measures i.e. masks and hand gloves when treating a sick person.
o Wash your hands properly with sanitizer or soap and water.

MVD
03/12/2025

MVD

Address

Gambella Town Primary Hospital
Gambela
5540

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gambella Town Primary Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category