GO'H Clinic

GO'H Clinic We provide all clinic services in all department including outpatient and inpatient treatment, lab investigations and minor procedures by qualified physicians.

We also provide a 24 Hr pharmacy service

እንኳን ደስስስስ አልዎት🙏🌹🙏🌹🙏ክሊኒካችን ሰሞኑን በተከታታይ 5 ቀናት ከረቡዕ ጀምሮ ከጎንደር አካዳሚ የመዋዕለና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር  በመስማማት ለ 600 ሕፃናት የጤና Surviell...
24/09/2022

እንኳን ደስስስስ አልዎት🙏🌹🙏🌹🙏
ክሊኒካችን ሰሞኑን በተከታታይ 5 ቀናት ከረቡዕ ጀምሮ ከጎንደር አካዳሚ የመዋዕለና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር በመስማማት ለ 600 ሕፃናት የጤና Surviellanceና Screening program በሦስት የሕፃናት ስፔሻሊስት ሐኪሞችና የላብራቶሪና የነርስ ባለሙያዎች ታግዞ አካሄደ!! በመርሃ ግብሩም
1. የነፃ የሰገራ ምርመራና Deworming(for those who had positive findings only)
2. የሕፃናት Wholistic school readiness check up( using 5 core components)
3. ለሕፃናቱ የአጠቃላይ well child care(Health promotion, Disease prevention, Anticipatory Guidance እና Disease Detection) የጤና ምክርና አገልግሎት ለሕፃናቱ ወላጆች ተሰጥቶል። ይህ የsurviellance program በአመት ሁለት ጊዜ(በየ 6 ወሩ) የሚቀጥል ይሆናል።
4. ከዚህ የSurviellance ፕሮግራም ጎን ለጎን ለጎንደር አካዳሚ መምህራንና ስታፍ ሰራተኞችም በ ሕጻናት ባህሪና የትምህርት አቀባበል ዘዴ እንዲሁም ስለ ሕፃናት ጤና አጠባበቅ ዙሪያ በክኒኒኩ በኩል ተሰጥቷል። በቀጣይም ይህን ስልጠና ለተማሪ ወላጆች ለመስጠት ክሊኒኩም ሆነ ት/ቤቱ በዝግጅት ላይ እንገኛለን። በመጨረሻም በዚህም መርሃ ግብር ለተሳተፋችሁ የክሊካችን staff ሰራተኞች ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

"ይምጡና ይጎብኙን ሙያዊ ፍቅርና ትህትናን ከሰውነት ጋር በተላበሱ ሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ታክመውና ስለ የሚያሳስቦት የጤና ሁኔታ መፍትሔ አግንተው ይሄዳሉ"

# # #አድራሻችን ቀበሌ 20 አዘዞ ሲሳይ ጋራዥ ነው።
# # #በ0987876465 ያገኙናል❤️

16/09/2022
አገልግሎት መጀመራችን ስንገልጽ በደስታ ነወ። #ጎህ ክሊኒክ የጤናዎ አጋር ነወ!
21/08/2022

አገልግሎት መጀመራችን ስንገልጽ በደስታ ነወ።
#ጎህ ክሊኒክ የጤናዎ አጋር ነወ!

07/08/2022

የህፃናት ምግብ ፍላጎት መቀነስ ምክንያቶች ምንድናቸው️?
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
በዶ/ር ታመነ ሀብቱ
የሕፃናት ሕክምናና
ጤና አጠባበቅ ስፔሻሊስት
ነሐሴ 01/12/2014 ዓ.ም
ጎንደር-ኢትዮጵያ
አድራሻችን አዘዞ ቀበሌ 20 በተለምዶ ሲሳይ ጋራዥ እየተባለ ከሚታወቀው ሰፈር እንነገኛለን።።በወጣት ስፔሻሊስት ሐኪሞችና በSeniour የጤና ባለሙያዎች ስብስብ የተከፈተው ክሊኒካችን እናንተን ለማገልገል ዝግጁ ነው። አገልግሎታችን በሁለንተናዊ መልኩ ሥለሆነ በማንኛውም ስላሳሰበዎ የጤና ሁኔታ መጥተው እንዲጎበኙን የቀደመ ምክራችን ነው። መልካም ንባብ #
✍️✍️✍️
👦👧 የሕፃናት የምግብ ፍላጎት መቀነስና ምክንያቶቻቸው👩‍⚕🧑‍⚕
✈️🏩✈️
በዛሬው ዕለት ስለ ሕፃናት የምግብ ፍላጎት መቀነስና እንዲሁም ዋና ዋና ምክንያቶቻቸውን በተመለከተ በተወሰነ መልኩ እንዳስሳለን።
ይህ እንግዲህ እንደየ ሕፃናቱ የእድገት መጠናቸው እና እንደየእድሜያቸው እና እንደተፈጥሯቸው ይለያያል::
ይህም የሕፃናቱ ችግር የብዙ ቤተሰቦች ጥያቄ ነው። ልጄ የምግብ ፍላጎቱ ቀነሰብኝ? ምን ላድርግ?! ወዘተ የብዙ ወላጆች ጥያቄ ነው።
🔹በተለይ በመጀመሪያ ወራት እስከ አንድ ዓመትና የተወሰኑ ወራት ዉስጥ በደንብ ሲመገብ የነበረ ልጅ ከ 1 አመት ወይም ከ 2 አመት ከሞላው በዋላ የምግብ ፍላጎቱ በእጅጉ ሊቀንስ ይችላል ::
🔹 ይህ እንግዲህ በብዙ መልኩ ሊከሰት ቢችልም ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተፈጥሯዊ እና ብዙ ልጆች ላይ የሚታይ ነው::
እንደሚታወቀው ሕፃናት በመጀመሪያ 1 ዓመት ፈጣን የሚባለውን እድገት ያሳያሉ። (እስከ 7 ኪሎ በ አንድ አመት ይጨምራሉ ) ስለዚህ በመጀመሪያው ዓመታቸው የምግብ ፍላጎታቸው ጥሩ የሚባል ነው።
👉 ሁለተኛው አመት ላይ ግን በተፈጥሮ የሚጨምሩት 2 ኪሎ ብቻ ነው ስለዚህ ምግብ ፍላጎታቸው መቀነሱ ተፈጥሯዊ እና የሚጠበቅ ነው:: ነገር ግን ይህ ተፈጥሮአዊ ጉዳይ ከልጆቹ የተለየ ባህሪና አእምሮአዊ ጠባይ ጋ ሲያያዝ Avoidant/Restricted food intake behaviour በመባል ይታወቃል። ልክ እንዲህ ዓይነት አፋጣኝ ሕክምና የሚያሻቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሁኖ ነገር ግን በቅድሚያ ወላጆችም ይህን ተፈጥሮአዊ ሂደት በሁሉም ሕፃናት መኖሩን ቢያውቁና ቢረዱ እንወዳለን።
👉 ስለዚህ ወላጆች በተፈጥሮ ሂደት የሚመጣን የልጆችን የምግብ ፍላጎት መቀነሰ የተፈጥሮ ሂደት መሆኑን ተረድተው ማድረግ ያለባቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው!!
📌በተቻለ መጠን ጤናማ ምግብ ማቅረብ🍅🍌🍇🍓
📌 የተለያዩ የምግብ አይነቶችን ማቅረብ( Choose my plate.com)
📌 የልጆዎን የምግብ ምርጫ ያክብሩ(ይህ ሲባል ግን ልጆች ጣፋጭ ነገርን አብዝተው ስለሚወዱ ጥንቃቄ ያሸዋል)
📌 አዳዲስ ምግቦች ቀስ በቀስ ያለማምዱ (ከእንስሳትም፣ ከእፅዋትም ከፍራፍሬም ወዘተ)
📌 ልጅዎትን ለመመገብ ብለው የቁጣም ሆነ ኃይል አይጠቀሙ ፤ይልቁን ልጅዎን ከቤቸሰብና ከልጆች ጋ እያሻሙ እያባበሉ በፍቅር ይመግቡ
📌 የጤና ምርመራ እና የእድገት ክትትል ያድርጉ እና ጤንነቱን ያረጋግጡ:: ሌሎች ተጓዳኝ ሕክምና የሚያሻቸው ጉዳዮች እንዳይኖሩ ይረዳልናና ይህን ተፈጥሮአዊ ሂደት አበብሰውት እንዳይሆን ወደ ሕክምና በመሄድ ምርመራ ማድረግም ተመራጭ ነው። ተጓዳኝ በሽታም ካለ በምርመራ ይታወቃልና በአፋጣኝ እንዲታከም ያግዛል።
✍️✍️
🛑 ከተፈጥሯዊ ምክንያት በተጨማሪ የህፃናትን የምግብ ፍላጎት የሚቀንሱ ነገሮች ምን ምንድናቸው❓️
🩸 1. የደም ማነስ(Anemia):
❤️ ህፃናት በብዙ ምክንያቶች የደም ማነስ ሊገጥማቸው ይችላል ።
--የህፃናት የደም ማነስ በእኛ ሀገር ብዙ ጊዜ ምክንያቱ የላም ወተትን ያለጊዜው በመጀመር ወይም ደሞ የላም ወተትን አብዝቶ ከመስጠት(በቀን 600 ሲሲ በላይ) የሚመጣ የጤና ችግር ነው:: የላም ወተት እድሜአቸው ከ 12ወር በታች ለሆኑ ሕፃናት አይመከርም። ይሄም የአንጀት ቁስለትና አለርጂ እንዲሁም የብረት እጥረት(Iron deficiency anemia) ይባላል።
2. የሌሎች ንጥረ ነገሮች እጥረት (micronutrients and mineral deficiency)
🔷 የቫይታሚን የዚንክ የሰሌንየም እጥረት - ብዙ ጊዜ የተመጣተነ ምግብ ያላገኙ ህፃናት ላይ ጎልቶ ይታያል ::
3. ልዩ ልዩ ህመም 🤒🤕
📌ህፃናት ማንኛዉም አይነት ህመም ወይም ኢንፌክሽን ከያዛቸው የምግብ ፍላጎታቸው በእጅጉ ይቀንሳል ለምሳሌ የሆድ ትላትልና የአንጄት ኢንፌክሽን፣ ጉንፋን የቶንሲል ህመም፣ የጆሮ ህመም ፣ የ ሽንት የቧንቧ ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉት የሕፃናቱን የምግብ ፍላጎት ይቀንሳሉ።
4. ጣፋጭ ምግብ በብዛት መመገብ🥯
👦👧 ሕፃናት በተደጋጋሚ እንደ ኬክ ብስኩት ጁስና ጭማቂ የመሳሰሉ ጣፋጭ ምግቦችን የሚወስዱ ከሆነ ሌላ ምግብ የመመገበ ፍላጎታቸው በእጅጉ ሊቀንስ ይቺላል አልፎ ተርፎም ለአላስፈላጊ ዉፍረት(obesity) ሊዳርጋቸው ይቻላል። እዚህ ላይ የወላጆች ክትትል ወሳኝነት አለው።
5. ሌላውና ወሳኙ ነገር የእናት ጡት ወተት ነው(...አዘግይቶ ማጥባት/Delayed weaning)
የእናት ጡት ወተት በመጀመሪያዎቹ ወራትና ዓመት ውስጥ ወሳኝ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ከ 6-12 ወር በኋላ የልጁን አመጋገብ ቀስ በቀስ ወደ የዘወትር ምግቦች ማዛወር ያስፈልጋል። ከዚህም ጋ ተያይዞ ሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦችን ቅድሚያ እየሰጠን የእናት ጡት ወተት እንደተጨማሪ(Suplements) ተደርጎ መወሰድ አለበት።
አንዳንዴ ዕድሜአቸው ከአንድ ዓመትና በላይ ለሆናቸው ሕፃናት ፈሳሽ ነገሮችን የእናት ወተትን ጨምሮ አብዝቶ መጠቀም ልጆች ጨጓራቸው ትንሽ ስለሆነ በፈሳሽ ነገሮች ቀድሞውኑ ከተሞላ ሌላ ምግብ አልበላም ይላሉና ፈሳሽ ነገሮችን ከተቻለ ከምግብ በኋላ እንድ ተጨማሪ(suplements) እንዲወስዱ ማድረጉ ወሳኝነት አለው።

👉 ሕፃናቱ ጁስ በጣም ስለሚወዱ መከልከሉ ሊያዳግት ይችላል ነገር ግን መጥኖ መስጠቱ ተገቢ ነው ለምሳሌ እድሜያቸው ከ 2-6 ዓመት ያሉ ህፃናት በቀን ከ 120- 180 ሲሲ (ከሁለት - ሶስት የቡና ሲኒ) ጁስ በላይ መውሰድ የለባቸውም::
6. የቤት ዉስጥ ተፅዕኖ እና ጭንቀት :
🔘 ቤት ውስጥ በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ተደጋጋሚ ጭቅጭቅ ደብድብ ሲደርስባቸው ወይም ሐዘን ካለ ህፃናት የምግብ ፍላጎታቸው ይወርዳል። ይህ እድሜአቸው ትንሽ ከፍ ባሉና በተወሰነ መልኩ ማገናዘብ በሚችሉ ሕፃናት የሚስተዋል ችግር ነው።
7. እንቅስቃሴ አለማድረግ ።
🔘 ህፃናት የአይምሮ እና የአካል እድገታቸው የተፋጠነና ሰውነታቸው ጠንካራ እንዲሆን እንዲሁም የተመገቡት ምግብ በአግባቡ እንዲፈጭና ከፍተኛ የሆነ የምግብ ፍላጎት እንዲኖራቸው በቀን ቢያንስ 30- 60 ደቂቃ ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርባቸዋል:: ወላጆች በዚህ እናንተም አብራችሁ እየሰራችሁ ብታበረታቷቸው ተመራጭ ነው።
🔘 ከአካላዊ እንቅስቃሴ ይልቅ በአንፃሩ ይህን የማያደርጉ እና በተለይ ጌም እና ቴሌቪዥን ላይ የሚውሉ ሕፃናት የምግብ ፍላጎታቸው ዝቅ ሊል ይቻላል።
8. ሌላው የጨጓራ ቁስለት እና ህመም ካለባቸው ነው። ይህም በተወሰነ መልኩ ከፍ ያሉ ሕፃናትን ያጠቃል። በሰገራ ምርመራ ይገኛል።የሚታከም ነው።
9. ሌላውና የመጨረሻው ሕፃናቱ በአብዛኛው ጊዜ ጨዋታና ማኅበራዊ ሕይዎት ጀማሪዎች ስለሆነና ስለሚያስደስታቸው የምግብ ሰአታቸውን ይዘላሉ። ከመብላት መጫዎትን ይወዳሉ። ሁኖም ይህ ማኅበራዊ ሕይዎቱ ለልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝና የሚመከር ቢሆንም ነገር ግን በዚህ ሰአት ቤተሰብ ለልጆቹ ልዩ ትኩረትን ሊያደርግ ይገባል። ሰአቱን ቆጥሮ ቁርስን ጨምሮ በቀን ከ 5-6 ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ይኖርባቸዋል። አንዳንዴ የልጆችን የምግብ ፍላጎት ለመቀስቀስ ልጁን ከቤተሰብና ከሌሎች ሕፃናት ጋ እያስቀኑና እያጎረሱ መመገብ ተመራጭነት አለው። ለጊዜው እዚህ ላይ ይብቃን በሌላ ጊዜ በስፋት እንመለስበታለን።

👉 ጽሑፉን በጽሞና ስላነበቡልንና በክሊኒካችን ጤናማ ትውልድ ግንባታ ላይ ስተለተሳተፉ "በጎሕ ክሊኒካችን" ሥም እናመሠግናለን #
ለወዳጅ ዘመድዎ መልዕክቱን share ማድረጉዎን አይዘንጉ። ማንኛውም ጥያቄ ካለወት በዚህ 0992704882/0987876465 ደውለው ያግኙን።
❤️🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️

የ24 ሰዓት አገልግሎት እንሰጣለን! # አዘዞ አባ ሳሙኤል ሲሳይ ጋራዥ ፊትለፊት።
04/08/2022

የ24 ሰዓት አገልግሎት እንሰጣለን!
# አዘዞ አባ ሳሙኤል ሲሳይ ጋራዥ ፊትለፊት።

From next week......
31/07/2022

From next week......

31/07/2022

It will be opened starting from next week. Come and get our service!

24/07/2022
24/07/2022
 #ይህ የጎህ ክሊኒክ የፌስቡክ ገጽ ነው።  #በዚህ ገጽ ጤና እና ጤና ነክ የሆኑ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፣ ትንታኔ በባለሙያወች ይሰጥበታል ሐሳቦች ይንሸራሸራሉ።  #ወደ ገጹ ወዳጅዎን በመጋበዝ ለጤ...
24/07/2022

#ይህ የጎህ ክሊኒክ የፌስቡክ ገጽ ነው።
#በዚህ ገጽ ጤና እና ጤና ነክ የሆኑ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፣ ትንታኔ በባለሙያወች ይሰጥበታል ሐሳቦች ይንሸራሸራሉ።
#ወደ ገጹ ወዳጅዎን በመጋበዝ ለጤናቸው ጠቃሚ መረጃወችን እንዲያገኙ ይተባበሩ።

# # #አላማችን ህብረተሰቡን ማገልገል ነው።

24/07/2022

Address

Gondar, Aba Samuael, Infront Of Sisay Garaj
Gondar
156

Telephone

+251987876465

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GO'H Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category