Gashaw Clinic ጋሻው ክሊኒክ

Gashaw Clinic  ጋሻው ክሊኒክ Quality service for all !!!

02/04/2023

የለውጥ ሂደቶች

▪️ሰዎች በህይወት ዘመናቸው በተለያዩ የለውጥ ሂደቶች ያልፋሉ:: ለውጥ በአንድ ጀምበር አይመጣም:: ሂደት ነው:: ብዙ መውደደቅና መነሳቶች: ብዙ ተስፋ ሰጪና ተስፋ አስቆራጭ ጊዜያቶች ታልፈው ነው ስኬት ላይ የሚደረሰው:: ምናልባት አንዳንዶቹ እድል: ብርታት ወይንም ብልጠት በታከለበት ሁኔታ ነገሮች ቶሎ ተፈጽመውላቸው ይሆናል::

▪️እንደ Prochaska እና DiClemente እይታ ከሆነ: መለወጥ በሽክርክሪት ይመሰላል::

▪️ ለዛሬ ለዚህ ጽንሰ ሃሳብ አስረጅ እንዲሆነን: ሱስ የማቆም ሂደትን እንመለከታለን

▶️ Pre-contemplation/ቅድመ ውጥን:-

▫️ በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ስለችግሮቻቸው ያላቸው ግንዛቤ እምብዛም ነው::

▫️ብዙ ሱስ አስያዥ እጾችን የሚጠቀሙ ግለሰቦች: ሱሱ በሚታይ ሁኔታ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሰባቸው ቢሆን እንኳን: ችግሩን አምኖ ከመቀበል ይልቅ: ምንም ችግር እንዳልተከሰተባቸው በመካድ (denial) እና ሱሰኛ እንዳልሆኑና ማቆም ከፈለጉ በየትኛውም ጊዜ ማቆም እንደሚችሉ ሲናገሩ ይስተዋላል:: በዚህ ወቅት የባለሙያው ሚና እነዚህን ጉዳቶች እንዲያስተውሏቸው (impact assessment): እጽ ተጠቃሚ መሆናቸው የጠቀማቸውንና የጎዳቸውን ነገር (pros and cons) እንዲዘረዝሩ በማድረግ ነገሮችን እንዲያሰላስሉ መፍቀድ ይሆናል::

▶️ Contemplation/ውጥን-

▫️በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ስለ ችግሩ እውቅና ይኖራቸዋል:: ንግግሮቻቸው በመለወጥና ባለመለወጥ ሃሳቦች መሃል ይዋልላሉ::

▫️ 'እጹን መጠቀሜ ከባለቤቴ ጋር እንዳጋጨኝ አውቃለሁ: ግን ደሞ ጓደኞቼን ሳገኝ መጠቀሜ አይቀርም: የክፋ ቀን ወዳጆቼን ማጣት ደሞ አልፈልግም' አይነት ንግግሮች ይስተዋላሉ::

▫️ብዙዎቹ የዕጽ ተጠቃሚዎች እዚህኛው ደረጃ ሲደርሱ ወደ ባለሙያ እርዳታን ለማግኘት የማቅናት እድላቸው ይጨምራል::

▫️በዚህ ወቅት የባለሙያው ሚና ወደ መለወጥ ሃሳቦች እንዲዘነብሉ ማበረታታት ይሆናል::

▫️ የችግሩን ግዝፈት እንዲረዱ እና ለውጥ ለማምጣት ብቁ እንደሆኑ እንዲገነዘቡ በማድረግ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሻገር ይቻላል::

▶️ Preparation/ የዝግጅት ምዕራፍ

▫️በዚህ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የመለወጥ ውጥናቸው ሚዛን መድፋት ይጀምራል::

▶️ Action/ ተግባራዊ የመለወጥ ስራዎች

▫️የለውጥ ስራዎቻቸው መታየት ይጀምራሉ:: የሚጠቀሙትን ሱስ መጠን ሲቀንሱ: ከፍ ሲልም ሲያቆሙት ይስተዋላል::

▫️በዚህ ሂደት ውስጥ ያሉ ሰዎች: የለውጥ ሂደቱን የሚያሳልጡ መሰረታዊ ክህሎቶችን እንዲማሩ ይደረጋል::

▶️ Maintenance/ ለውጥን ማስቀጠል

▫️በዚህ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች: የቀድሞ ባህርያቸው እንዳያገረሽ ስራን ይፈልጋል::

▶️ Relapse/ ወደ ቀደመ ባህርይ መመለስ

▫️ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ወደቀደመ ባህርያቸው ሊመለሱ ይችላሉ:: እነዚህ ምክንያቶችን መለየትና መስራት መቋቋምያ መንገዶችን መፈለግ ያሻል::

▪️የሱስ ማቆም ህክምናዎች እነዚህ የለውጥ ሂደቶቾን መሰረት አድርገው ይካሄዳሉ::
▪️በግል ወይንም በቡድን ሊሰጡ ይችላሉ::
▪️የሱስ ማቆም ህክምናን ለማግኘት የተለያዩ የህክምና ተቋም አማራጮች በመዲናችን ይገኛሉ::
▪️በቀጣይ ስለ ህክምና አማራጮቹ እንቃኛለን::

Reference
- Curriculum based motivational group by Ann Fields and Internet

ቸር ይግጠመን!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው: የአእምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም

25/05/2022

ሠሞኑን ተከሠተ የተባለው ቫይረስ አንደ ኮሮና ቫይረስ ተዛማች እና ገዳይ ይሆን?🤔

የጦጣ ፈንጣጣ (monkey pox)
📍የጦጣ ፈንጣጣ (monkey pox)ለመጀመሪያ ጊዜ በሰዉ ላይ የተገኘው እአአ በ1970 በ11 የአፍሪካ ሀገሮች ነው።

📍 May 2022፣ በርካታ የጦጣ ፈንጣጣ ተጠቂዎች በበርካታ አገሮች ተለይተው እየታወቁ ይገኛል።

📍እስከ may 19, በ12 ሀገራት ከ80 በላይ በበሽታው የተያዙ ሠዎች ተገኝተዋል። ሌሎች 50 ተጠርጣሪዎች በምርመራ ላይ ናቸው።

👉አንድ ሰዉ ለቫይረሱ ከተጋለጠ ከ6 እስከ 13 ቀናት ቡሃላ ምልክት ያሳያል ነገር ግን እስከ 21 ቀናት ሊደርስ ይችላል።

👉ይህ ቫይረስ በተለምዶ በጣም ተላላፊ ነው ተብሎ አይታሰብም ምክንያቱም ከአንድ ሰው ወደ ሌላው የሚተላለፈው በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ማለትም ከቁስሎች፣ ከሰውነት ፈሳሾች፣ ከመተንፈሻ አካላት ጠብታዎች ጋር ሲኖር ነው።

👉ሕጻናት እና የበሽታ መከላከል ችግር ያለባቸው ሰዎች በበለጠ ይጋለጣሉ እና በጦጣ በሽታ ሊሞቱ ይችላሉ።

ምልክቶች
📍ሙቀት እና ብርድ ብርድ ማለት
📍የእራስ ምታት
📍ከፍተኛ ድካም
📍ዉሃ የቋጠሩ ቁስሎች

👉ብዙ ጊዜ የጦጣ በሽታ ምልክቶች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በራሳቸው ይጠፋሉ, ነገር ግን በአንዳንድ ግለሰቦች ግን ወደ ከፍተኛ ህመምና ሞት ሊዳርጉ ይችላሉ።

ህክምናው
👉እስካሁን በሳይንስ የተረጋገጠ መድኃኒት የለውም። ምልክቶቹን ግን ማከም ይቻላል።

👉ቀደም ባሉት ጊዜያት የፈንጣጣ (small pox) ክትባት የተከተቡ ሰዎች እንዲሁ ከጦጣ በሽታ መከላከያ ይኖራቸዋል።

👉ቫይረሱ እንዴት እየተሰራጨ እንደሆነ መለየት እና ብዙ ሰዎችን ከበሽታው ለመጠበቅ WHO ቅድሚያ ሰጥቶ እየሠራበት ይገኛል እንዲሁም እንደ ኮሮና ቫይረስ አስጊ እንዳልሆነ ተገልጿል።

✍️ዶ/ር ያብስራ

Address

Enfraz
Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gashaw Clinic ጋሻው ክሊኒክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Gashaw Clinic ጋሻው ክሊኒክ:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram