21/11/2025
የብሽሽት ጉዳት ወይም የግሮይን ጉዳት_ Groin injury
**************************
ከትንሽ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የሚደርስ የብሽሽት ስጋዎች መሳሳብ ወይም መቆረጥ ጉዳት ነው።
ጉዳቱን ለመለዬት የ x ray, Ultrasound እና MRI ምርመራ አስፈላጊ ሲሆን
የጉዳት አይነቱ በ ሶስት ደረጃዎች ይታያሉ
ደረጃ 1፡የግሮይን ስጋ መሳሳብ ወይም እስከ 5% የሚሆኑት የግሮይን ስጋ ፋይበር ሲጎዱ
የተጎዳው ሰው ያለህመም መራመድ ሲችል ነገር ግን ሩጫ፣ዝላይ ፣ግጭት እንዲሁም የመሳሳብ እንቅስቃሴዎች ህመም እንዲኖር ያደርጋሉ።
ደረጃ 2፡ ይህ ደረጃ ከመጠን በላይ የሆነ የግሮይን ስጋ መቆረጥ tear ማድረግ ሲሆን መራመድ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል እንዲሁም የተጎዳው ሰው እግሮቹን ማጠጋጋት bringing leg close together አስቸጋሪ ይሆንበታል።
በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ የሁለቱን ብራዚላውያንን ጉዳት በሰማን ጊዜ ለመፃፍ ተገደድን...✍️
Get well soon and !
ዶር ጋሻዬ ታገለ (የአጥንትና መገጣጠሚያ ስፔሻሊስት ሐኪም)
በሳይንስ አምባ እስፔሻሊቲ ክሊኒክ ቀጠሮ ለመያዝ👉ረዕቡና አርብ
ይደውሉ:👉0966333377/0966333777