12/04/2026
ክንዳችሁን ዘርግታችሁ ደማችሁን ለግሳችሁ ህይዎት የታደጋችሁ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች፣መላው የደም እና ህብረህዋስ ባንክ ቤተሰቦች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!
ዛሬ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል የነሳበት ታላቅ ቀን ነው።
ክርስቶስ በመስቀል የተሸነፈ ቢመስልም፤ ነገር ግን በትንሳኤ ሞትን አሸንፎ ለዓለም ሕይወት አመጣ!
“እርሱ እዚህ የለም፤ ተነስቶአል!” (ሉቃስ 24፡6) ትንሳኤ የፍቅር፣ የመስጠትና የሕይወት መልእክት ነው። ይህን በውል በመገንዘብ ደም በመለገስ ህይዎት ለታደጋችሁ ወገኖች በዚህ በተከበረ ቀን ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ:: የደም ማሰባሰብ ስራ ቁርጠኛ እና ርሁሩህ ሰራተኛን ይፈልጋል፣ ከዚህ አንፃር የደም እና ህብረህዋስ ባንክ ሰራተኞች በማይመች የስራ ከባቢ ሳይቀር ለወገናቸው በህይዎት መኖር ከፍተኛ ትጋት አድርገዋል፣ እያደረጉም ነው፣ ምስጋና ይድረሳችሁ!!
🩸 ደም መስጠት ሕይወት ማዳን ነው
ትንሳኤን በፍቅር እና በመስጠት እናክብር
የእኛ ትንሽ ስጦታ ለሌሎች ታላቅ ሕይወት ሊሆን ይችላል
ትንሳኤው ሰላም፣ ጤናና ደስታ ወደ ቤታችሁ ያመጣ!
መልካም ፋሲካ!
የቡሌ ሆራ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ