Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital

  • Home
  • Ethiopia
  • Harar
  • Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital

Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital Hiwot Fana Comprehensive University Hospital (HFCSUH) is a central teaching and referral hospital under Haramaya University.

It serves an estimated 20-30 million population in Eastern Ethiopia.

12/04/2026
12/04/2026

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!

Baga Guyyaa Ayyaana Du'aa Ka'uu Yesuus Kiristoosif Nagaan Geessan!

ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Hordoftoota Amantaa Kiristaanaa Hundaaf Baga Ayyaana Du'aa Ka'uu Yesuus Kiristoos nagaan Geessan!

የ2018 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ከመላው ቤተሰብዎና ወዳጆችዎ ጋር የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የምህረትና የበረከት በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
Ayyaanni Faasikaa kan bara 2018 maatii fi hiiriyoota keessanif kan nagaa, kan jaalalaa,kan tokkummaa fi kan dhiifama akka isiniif ta'u hawwina!

መልካም በዓል!
Ayyaana Gaarii!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
Yuunivarsiitii Haramaayaa

08/04/2026
08/04/2026
የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በቀዶ ህክምና እስፔሻሊቲ ዘርፍ ያስተማራቸውን የህክምና ባለሞያዎች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ተጠናቀቀ ። ለ7ኛ ዙር የጠቅላላ ቀዶ ህክምና እስፔ...
07/04/2026

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በቀዶ ህክምና እስፔሻሊቲ ዘርፍ ያስተማራቸውን የህክምና ባለሞያዎች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ተጠናቀቀ ።

ለ7ኛ ዙር የጠቅላላ ቀዶ ህክምና እስፔሻሊቲ ትምህርት ፕሮግራም ለአራት አመታት ሲከታተሉ የነበሩ 11 የህክምና ተማሪዎች ለሁለት ቀናት ሲካሄድ በቆየው የብቃት ማረጋገጫ ምዘናን በላቀ ውጤት ማጠናቀቃቸውን በሐረማያ ዩኒቨርስቲ የሕይወት ፋና ኮሞፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ፋሲል ወንድሙ አስታውቀዋል ።

ዶክተር ፋሲል አክለውም በዛሬው እለት ምዘናቸውን ያጠናቀቁ ብቁ የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ባለሞያዎችን ጨምሮ በአገራችን የቀዶ ህክምና ዘርፍን የበለጠ ለማጎልበት በሰብ እስፔሻሊቲ ፕሮግራም የኮሎሬክታል ቀዶ ህክምና (Colorectal surgery) ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል ።

በጤናው መስክ የቀዶ ህክምና ዘርፉን የበለጠ እገዛ ማድረግ የሚችሉ እና ማህበረሰቡን የሚያገለግሉ ባለሞያዎችን በማፍራት ሂደት ውስጥ ጥራት እና ብቃትን ለማረጋገጥ ምዘናዎች አስፈላጊ መሆናቸው ተገልጿል።

በህክምና ትምህርት አለም በተጋባዥ ሐኪሞች የሚሰጠው ምዘና ተማሪዎች በነበራቸው ቆይታ ያገኙት እውቀት እና ክህሎትን ተጠቅመው ማህበረሰባቸውን ለማገልገል ብቁ መሆናቸው የሚረጋገጥበት መሆኑን አውስተው የሐረማያ ዩኒቨርስቲ በቀዶ ህክምና እስፔሻሊቲ ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ጥሩ ደረጃ ላይ መሆናቸውን እንደገመገሙ ዶክተር እንዳለ አበበ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ገልፀዋል ።

ዶክተር በቀለ አያሌው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሎሬክታል ሰርጅን በበኩላቸው ለምዘና የቀረቡ ተማሪዎች ተገቢውን የቀዶ ህክምና እውቀት እና ክህሎት መጨበጣቸውን ተመልክተናል በዚህም ለሌሎች ጥሩ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ማለፋቸውን አስመስክረዋል ብለዋል ።

በመጀመሪያ የህክምና ሙያ ዲግሪውን ከአዋሳ ዩኒቨርስቲ አጠናቆ በጠቅላላ ቀዶ ህክምና እስፔሻሊቲውን በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ያጠናቀቀው ዶክተር አስቻለው ዘየደ የነበረው ቆይታ ጥሩ መሆንን ገልፆ እለት እለት የነበረው ተግባር ላይ መሠረት ያደረገው የትምህርት ቆይታ ተገቢውን እውቀት እና ክህሎት ማግኘቱን ገልጿል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በመጡ አራት የዘርፉ ሰብ እስፔሻሊስት እና እስፔሻሊስት ባለሞያዎች ውጪያዊ የብቃት ማረጋገጫ ምዘናው ተሰጥቷል ።

የእስፔሻሊቲ ተማሪዎች ያላቸውን ውጤት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጉባኤ (ሴኔት) መርምሮ ሲያፀድቅላቸው የእስፔሻሊቲ ሰርተፊኬታቸውን የሚያገኙ ይሆናል ።

ዘጋቢ : ታደለ ጥላሁን
ፎቶ ግራፈር በሐይሉ ግርማ
መጋቢት 29/2018 ዓ.ም
የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት ክፍል

Address

Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share