14/04/2026
ሕዝበኝነት የሐሳብ አልባ ፓለቲከኞች መመርኮዣ ነዉ፡፡
የማንነትንም ሆነ የሐሳብ ብዝኃነትን የሚያስተናግዱበት ዕዉቀትም፤ እዉነትም፤ ፍላጎትም የላቸዉም፡፡ ዓለምን የሚመለከቷት “የእኔ” በሚሉት አጥር ዉስጥ ነዉ፡፡ አጥራቸዉን ለማስጠበቅ የልዩነት ዘርን ይዘራሉ፡፡ የእኛ ብሔር፤ የእኛ ሐይማኖት፤ የእኛ መሬት ፤ የእኛ …በሚል ትንታኔ፤ ሕዝብን የራስ ሃብትና ሥልጣን ማስገበሪያ እያደረጉ ሌሎችን ነጣቂ ተኩላ አድርገዉ ያቀርባሉ፡፡
- የመደመር መንግሥት - ገጽ - 374