Mohammad Getachew Medium Clinic

Mohammad Getachew Medium Clinic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mohammad Getachew Medium Clinic, Medical and health, Harbu.

Mohammed Getachew Medium Clinic, Harbu, Kebele 01, He entered 200 meters on the way from Zenbaba to the HC
መሀመድ ጌታቸው መካከለኛ ክሊኒክ
አድራሻ:- ሀርቡ ከዘንባባ ወደ ጤና ጣቢያ መወረጃ 200 ሜትር ወረድ ብሎ በስተግራ ከወፍጮ ቤቱ ፊትለፊት እንገኛለን።

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ
06/10/2025

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

19/09/2025
🫘🫘ስለ ኩላሊት ጠጠር ማወቅ ያለብዎ ጠቃሚ መረጃ 🫘🫘✍️ የኩላሊት ጠጠር ማለት በኩላሊታችን ውስጥ ከሚገኙ ማዕድናት እና ጨዎች ተሰባስበው እና ደርቀው የሚፈጠሩ ጠንካራ ክምችቶች ናቸው። እነዚ...
18/09/2025

🫘🫘ስለ ኩላሊት ጠጠር ማወቅ ያለብዎ ጠቃሚ መረጃ 🫘🫘

✍️ የኩላሊት ጠጠር ማለት በኩላሊታችን ውስጥ ከሚገኙ ማዕድናት እና ጨዎች ተሰባስበው እና ደርቀው የሚፈጠሩ ጠንካራ ክምችቶች ናቸው። እነዚህ ጠጠሮች መጠናቸው ከአሸዋ ቅንጣት እስከ ጎልፍ ኳስ ሊደርስ ይችላል። መጠናቸው አነስተኛ ሲሆን ብዙ ጊዜ ሳናውቀው ከሽንታችን ጋር ታጥበው ይወጣሉ፤ ነገር ግን መጠናቸው ሲጨምር የሽንት ቧንቧን በመዝጋት ከፍተኛ ህመም ያስከትላሉ።

👉 የኩላሊት ጠጠር ለምን ይከሰታል?

✳️ የኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር የሚያደርጉ ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
💧 በቂ ውሃ አለመጠጣት፦ ይህ ዋነኛው መንስኤ ነው! ውሃ በበቂ ሁኔታ ካልጠጣን ሽንታችን ስለሚወፍር በውስጡ ያሉ ማዕድናት በቀላሉ እንዲረጋጉና ጠጠር እንዲሰሩ ያደርጋል።

🥗 የአመጋገብ ስርአት፦
• ከፍተኛ የጨው፣ የስኳር እና የእንስሳት ተዋፅኦ (ስጋ) አጠቃቀም።
• ኦግዛሌት (Oxalate) በብዛት ያላቸውን ምግቦች (እንደ ስፒናች፣ ለውዝ፣ ቸኮሌት) አብዝቶ መመገብ።

👨‍👩‍👧 የቤተሰብ ታሪክ (በዘር)፦ በቤተሰብ ውስጥ የኩላሊት ጠጠር ተጠቂ ካለ ለችግሩ ተጋላጭነት ይጨምራል።

🩺 ሌሎች የጤና እክሎች፦
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት።
• ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን።
• የምግብ መፈጨት ችግሮች እና አንዳንድ ቀዶ ጥገናዎች።

💊 አንዳንድ መድሃኒቶች፦ የተወሰኑ መድሃኒቶች ለጠጠር መፈጠር አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይችላሉ።

✳️ ምልክቶች፡
የኩላሊት ጠጠር በተለይ ከቦታው ሲንቀሳቀስ የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያል፦
🔸 ከባድ የህመም ስሜት፦ በጎንና በጀርባ፣ ከጎድን አጥንት በታች የሚሰማ ድንገተኛና በጣም ከባድ ህመም። ህመሙ ወደ ታችኛው የሆድ ክፍል እና ብልት አካባቢ ሊሰራጭ ይችላል።
🔸 የሚቆርጥ ህመም፦ ህመሙ በየተወሰነ ጊዜ እየመጣ የሚሄድ (በማዕበል መልክ) እና የሰውነት አቋቋምን ሲቀይሩ የማይሻሻል አይነት ነው።
🔸 በሽንት ጊዜ የማቃጠል ወይም የህመም ስሜት።
🔸 የሽንት ቀለም መቀየር፦ ሽንት ወደ ሮዝ፣ ቀይ ወይም ቡናማ ቀለም ሊቀየር ይችላል (የደም ምልክት ነው)።
🔸 የደፈረሰ ወይም መጥፎ ሽታ ያለው ሽንት።
🔸 ቶሎ ቶሎ የሽንት መምጣት ወይም
🔸 ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ።
🔸 ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት (ኢንፌክሽን መኖሩን ሊያመለክት ይችላል)።

✳️ የኩላሊት ጠጠር ዓይነቶች፡

የኩላሊት ጠጠር በተሰራበት የማዕድን አይነት በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦
1️⃣ የካልሲየም ኦግዛሌት ጠጠር (Calcium Oxalate)፦ በብዛት የሚከሰተው የጠጠር አይነት ነው።
2️⃣ ስትሩቫይት ጠጠር (Struvite)፦ አብዛኛውን ጊዜ ከሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ጋር ተያይዞ ይከሰታል።
3️⃣ የዩሪክ አሲድ ጠጠር (Uric Acid)፦ በቂ ውሃ ካለመጠጣትና ብዙ ቀይ ስጋ ከመመገብ ጋር ይያያዛል።
4️⃣ ሲስቲን ጠጠር (Cystine)፦ በዘር የሚመጣና ብዙ ጊዜ የማይከሰት ነው።

🩺 ሕክምናው
ሕክምናው በጠጠሩ መጠን፣ አይነት እና በሚያስከትለው ህመም ይወሰናል።

🌟 ለአነስተኛ ጠጠሮች፦
▶️ ብዙ ውሃ መጠጣት፦ ጠጠሩ በሽንት ታጥቦ እንዲወጣ በቀን ከ2-3 ሊትር ውሃ መጠጣት።
▶️ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች፦ ህመሙን ለመቆጣጠር ይረዳሉ።
▶️ የሽንት ቧንቧን ዘና የሚያደርጉ መድሃኒቶች፦ ጠጠሩ በቀላሉ እንዲያልፍ ይረዳሉ።
▶️ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ፦ ካለ ህክምና ማድረግ እና አስፈላጊውን የኢንፌክሽን መድሃኒት መውሰድ በሀኪም ትዛዝ

🌟 ለትላልቅ ጠጠሮች፦
⏩ በድምፅ ሞገድ ማፈንዳት (ESWL)፦ ከሰውነት ውጪ በሚፈጠር የድምፅ ሞገድ ጠጠሩን ወደ ትናንሽ ፍርስራሾች በመከፋፈል በሽንት እንዲወጣ ማድረግ።
⏩ በቀዶ ጥገና ማስወገድ፦ ዩሬትሮስኮፒ (Ureteroscopy)፦ ካሜራ የተገጠመለት ቀጭን ቱቦ በሽንት ቧንቧ በኩል በማስገባት ጠጠሩን ማውጣት ወይም በሌዘር መስበር።
⏩ ፐርኩታኒየስ ኔፍሮሊቶቶሚ (PCNL)፦ በጀርባ በኩል ትንሽ ቀዳዳ ሰርቶ በቀጥታ ወደ ኩላሊት በመግባት ትላልቅ ጠጠሮችን ማስወገድ።

❇️ እንዳይከሰት መደረግ ያለበት
አንዴ ከያዘን ዳግም የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ስለሆነ መከላከሉ በጣም አስፈላጊ ነው።

✅ ውሃ፦ በቀን ቢያንስ ከ2-3 ሊትር ውሃ መጠጣት። ሽንት ቀለማችን ፈካ ያለ ቢጫ ቀለም ሊኖረው ይገባል።
✅ የሎሚ ጭማቂ፦ በውሃ ውስጥ የሎሚ ጭማቂ ጨምሮ መጠጣት የካልሲየም ጠጠር እንዳይፈጠር ይረዳል።
✅ ጨው መቀነስ፦ በምግብ ውስጥ የሚጠቀሙትን የጨው መጠን መቀነስ ያስፈልጋል።
✅ የእንስሳት ፕሮቲንን መቀነስ፦ የቀይ ስጋ፣ የዶሮ እና የአሳ አመጋገብ መቀነስ።
✅ ጤናማ አመጋገብ፦ በአትክልትና ፍራፍሬ የበለፀገ ምግብ።
✅ ጤናማ ክብደት፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እና አመጋገብን በማስተካከል ጤናማ ክብደት እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል።

የተጠቀሱት ምልክቶች ከታዩብን ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የባለሙያ ምክር እና ህክምና ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው::

♻️ #የራስወ እና የቤተሰብዎ ጤና ያሳስበዎታል #
እንግዳውስ 🚶🚶🚶🏾‍♀️🚶🏿‍♂️🚶🏼‍♀️⤵️

ወደ ክሊኒካችን ወጥተው ስለ ጤናዎ ምርመራም ሆነ የምክር አገልግሎት ማግኘት ከፈለጉ መሀመድ ጌታቸው መካከላኛ ክሊኒክ መጥተው ይጎብኙን በመልካም መስተንግዶ ከተሟላ ላቦራቶሪ ፣ አልትራሳውንድ ፣ የልብ ራጂ (ECG) እና ሌሎች ዘመኑ ባፈራቸው መመርመሪያ መሳሪያዎችን አሟልቶ የረጅም ጊዜ የሆስፒታል ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ጋር ከ24 ሰዓት አገልግሎት ጋር እንጠብቀወታለን ።

🌏 #አድራሻ
📍 Wollo [ወሎ] 💖 ሀርቡ 💖
📍🏥መሀመድ ጌታቸው መካከላኛ ክሊኒክ 🏥

ሀርቡ ከተማ 01 ቀበሌ ወደ ጤና ጣቢያ በሚወስደው መንገድ ከኑር መስጊድ ከፍ ብሎ ከወፍጮ ቤቱ ፊት ለፊት እንገኛለን።

☎️Tel. 09-20 -21-68-07
09- ዐ6-80-97-80

/ወደ ቴሌግራም ገፆችን ይቀላቀሉ /
https://t.me/mameclinic

ታማኝ የጤናዎ አጋር !
መሀመድ ጌታቸው መካከለኛ ክሊኒክ

✓        የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀         በአለማችን ያሉ ሴቶችን በብዛት ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች አራተኛውን ደረጃ የያዘው የማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚባለ...
27/04/2025

✓ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር
🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀🦀

በአለማችን ያሉ ሴቶችን በብዛት ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች አራተኛውን ደረጃ የያዘው የማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚባለው የካንሰር ዓይነት ነው፡፡ ይህን በሽታ ለየት የሚያደርገው ከ80% በላይ የሚያጠቃዉ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች የሚኖሩ ሴቶችን መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ቅድሚያ በሚሰጡ ክትባቶች እንዲሁም በግዜ አግኝቶ ለማከም የሚረዳውን (papsmear) የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡

✍️ አጋላጭ መንገዶች
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ዋናዎቹ አጋላጭ መንገዶች የሚከተሉት ናቸ፡፡

1. (HPV) ቫይረስ
በዚህ ካንሰር ከመጋለጥ ዋና ዋናዎቹ መንገዶች አንዱ ልቅ በሆነ የግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፈው ይህ ቫይረስ ሲሆን ብዙውን ጊዜ በሽታው ምልክቶች ሳይኖሩት በሰውነት ውስጥ ኖሮ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ሊያመጣ ይችላል፡፡
ይህን ለመከላከል የሚረዳ ክትባት እድሚያቸው ከ 17 – 25 እንዲሁም ከ 25-40 ዓመት ላሉ ሴቶች መስጠት ተጀምሯል፡፡

2. ሲጋራ ማጨስ
3. የአባላዘር በሽታ የተያዙ ሴቶች (HIV) ጨምሮ
4. ለረጅም ጊዜ ማለትም ከ5 አመት በላይ በክኒን የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል የሚወስዱ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ መንገዶች በጥቂቱ ምክንያት ሊሆኑ ቢችሉም በተለይ በHPV ቫይረስ መጠቃት ግን በሁሉም በበለጠ ተፅእኖ የሚያመጣ መንገድ ነዉ፡፡

✍️ ምልክቶች

የማህፀን ጫፍ ካንሰር ወደ ውስጠኛው የማህፀን በር ክፍል ገብቶ በደንብ ከመዛመቱ በፊት በተያዘችው ሴት ላይ ምንም ዓይነት ምልክቶች አያሳይም፡፡ ይህም ነው የማህፀን ጫፍ ምርመራ (papsmear) ለሁሉም ከ 22 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ቢያንስ በዓመት አንዴ መመርመር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ የሚነገረዉ፡፡

👉 ከመዛመቱ በፊት ማወቅ ከተቻለ ከነጭራሹ ማጥፋት ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን ካልቻለ ግን
1. ከወር አበባ ውጪ ከማህፀን የደም መፍሰስ
2. በግንኙነት ጊዜ ህመም ወይም መድማት መኖር
3. ሀይለኛ ሽታ ያለው የማህፀን ፈሳሽ መኖር
4. እንዲሁም የማህፀን አካባቢ ህመም እንደ ምልክት ሊታይ ይችላል፡፡

✍️ ህክምና

አንዲት ሴት የማህፀን ካንሰር መያዟ ከታወቀ በኋላ በመጀመሪያ የተዛመተበት ደረጃ መታወቅ አለበት፡፡ ይህንን በመመርኮዝ ህክምናውን መምረጥና መስጠት ይቻላል፡፡ ደረጃውም የሚወስነው ከማህፀን ጫፍ ላይ ብቻ መሆኑን ወይም ከዛ አልፎ የሰውነት ማጣሪያ ዕጢዎች (lymphnodes) መግባቱን እንዲሁም ከዛም አልፎ ወደ ሌሎች የሰዉኑት ክፍሎች መዛመቱን በማረጋገጥ ነው፡፡

✍️ እነዚህ ህክምናዎች የሚከተሉት ናቸው

👉 በማህፀን ጫፍ ላይ የተወሰነ ከሆነ በቀዝቃዛ ናይትሮጅን አማካኝነት የካንሰሩን ቦታ የማጥፋት ህክምና (cryotherapy).

👉 ከዚህ አልፎ ወደ ሁለተኛው ክፍል ከገባ የጨረር እንዲሁም የኬሞቴራፒ ህክምና ከማህፀን ጫፍ ቀዶ ጥገና ጋር

👉 በመጨረሻም ወደሌሎች የሰውነት ክፍሎች ከተዛመተ ሙሉ የማህፀን ማውጣት ቀዶ ጥገናን ጨምሮ የጨረርና የኬዎቴራፒ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

👉 በአጠቃላይ ማንኛውም ሴት አስቀድማ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ (papsmear) በማድረግ እንዲሁም የ HPV ቫይረስ ክትባት በመውሰድ ይህንን ከ270,000 በላይ ሴቶች በአመት የሚገድለውን አደገኛ ካንሰር መከላከል ትችላለች፡፡

👉 ከዚህ ጋር ተያያዞ ለማስጠንቀቅ የምንወደው በዚህ ከሚሞቱት ሴቶች 80% የሚሆኑት በታዳጊ አገር የሚኖሩ በመሆናቸው የተለየ ጥንቃቄና ትኩረት እያንዳንዱ ሴት ሊሰጥ እንደሚገባና አጋላጭ መንገዶቹን በማስወገድና መከላከያ መንገዶችም በመጠቀም የመያዝ መጠኑን በደምብ መቀነስ እንደሚቻል ነው፡፡

🌏 #አድራሻ

📍 Wollo [ወሎ] 💖 ሀርቡ 💖
📍🏥መሀመድ ጌታቸው መካከላኛ ክሊኒክ 🏥

/ ወደ ቴሌግራም ግሩፓችን ይቀላቀሉ /
https://t.me/mamegclinic

🩺 የስኳር በሽታ (Diabetes Mellitus) ~~~~~~~~~~~~~~~~~~✅ የስኳር በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?            🔹ቶሎ ቶሎ መሽናት            🔹 ከፍተኛ የሆነ...
19/04/2025

🩺 የስኳር በሽታ (Diabetes Mellitus)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~

✅ የስኳር በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
🔹ቶሎ ቶሎ መሽናት
🔹 ከፍተኛ የሆነ ውሃ ጥማት፣ ረሃብ
🔹 ክብደት መቀነስና ድካም
🔹 አይን ላይ ብዥ ማለት

💉 የስኳር በሽታ ምልክቶች ሲኖሩ ቶሎ መታከም የሚጠቅመው ለምንድን ነው?

💊 ስኳር በሽታ በቶሎ ካልታከመና በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በፍጥነት በቁጥጥር ስር ካልዋለ የተለያዩ የጤና እክሎችን ሊያስከትል ይችላል።
ከእነዚህ ችግሮች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው።
🔹 የልብ ድካም ( Heart Attack)
🔹 ስትሮክ (Stroke)
🔹 የኩላሊት ችግር
🔹 የአይን ችግር
🔹 የእጅና እግር መደንዘዝ (Peripheral Neuropathy)
🔹 ከደም ስሮች ጋር የተያያዘ የጣቶች ወይም የሌሎች ሰውነት ክፍሎች በሽታ ( ለእግር ወይም እጅ መቆረጥ ሊዳርግ ይችላል)

🟦 የስኳር በሽታ ዓይነቶች ምንድናቸው?
👉 1ኛው ዓይነት የስኳር በሽታ (Type I Diabetes) የሚከሰተው ቆሽት በቂ ኢንሱሊን ማመንጨት ሲያቅተው ነው። ሁሌም ባይሆን በአብዛኛው ይህ የስኳር በሽታ ዓይነት ከ40 ዓመት በታች ባሉ ሰዎች ላይ ይከሰታል። ታካሚዎች በአብዛኛው ከመጠን ያለፈ ወፍራም አይባሉም። ይህ ዓይነቱ የስኳር በሽታ ሁልጊዜ በመርፌ መልክ በሚሰጥ መድኃኒት ( Insulin) ይታከማል።

👉 2ኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ( Type II Diabetes) የሚከሰተው ሰውነት ቆሽት ያመረተውን ኢንሱሊን መቀበል ሲያቅተውና ኢንሱሊን በዚሁ ምክንያት አቅም ሲያጣ ነው። በአብዛኛው ይህ የስኳር በሽታ ዓይነት ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ በሆኑና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ባላቸው ሰዎች ላይ ይከሰታል። እንደ አስፈላ ጊነቱ በሚዋጥ መድኃኒት ወይም መርፌ (Insulin) ይታከማል። የዚህ ዓይነቱ ስኳር በሽታ ታካሚዎች ላይ የህመሙ ምልክቶች ሳይታዩ ለረዥም ጊዜ ስለሚቆዩ ቅድመ ምርመራ ካልተደረገ በስተቀር ስኳር መኖሩ ላይታወቅ ይችላል። በዚህም ምክንያት በጊዜ ስለማይታከሙ ከላይ የተጠቀሱት የጤና እክሎች ይከሰታሉ።

💉 ስኳር እንዴት ይታከማል?

ይቀጥላል...

🌏 #አድራሻ

📍 Wollo [ወሎ] 💖 ሀርቡ 💖
📍🏥መሀመድ ጌታቸው መካከላኛ ክሊኒክ 🏥

/ ወደ ቴሌግራም ግሩፓችን ይቀላቀሉ /
https://t.me/mamegclinic

የኩላሊት ህመም ምልክቶች====================የኩላሊት ህመም ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው ይለያያሉ። መሰረታዊ የህመሙ ዓይነት እና እንደ ክብደቱ  የህመሙ ምልክት ይወሰናል። ምልክቶቹ ...
17/04/2025

የኩላሊት ህመም ምልክቶች
====================
የኩላሊት ህመም ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው ይለያያሉ። መሰረታዊ የህመሙ ዓይነት እና እንደ ክብደቱ የህመሙ ምልክት ይወሰናል። ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ ፣ ግልጽ ያልሆኑ እና አስደንጋጭ ያልሆኑ ናቸው። ስለሆነም በህመሙ የመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ህመም ስለመኖሩ ለመለየት አዳጋች ነው።

✅ የኩላሊት ህመም በአብዛኛውን ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች

👉 የፊት እብጠት
የፊት ፣ የሆድ እና የእግር እብጠት ብዙ ጊዜ የኩላሊት ህመም ማሳያ ነው። በኩላሊት ህመም ምክንያት የሚከሰት እብጠት አንድ ባህሪይ በመጀመሪያ ከዐይን ሽፋኖቹ በታች የሚስተዋል መሆኑ ነው ፡፡ ይህም በማለዳ በጣም ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን እብጠት የግድ የኩላሊት መጎሳቆልን እንደማያመለክት ልብ ልንለው ይገባል። በተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ መደበኛ የኩላሊት ሥራ ቢኖርም እብጠት ይከሰታል (ለምሳሌ ኔፍሮቲክ ሲንድሮም)። ከዚህም ጎን ለጎን መረዳት የሚያስፈልገው ከባድ ህመም ቢከሰትም በአንዳንድ ታካሚዎች ላይ እብጠት ላይታይ እንደሚችል ነው።

👉 የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ
የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ በአፍ ውስጥ ያልተለመደ ጣዕምና የምግብ መመገብ ደካማነት የኩላሊት ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚያጋጥማቸው የተለመዱ ችግሮች ናቸው። የከፋ የኩላሊት ድክመት በሚኖርበት ጊዜ የማቅለሽለሽ ፣ ማስመልስ እና የአእምሮ ህመም የሚያስከትሉ መርዛማ ንጥረነገሮች መጠን እየጨመረ ይሄዳል።

👉 ከፍተኛ የደም ግፊት
የኩላሊት ችግር ያለባቸው ታካሚዎች ብዙውን ጊዜ የደም ግፊት ይኖራቸዋል። የደም ግፊት ችግር በወጣትነት ዕድሜ (ከ 30 ዓመት በታች) ከተገኘ ወይም በምርመራው ወቅት የደም ግፊት በጣም ከፍተኛ ከሆነ ምክንያቱ የኩላሊት በሽታ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ያስፈልጋል።

👉 የደም ማነስ እና ድክመት
ቶሎ መድከም ፣ ማተኮር አለመቻል እና የቆዳ መገርጣት የደም ማነስ ችግር ያለበት ሰው የተለመዱ ምልክቶች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ሥር የሰደደ የኩላሊት መድከም የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ አንድ ሰው የሚያሳያቸው ብቸኛ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። የደም ማነስ ያለበት ሰው በመደበኛ ህክምና በተለምዶ በሚሰጡ መድኃቶች ካልዳነ፣ የኩላሊት ህመም እንዳለበት መጠርጠር ያስፈልጋል።

👉 ከዚህም ተጨማሪ ምልክቶች -ዝቅተኛ የጀርባ ህመም ፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም ፣ እና የእግር ማሳከክ እና ህመም በኩላሊት ህመም ውስጥ ተደጋጋሚ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው። በደንብ አለማደግ ፣የቁመት ማጠር እና የግር አጥንት ቀጥ አለማለት በልጆች ላይ የኩላሊት ህመም የሚያሳይ ነው።

🔷 የተለመዱ ምልክቶች
1. በሽንት መጠን መቀነስ ፣ በተለያዩ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ በጣም የተለመደ ነው።

2. ሽንት በሚወገድበት ወቅት የሚያቃጥል ስሜት ፣ በተከታታይ መሽናት (ያልተለመደ ድግግሞሽ) እንዲሁም ደም ወይም መግል በሽንት ውስጥ ማየት የሽንት ቧንቧ ህመም የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው።

3. የሽንት ፍሰት መዘጋት ሽንትን ለማስተላለፍ ችግር ያስከትላል።

ምንም እንኳን አንድ ሰው ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ሊያሳይ ቢችልም የግድ ሰውዬው በኩላሊት ህመም ተይዟል ማለት ግን አይደለም። ሆኖም እንደዚህ አይነት ምልክቶች ባሉበት ሁኔታ ሀኪምን ማማከር እና የኩላሊት ህመም እና ሌሎች ህመሞች መኖር ወይም አለመኖራቸውን በደም እና በሽንት ናሙና ምርመራዎች ማረጋገጥ የግድ ይላል።

አድራሻ
📍 Wollo [ወሎ] 💖 ሀርቡ 💖

📍🏥መሀመድ ጌታቸው መካከላኛ ክሊኒክ 🏥

/ ወደ ቴሌግራም ግሩፓችን ይቀላቀሉ /
https://t.me/mamegclinic

🚬ሲጋራ ማጨስ እና የጤና መዘዞቹ🚬   ✓❌❌❌❌❌❌❌❌●ሲጋራ ማጨስ ለተለያዩ የጤና እክሎች ያጋልጣል:◇የልብ  እና የሳምባ ችግሮች ◇ስትሮክ◇በሴቶች እና ወንዶች መካንነትን ሊያስከትል ይችላል◇...
13/04/2025

🚬ሲጋራ ማጨስ እና የጤና መዘዞቹ🚬 ✓
❌❌❌❌❌❌❌❌
●ሲጋራ ማጨስ ለተለያዩ የጤና እክሎች ያጋልጣል:

◇የልብ እና የሳምባ ችግሮች
◇ስትሮክ
◇በሴቶች እና ወንዶች መካንነትን ሊያስከትል ይችላል
◇የጥርስ እና የድድ ጤናን ይጎዳል
◇ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ያስከትላል
◇የበሽታ መከላከል አቅምን ይቀንሳል
◇እንዲሁም የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ካንሰርን ያስከስታል :
♧የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ
♧የደም
♧የማህጸን በር ጫፍ
♧የአንጀት እና የፊንጢጣ
♧የጉሮሮ፣ ምላስ፣ ላንቃ፣ ቶንሲል እንዲሁም የምግብ ቱቦ ካንሰር
♧የጉበት፣ ቆሽት እና የጨጓራ ካንሰር
♧የአየር ቱቦ እና ሳምባ ካንሰር ያስከትላል
◇እንዲሁም በካንሰር የመሞት እድልን ይጨምራል

⏰ ሲጋራ ማጨስ ለማቆም ግዜው አሁን ነው!!!⏰

አድራሻ
📍 Wollo [ወሎ] 💖 ሀርቡ 💖
📍🏥መሀመድ ጌታቸው መካከላኛ ክሊኒክ 🏥

/ ወደ ቴሌግራም ግሩፓችን ይቀላቀሉ /
https://t.me/mamegclinic

እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡🌙⭐️ ኢድ ሙባረክ  !!! ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አእመል !!! ⭐️🌙
29/03/2025

እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

🌙⭐️ ኢድ ሙባረክ !!! ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አእመል !!! ⭐️🌙

የህጻናት የሳንባ አለርጂ (አስም በሽታ)      የህጻናት የሳንባ አለርጂ(አስም በሽታ) አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎች ተጽእኖ ከሚገባው በላይ በድንገትኛ እ...
04/03/2025

የህጻናት የሳንባ አለርጂ (አስም በሽታ)

የህጻናት የሳንባ አለርጂ(አስም በሽታ)
አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎች ተጽእኖ ከሚገባው በላይ በድንገትኛ እና ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ አየር ቧንቧ መጥበብ ነው።

የአስም በሽታ የሚያጠቃው የሳንባችንን የአየር ቧንቧዎች ሲሆን እነዚህን ቧንቧዎች በማጥበብ እና በቂ አየር ወደ ሳንባችን እንዳይገባና እና እንዳየወጣ የሚያደርግ ነው፡፡

ዋና ምክንያቱ ተፈጥሯዊ እና አካባቢያዊ ቀስቃሽ ነገሮች የሚፈጠረው መስተጋብር አየር ባንቧን ለዘለቀ ብግነት በማጋለጥ አለርጅ ቀስቃሽ ሽታዎች ሲኖሩ የአየር ቧንቧ ከልክ ያለፈ ተለዋዋጭ ጥበት በ ማምጣት ወደ ሳምባ የገባ አየር ከሳንባ በሚፈለገው ልክ እንዳይወጣ በማድረግ የመታፈን ምልክት ያመጣል

የአየር ቧንቧዎች እድገትና መስፋትን ተከትሎ ህፃናት ላይ የአየር ቧንቧ መቆጣት(አለርጂ) ከ 5 እስከ 7 አመት በኋላ የመጥፋት እድሉ ከፍተኛ ነው። በመሆኑም እስከ 7 አመት ያሉ ሕፃናት ላይ የሚከሰት የሳንባ አለርጂን አስም ብለን አንጠራውም።

#የሳንባ አለርጂ(አስም) ቀስቃሽ ሁኔታዎች
👉ጭስ ( የሲጋራ፣ የማገዶ፣ ምድጃ ወዘተ)
👉የተለያዩ ሽታዎች (ሽቶ፣ ሰንደል፣ ቀለም፣ ሻማ ወዘተ)
👉እርጥበት እና ቅዝቃዜ ያለው ስፍራ
👉የጉንፋን ቫይረስ
👉የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
👉የቤት ውስጥ እንስሳት ድመት፣ ውሻ ወዘተ

#አጋላጭ ሁኔታዎች
👉 የቆዳ ወይም የአፍንጫ አለርጂ ያለባቸዉ ህፃናት
👉የምግብ አለርጂ ያለባቸዉ ህፃናት
👉እናት ወይም አባት አስም ካለባቸዉ
👉በቤት ዉስጥ ሲጋራ የሚያጨስ ሰዉ ካለ

#ምልክቶች
👉ሳል(በተለይም ጧትና ማታ እንዲሁም በቅዝቃዜ ወቅትየሚጨምር)
👉ትንፋሽ (አየር) ማጠር
👉ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
👉ደረት አካባቢ ሲር ሲር የሚል ድምፅ (Wheezing)
👉በሚተነፍሱበት ጊዜ የደረት ወደውስጥ መግባት
👉 የድካም ስሜት እና ላበት
👉በትንፋሽ ማጠር ምክንያት ለመተኛት መቸገር
👉ራስ ምታት፣ የትኩረት መቀነስ፣ እና አቅልን መሳት
👉የፊት እና የከንፈር መገርጣት/ሰሰማያዊ መምሰል

#ህክምናው
👉የአየር ማጠር ካለ ባፋጣኝ ድንገተኛ ህክምና እንዲያገኙ አቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ተቋም መውሰድ ያስፈልጋል።
👉 የአየር ቧንቧን ጥበት የሚያስተካክሉ መድሀኒቶች (ሳልቡታሞል) መስጠት። እስከ ስምንት አመት ያሉ ልጆች በቀላሉ መሳብ ስለማይችሉ ሰፔሰር በመጠቀም ወይም ከውሀ ማሸጊያፕላስቲክ(ሀይላንድ) በማዘጋጀትና ውስጡ በመንፋት እንዲስቡ ማድረግ። አሰጣጡ እና መጠኑን ከሀኪሞ በአግባቡ መረዳት ያስፈልጋል።
👉 የአየር ቧንቧ ብግነትን የሚቀንስ መድሃኒቶች መሰጠት
👉 አስም ቀስቃሽ የሆነውን ህመም ማከም
👉 ቤትን ከአስም ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ነጻ በማድረግ አስም እንዳይነሳ መከላከል
👉 በቅዝቃዜ እና ጉንፋን በሚበዛባቸው ወቅቶች የአስም ቅድመ መከላከል መድሃኒት መስጠት ይመከራል

#የልጆቾዎ ጤና አመጋገብ #
ያሳስበዎታል እንግዳውስ ወደ መሀመድ ጌታቸው መካከላኛ ክሊኒክ ጋር በልጀዎ ዙሪያ ላይ የማማከር ሆነ የማንኛውንም የህፃናት ህክምና እንሰጣለን.

#አድራሻ
📍 Wollo [ወሎ] 💖 ሀርቡ 💖
📍🏥መሀመድ ጌታቸው መካከላኛ ክሊኒክ 🏥

ሀርቡ ከተማ 01 ቀበሌ ከዘንባባ ወደ ጤና ጣቢያ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ርቀት ላይ በስተ ግራ ከወረፍጮ ቤት ፊት ለፊት እንገኛለን።

📲 Tel. 09-2021-68-07
📲 09-1491-37-21

/ ወደ ቴሌግራም ፔጃችን ይቀላቀሉ /
https://t.me/mohammedmediumclinic

መሀመድ ጌታቸው መካከለኛ ክሊኒክ
እዉነተኛ እና ታማኝ የጤናዎ አጋር !

Ramadan Mubarak
04/03/2025

Ramadan Mubarak

Address

Harbu
000

Telephone

+251920216807

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mohammad Getachew Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Mohammad Getachew Medium Clinic:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram