Dr Girum Telederma

Dr Girum Telederma ለማንኛውም የቆዳ ላይ ችግር በተንቃሳቅሽ ምስል(video) ፣ በድም?

ፒኮሴኮንድ ሌዘር  በዚህ የህክምና ዘርፍ የመጨረሻው ደረጃ ቴክኖሎጂ ሲሆን ፡በተለያየ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ መልክ መቀየርን ለማጥፋት ይረዳል፡፡ በተለይም፡ለንቅሳት ለማድያት ለሽታ ( n...
13/03/2023

ፒኮሴኮንድ ሌዘር
በዚህ የህክምና ዘርፍ የመጨረሻው ደረጃ ቴክኖሎጂ ሲሆን ፡በተለያየ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ መልክ መቀየርን ለማጥፋት ይረዳል፡፡ በተለይም፡
ለንቅሳት
ለማድያት
ለሽታ ( naevus of Ota ፥ naevus of Ito ...... ) ፡ በፀሀይ እና በመድሀኒት ለሚመጣ ጥቁረት (solar lentigines : drug-induced pigmentation...)
በተጨማሪም በብጉር የሚመጣ ጠባሳ እና ካለ እድሜ በፀሀይ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ መሸብሸብን ያጠፋል ፡፡

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) ምልክቶችየዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ምልክቶች ከፈንጣጣ (small pox) ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም የበሽታው ምልክቶች በተወሰነ  ቀለል ያለ ነው።.በዝንጀሮ ፈንጣ...
31/05/2022

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) ምልክቶች
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ምልክቶች ከፈንጣጣ (small pox) ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም የበሽታው ምልክቶች በተወሰነ ቀለል ያለ ነው።.
በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ አንድ ሰው ከተያዘ በኋላ ፡ የበሽታው ምልክቶች ለመታየት ከ7-14 ቀናት ይወስዳል።
ታካሚው መጀመሪያ የሚታይባቸው ምልክቶች፡• ትኩሳት፡ ራስ ምታት፡የጡንቻ ህመም ፡የጀርባ ህመም ፡ድካም ፡ብርድ ብርድ ማለት እና የንፍፊት መቆጣት (lymphadenopathy) ነው።
ትኩሳት ከተከሰተ፡በአማካኝ ከ1 እስከ 3 ቀናት በኋላ ፤ በፊት፡በእጅ መዳፎች ፡በእግር መርገጫ ፡ አፍ ፡ዓይን ላይ ሽፍታ ይታያል ።
ሽፍታው መጀመሪያ ቀላ ቀላ ያለ መልክ መቀየር፤ከዛም ከፍ ከፍ ብሎ የሚታይ ሽፍታ፤ቀጥሎም ውሀ መቐጠር እና ነጣ ያለ ፋሳሽ የቐጠረ ሽፍታ ያስከትላል።
ከ 2- 4 ሳምንታት በኋላ ሽፍታው ደርቆ ይረግፋል።
በከፋ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ሊመጡ የሚችሉ ህመሞች መሀል
• የሳንባ ምች (bronchopneumonia)
• አጠቃላይ የሰውነት (የደም) በሽታ
• የአንጎል እና የዓይን በሽታ ለሞት ሊዳርጉ ይችላሉ።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ገዳይ ነው?
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከተያዘ አስር ሰው መሀል በአንዱ ላይ ሞት ያስከትላል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መያዞን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
የህክምና ታሪክ (የጉዞ ታሪክ, የዝንጀሮ ፈንጣጣ ካላቸው ሰዎች ጋር መኖር፤በሽታው ባለበት እንስሳት ንክሻ ወይም ጭረት ካጋጠሞ ፡በበሽታው የተያዘ በከፊል የበሰለ ወይም ጥሬ ስጋ ከበሉ ወ።ዘ።ተ)
• የቤተሙከራ ፍተሻዎች ፡ከቆዳ ቁስለት በሚወሰድ የዘረምል ምርመራ(PCR)
• የስነደዌ ምርመራ፡ ትንሽ ከቆዳ ላይ ተቆርጦ በሚወሰድ ምርመራ።
ቫይረሱ በደም ውስጥ ለአጭር ጊዜ ብቻ ስለሚቆይ ፤በሽታው መኖሩን ለማወቅ የደም ምርመራ ብዙውን ጊዜ ተመራጭ አይደለም።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ እንዴት ነው የሚታከመው?
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአሁኑ ጊዜ ምንም ህክምና የለውም። ይሁን እንጂ, ከላይ እንደተጠቀሰው 90% ሰው ከበሽታው በራሱ ይድናል።
የበሽታውን መስፋፋት እና ክፋት ለመቆጣጠር ከሚረዱ መድሀኒቶች መካከል፡
• የፈንጣጣ ክትባት
• የፈንጣጣ በሽታ የሚከላከል ፕሮቲን (VIG) እና ፀረ-ቫይረስ መድሃኒቶች አሉ።
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መረጃ ፤ የፈንጣጣ ክትባት በአማካይ 85 በመቶ የዝንጀሮ ፈንጣጣን የመከላከል አቅም ኣለው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው?የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በሚባል ቫይረስ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መንስኤው ምንድን ነው?የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypo...
31/05/2022

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው?
የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በሚባል ቫይረስ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መንስኤው ምንድን ነው?
የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በሚባል ቫይረስ አማካኝነት ይከሰታል። ቫይረሱ ፈንጣጠጣን ከሚያመጣው ቫይረሶች ቤተሰብ ነው።
ሳይንቲስቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ቫይረሱን ያገኙት፡በ1966 ዓም ለምርምር ተብሎ በተያዙ ሁለት ዝንጀሮዎች ላይ ስለነበረ ፤ የዝንጀሮ ፈንጣጣ (monkeypox) ብለው ሰይመውታል።
በሽታው ለመጀምሪያ ጊዜ በሰው ላይ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ በ 1978 ዓም ተገኝቶል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ የት ይገኛል?
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ በተለይም ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ አፍሪካ ሞቃታማ, የገጠር ክፍሎች ውስጥ ይገኛል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ መተላለፊያ መንገድ፡
ከእንስሳት ወደ ሰው እና ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፍ ይችላል።
በሽታው ከያዘው ሰው ወይም እንስሳ ደም፡ የሰውነት ፈሳሽ ፡ የቆዳ ወይም የአፍ ቁስል ፡ የመተንፈሻ ጠብታዎች ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ወይም ከታማሚ ልብስ ጋር በሚፈጠር ንክኪ ይተላለፋል።

የአራስ ሕፃናት ቆዳ እንክብካቤቆዳ ፡ ትልቁ የሰውነት አካል ሲሆን ፣ ከውጪ ጎጂ ነገሮች መከላከልን ጨምሮ  የሰውነት ሙቀት መቆጣጠር ፣ በሽታ መከላከል እና የመሳሰሉት ተግባር አለው።አንድ ህ...
06/03/2022

የአራስ ሕፃናት ቆዳ እንክብካቤ

ቆዳ ፡ ትልቁ የሰውነት አካል ሲሆን ፣ ከውጪ ጎጂ ነገሮች መከላከልን ጨምሮ የሰውነት ሙቀት መቆጣጠር ፣ በሽታ መከላከል እና የመሳሰሉት ተግባር አለው።

አንድ ህፃን እንደተወለደ ቬርኒክስ ካሴኦሳ (Vernix caseosa - ውሃ (80.5%) እና ፕሮቲኖች, ወዝ እና ፀረ-ተሕዋስያን ስብጥር ) በተባለው ንጥረ ነገር የተሸፈነ ቢሆንም ፡ በማህፀን ውስጥ ከነበረው ሞቃት እና የውሃ ከባቢ በፍጥነት ውጭ ወዳለው ቀዝቃዛ እና ደረቅ ከባቢ መጋለጥ አዲስ የተወለደውን ህፃን ቆዳ ለብዙ አሉታዊ ግብረመልሶች ተጋላጭ ያደርገዋል።

ስለዚህ የቆዳ መጎዳትን ለመከላከል፣ በበሽታ አምጪ ተህዋሲያን ላለመጠቃትእና የውስጥ አካላት ድርቀትን ለመከላከል ፤ አጠቃላይ የአራስ ህፃናት የቆዳ እንክብካቤ ስርዓት ያስፈልጋል።

የመጀመሪያ እጥበት

• የዓለም ጤና ድርጅት የመጀመሪያው እጥበት ከተወለደ በዃላ እስከ 24 ሰዓት ድረስ እንዲዘገይ ይመክራል (ሆኖም በተለያየ ምክንያት ማጠብ ግድ ከሆነ ከተወለደ 6 ሰዓት ሳይሞላ መሆን የለበትም)
• በተቻለ መጠን ቫርኒክስ ካሴኦሳን ለማፅዳት / ለማስለቀቅ አይሞክሩ (የሕፃኑ ቆዳ በደም ወይም በሜኮኒየም የተበከለ ከሆነ በእርጥብ ጨርቅ በጥንቃቄ ማጽዳት ይሞክሩ)

• በኤች አይ ቪ ከተያዘች እናት ለተወለዱ አራስ ሕፃናት, የመጀመሪያው መታጠቢያ በተቻለ ፍጥነት መደረግ አለበት
• መታጠቢያው ሁል ጊዜ ሙቅ በሆነ ክፍል ውስጥ ፤ ሙቀቱ ከ 370 ሴ እስከ 37.50 ሴ በሆነ ውሀ ቢሆን ይመረጣል

• ገላውን ከታጠበ በኋላ ህፃኑ ከጭንቅላቱ እስከ እግሩ በደረቅ ሙቅ በሆነ ፎጣ መድረቅ አለበት
• ከታጠበ በኋላ ከእናቱ ጋር የቆዳ-ቆዳ ንክኪን ጨምሮ ተገቢውን የመልሶ ማሞቅ እርምጃዎችን ይጠቀሙ

• መዳህ እስኪጀምሩ ድረስ በሳምንት ከሁለት ጊዜ ማጠብ በቂ ነው
• የመታጠቢያው ቆይታ ከ5-10 ደቂቃዎች መብለጥ የለበትም

• መደበኛ እጥበት እምብርት ከመውደቁ በፊት ሊጀመር ይችላል
• ምሽት ላይ ማጠብ ህፃኑን ለማረጋጋት እና እንቅልፍን ለማሻሻል ይረዳል

• የሕፃን ሳሙናዎችን ይጠቀሙ፣የፀረ ተውሳክ /ባክቲሪያ ሳሙና መጠቀም አይመከርም

የድያፐር (ሽንት ጨርቅ) የሚደረግበት ቦታ እንክብካቤ

• የድያፐር (ሽንት ጨርቅ) ቦታ በተለየ ሁኔታ የእርጥበት መጨመር እና ከሚያስቆጣ ነገር ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ንክኪ ስለሚኖረው፡ ለቆዳ መቆጣት ተጋላጭ ያደርገዋል። ስለዚህ የዳይፐር ቦታ ሁል ጊዜ ንጹህና ደረቅ መሆን አለበት
• ድያፐር (ሽንት ጨርቅ) በቶሎ ቶሎ መቀየር (አንድ ወር ላልሞላቸው ሕፃናት በየ 2 ሰዓቱ፥ 1 ወር ለበለጣቸው በየ 3-4 ሰዓቱ)

• የሚጣሉ የድያፐር (ሽንት ጨርቅ) መጠቀም
• በተቻለ መጠን ድያፐር ሚደረግበት ቦታን ክፍት መተው እና ለአየር ማጋለጥ ፤ዲያፐር ከማድረግ በፊት ቫዝሊን አከባቢውን መቀባት እንደ መከላከያ ሆኖ ያገለግላል.

• በዲያፐር ለውጦች መካከል ፤ተቀብተው የነበሩ መከላከያ ቅባቶችን ማስወገድ አስፈላጊ አይደለም
• የጆሮ ማፅጃ ወይም ለስላሳ የሚጣሉ ፎጣዎች በሞቀ ውሃ በመንከር ማጽዳት

• ሰገራ ወይም ሽንት በሚወገድበት ጊዜ ወይም በሚደርቅበት ጊዜ ፎጣ / ጨርቅ ቆዳ ላይ መፈተግ የለበትም.

የእምብርት አከባቢ እንክብካቤ

• የእምብርት አከባቢን በውሃ (ከቆሸሸ በውሃ እና ህፃነት ሳሙና ) ያፅዱ። የአልኮል መጥረጊያዎችን አይጠቀሙ
• የድያፐር (ሽንት ጨርቅ) ከእምብርቱ በታች ማጠፍ

• በተቻለ መጠን ቦታው ደረቅ ሆኖ እንዲቆይ ያድርጉ (ለየት ያለ መሸፈኛ ወይንም ቅባት አያስፈልግም)

የራስ ቅል እጥበት

• አዲስ በተወለደ ሕፃን ውስጥ የመጀመሪያው የፀጉር እጥበት ፡ እትብቱ ከወደቀ በኋላ ሊሰጥ ይችላል.
• ፀጉርን በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ማጠብ በቂ ነው

የጥፍር እንክብካቤ ፡ ጥፍር በአጭሩ መቁረጥ

Baby powder አጠቃቀም : በአራስ ሕፃናት እና በጨቅላ ሕፃናት ላይ መደበኛ baby powder መጠቀም አይመከርም። በጣም አስፈላጊ ከሆነ ፤ እናት በእጆቹ ላይ በማሻሸት በስሱ መቀባት

ህፃናትን ስለማሸት

• ማሸት የሰውነትን የደም ዝውውርን ከማነቃቃት በተጨማሪ ፤ መረጋጋት እና የመዝናናት ስሜትን ይፈጥራል
• በሚታሽበት ጊዜ ዝግ ያለ እና ለስላሳ መሆን አለበት

• የሙቀት ሽፍታ ካለበት፡ በበጋ ወቅት የቅባት ማሸት አይገባም
• በቅባት ማሸት ፡ በበጋው ወቅት ገላ ከማጠብ በፊት እና በክረምት ወቅት ገላውን ከታጠበ በኋላ መስጠት ይመከራል

• ህፃናትን ፀሀይ ላይ ወይም ፀሀይ ላይ ከማውጣት በፊት በቅባት ማሸት አይመከረም

11. ብጉርዎን የመነካካት / የማፍረጥ ልማድብጉር ካለዎት፡ ብዙውን ጊዜ በፀጉር መውጫ ግርግዳ የተገደበ ነው።ብጉርን መነካካት እና ማፍረጥ፡ ከፀጉር መውጫ ግርግዳ ወደ ታችኝው የቆዳ ክፍል እ...
16/01/2022

11. ብጉርዎን የመነካካት / የማፍረጥ ልማድ

ብጉር ካለዎት፡ ብዙውን ጊዜ በፀጉር መውጫ ግርግዳ የተገደበ ነው።ብጉርን መነካካት እና ማፍረጥ፡ ከፀጉር መውጫ ግርግዳ ወደ ታችኝው የቆዳ ክፍል እንዲፈርጥ በማድረግ ጠባሳ እነዲፈጠር፣ እንዲያመረቅዝ እና የበለጠ ብጉር እነዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።

12. ከመጠን በላይ የቆዳ መላስለሻ ቅባት መጠቀም ወይም በቂ አለመጠቀም
ከመጠን በላይ የቆዳ መላስለሻ ቅባት መጠቀም ፡ቆዳና በጣም ወዛም እና ሽፍታ እንዲያወጣ ሲያደርግ, በቂ አለመጠቀም ደግሞ ደረቅ እና የገረጣ ፊት እነዲኖሮት ያደርጋል።

13. የቆዳ አይነትዎን አለማወቅ እና የቆዳ እንክብካቤ ምርቶችን በጥበብ አለመምረጥ
የቆዳዎ አይነት ምን እንደሆነ ይወቁ እና ተስማሚ የሆኑ ምርቶችን ይጠቀሙ። የቆዳዎን አይነት ካላወቁ ፡ከ https://www.prokerala.com/health/beauty/skin-type-test.php ላይ መጠይቅ በመሙላት ማወቅ እና የቆዳ እነክብካቤ ምርቶችን መምረጥ ተገቢ ነው።

14. በየቀኑ የፀሐይ መከላከያ አለመጠቀም
UV ጨረር እስከ 90% ያለጊዜው ለሚመጣ የቆዳ እርጅና ምክንያት ነው። ስለሆነም ሁል ጊዜ SPF 30 እና በላይ የሆነ ፀሀይ መከላከያ ይጠቀሙ።

Popping your pimples

Squeezing pimples can feel really satisfying, but can actually do more harm to your skin than good.
If you have a pimple, it's usually walled off inside the hair follicle or other pores, so it's like it's locked into that location, popping it can make it rupture under the skin. And this can create scarring, infection, and even more acne in some cases if you improperly pop your pimples.

Moisturizing Too Much or Not Enough

Too much moisture can make skin greasy and broken out, while too little can leave it dry and dull

Not Knowing your Skin Type and Choosing Skincare Products Wisely

Figure out what your skin type is and use products that suit it. If you don’t know how, take the test here. https://www.prokerala.com/health/beauty/skin-type-test.php

Not Using Sunscreen Daily

UV rays are to blame for up to 90% of premature aging. Those wrinkles you blame on genetics? Nah. Playing with your friends outdoors without sunscreen gave you those.

6. ከተገቢው በላይ scrub መጠቀምከመጠን በላይ scrub መጠቀም፡ በቆዳው ላይ ጥቃቅን ቁስለቶችን ሊያስከትል እና የቆዳውን መደበኛ የመከላከል አቅም ሊጎዳ ይችላል።በብዘት scrub መጠቀም...
16/01/2022

6. ከተገቢው በላይ scrub መጠቀም
ከመጠን በላይ scrub መጠቀም፡ በቆዳው ላይ ጥቃቅን ቁስለቶችን ሊያስከትል እና የቆዳውን መደበኛ የመከላከል አቅም ሊጎዳ ይችላል።
በብዘት scrub መጠቀም ለቆዳ ድርቀት እና ጉዳት እንደሚያጋልጥ ሁሉ፡ ጭራሽ አለመጠቀም ደግሞ በጣም የፈዘዘ ቆዳ እና የተደፈነ ቆዳ ቀዳዳ እነዲኖሮት ያደርጋል። ስለዚህ በሳምንት ውስጥ ጥቂት ጊዜ ብቻ scrub እንዲጠቀሙ ይመከራል።

7. ለእንቅልፍ እና አመጋገቦ ትኩረት አለመስጠት
የትኛውም የቆዳ እንክብካቤ ምርቶች ፡ መጥፎ አመጋገብን ወይም እንቅልፍ እጦትን እና የተሳሳተ የአኗኗር ዘይቤን ማካካስ አይችሉም።
ያስታውሱ ፤ ቆዳዎ ፡ የሚመገቡት ምግብ፡ የሆርሞኖችዎ መለዋወጥ እና የአኗኗር ዘይቤዎ ነጸብራቅ ነው።ስለዚህም ጤናማ የምግብ ስረአት መከተል እና ሁል ጊዜ በቂ እረፍት ማግኘቶን እርገጠኛ ይሁኑ።

8. የማህበራዊ ሚዲያ ምክሮችን ሁሉ መተግበር
አብዛኛው የቆዳ እንክብካቤ ምርቶችን በተመለከተ የሚጫኑ መልክቶች ፡ ዋና አላማቸው ምርቱን ማስተዋወቅ እና ገበያ ማግኘት ነው። መርሳት የሌለቦት ምርቱን የተጠቀሙ ተብለው የሚያዩአቸው ምስሎች ፡ እርሶን ለማሳመን የተለያዩ የፎቶግራፍ ቴክኖሎጂን እና Photoshop በመጠቀም የተሰሩ መሆኑን ነው። ስለሆነም፡ የትኛውንም ምርት እራሶ ላይ ከመሞከሮ በፊት፡ ስለምረቱ በቂ መረጃ እነዳሎ እርግጠኛ ይሁኑ።

9. ፊትዎን መነካካት
ፊትን መነካካት ብዙዎቻችን ልምድ የሆነብንና ለመተው የተቸገርንበት ልምድ ሊሆን ይችላል።ሆኖም መርሳት የሌለቦት ፡ፊቶን በእጆችዎ በሚነኩበት ጊዜ፡በአይን የማይታዩ ብዙ ባክቴሪያዎችን፡ ቆሻሻ እና ቅባት ወደ ፊትዎ ያሰራጫል ። ይህም ለሽፍታ እና ለተዘጉ የቆዳ ቀዳዳዎች መፈጠር መንስኤ ይሆናል።

10. በላብ እና እርጥበት የራሱ ልብሶችን ቶሎ አለመቀየር
በላብ እና እርጥበት የራሱ ልብሶች ፡ አቧራ እና ቆሻሻን ሊይዙ ስለሚችሉ ፡ የቆዳ ቀዳዳዎትን በመዝጋት ለሽፍታ እና ለሰውነት ጠረን መፈጠር ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።

Over exfoliating with harsh scrubs

Exfoliating can cause tiny tears in the skin and can impair the skin's normal skin barrier.
Another common mistake is over-exfoliating and over-cleansing the skin, both of which can damage the skin barrier: cause tiny tears in the skin.
To prevent this, it’s recommended to avoid aggressive scrubbing while cleansing, using gentle moisturizers (oil-free types for acne-prone skin) and choosing alcohol-free, hydrating toners.
Never exfoliating can leave you with dull, clogged skin that is more prone to acne and dryness, so it’s recommended exfoliating few times in a week.
Remember: a red, tight, flaky complexion is a sure sign you're overdoing it and need to back off.

Not Prioritizing Sleep and Nutrition

Topical skincare products can't compensate for a bad diet or sleep-deprived lifestyle.Remember than your skin is a reflection of what you eat, your sleeping habits and the fluctuations of your hormones.

Falling for Social Media Tips and Tricks

It is always important to not always trust social media that is loaded with skincare tips and tricks. Some of these tips and tricks are made to promote products that are advertised as a miracle cure to your skincare problem. However, miracle cures don’t exist, and a lot of Photoshop are done to make you believe them. Just remember that everyone has unique skincare needs and goals, and not all products that worked for a certain person will work for you.

Touching your Face too much

Touching your face is something that most of us are guilty of, that once it becomes a habit, it is a struggle to leave behind. Plus, touching your face is a big no-no, your hands contain a lot of bacteria that are not visible in the eye, and touching your face can spread dirt, oil, and bacteria from your hands to your face. Which are the cause of breakouts and clogged pores.

Keeping Sweaty and Wet Clothes On

It’s important to change immediately and not let that sweaty and wet clothing on your body for too long. Because wet and sweaty clothing can trap dust and dirt, that will clog your pores which will often lead to breakout and body odor.

የተለመዱ የቆዳ እንክብካቤ ስህተቶችብዙ የቆዳ እንክብካቤ ስህተቶች የሚመጡት: ተገቢው መረጃ/ መመሪያ ሳይኖራቸው ቆዳቸውን ለማከም ከሚሞክሩ ሰዎች ነው።  ስለዚህ  እራስዎን : ዙሪያዎ ካለ ጎ...
16/01/2022

የተለመዱ የቆዳ እንክብካቤ ስህተቶች

ብዙ የቆዳ እንክብካቤ ስህተቶች የሚመጡት: ተገቢው መረጃ/ መመሪያ ሳይኖራቸው ቆዳቸውን ለማከም ከሚሞክሩ ሰዎች ነው። ስለዚህ እራስዎን : ዙሪያዎ ካለ ጎጂ ከባቢ መጠበቅ እና ለቆዳ እንክብካቤ የሚገዟቸውን ምርቶች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ በተለይም እድሜዎ እየገፋ ሲሄድ አስፈላጊ ነው።
በመደበኛ የቆዳ ህክምና ማዕከላት ውስጥ በብዛት ከሚያጋጥሙ ስህተቶች በጥቂቱ፡

1. ከመጠን በላይ የቆዳ እንክብካቤ ምርቶችን መጠቀም

በገበያ ላይ በብዘት ከሚገኙ የቆዳ እንክብካቤ ምርቶች መሀል ፤ ለእርሶ የሚስማማውን ለይቶ መግዛት ፈታኝ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን ጥራት ከብዛት ይልቅ አስፈላጊ መሆኑን ያስታውሱ። እንደ ባለሙያዎች ፥በጣም የተመጠነ እና አስፈላጊ የሆነውን ያህል ብቻ የቆዳ እንክብካቤ ምርቶችን መጠቀም፡ ለቆዳዎ ጤና ወሳኝ ነው።

2. ከመተኛቶ በፊት ፊትዎን አለመታጠብ
ከአድካሚ የስራ ውሎ ሲገቡ፡ማድረግ የሚፈልጉት አልጋ ላይ መውደቅ ብቻ ሊሆን ይችላል።
ሆኖም ቀኑን ሙሉ ለብናኝ ቆሻሻ እነደመጋለጦ እና ቀን ላይ የተጠቀሙት የቆዳ እንክብካቤ ምርቶች እነደመኖራቸው ፡የቆዳን ቀዳዳ በመድፈን ፣ የቆዳ መቆጣት፡ ድርቀት፡ እነደሁም ሽፍታ እንከዲከሰት ሊያደርጉ ይችላሉ፣ በተጨማሪም በመደበኛነት የሚጠቀሙት የቆዳ እነክብካቤ ምርቶች ስራቸውን እንዳይሰሩ ይከላከላለሉ።
ስለሆነም በመደበኛነት በቀን ሁለት ጊዜ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካደረጉ በኋላ በቐሚነት ፊቶን መታጠብ ተገቢ ነው።
3. የቆዳ ህክምና ባለሙያን ለማማከር ጊዜ መውሰድ / መዘግየት
ብዙ ጊዜ ታካሚዎች ፡የወጣባው ብጉር ጠባሳ እስኪፈጥር - ወይም ደግሞ መጠነኛ የቆዳ ላይ እባጭን ፤እድገቱ ካንሰር እስኪሆን ዘግይተው ለማማከር ወደ ጤና ተቐም የመሄድ ልምድ አላቸው።
ሆኖም “ሳይቃጠል በቅጠል’ እንዲሉ ፡በቶሎ ማማከር ችግሮን በቶሎ ለመቅረፍ ወሳኝ ነው።

4. አንገትዎን ችላ ማለት
ለፊት ቆዳ እንክብካቤ የሚጠቀⶁቸውን ምርቶች ከመንጋጋ መስመር ላይ አያቁሙ! ከስር ያለውን ቦታ ችላ ማለት ፡ ለፀሀይ መጎዳት እና ያለእድሜ ለሚመጡ የእርጅና ምልክቶች ያገልጦታል።

5. በመዋቢያ ምርቶች ላይ የተጠቀሰውን SPF ያህል የፀሐይ ጥበቃ እንደሚያገኙ ማመን
የመዋቢያ ምርቶችን ሲጠቀሙ፡የተጠቀሰውን SPF ቁጥር ልክ የፀሐይ መከላከያ ብቃት እያገኙ ነው ማለት አይደለም። የመዋቢያ ምርትዎ ላይ የተጠቀውን ያክል የፀሀይ መከላከያ ብቃት ለማግኘት ከመደበኛው የመዋቢያ መጠን ከ5-10 እጥፍ መጠቀም ያስፈልግዎታል። በተጨማሪም፣ ለቀጣይ የጸሀይ ጥበቃ ያንኑ ያህል ከባድ ሜካፕ በየሁለት ሰዓቱ እንደገና መደረብ ያስፈልግዎታል።
ሁልጊዜ ከመዋቢያዎ በፊት ትክክለኛውን የፀሐይ መከላከያ ፡ ቢያንስ 30 SPF ያለው ፡ መጠቀሞን አይርሱ።

Common skincare mistakes

Many skincare mistakes come from people trying to treat their skin without proper guidance. Thus it’s important to be mindful and considerate of your skin care routine, the products you buy and how you’re protecting yourself from the environment, especially as you age.
Here are few of the common mistakes noticed in routine dermatology consultations:

Doing too much

It can be tempting to buy an array of skincare products to treat your skincare concerns, but remember that as for every item out there; quality is more important than quantity. Less is more, your routine doesn't need to be complicated. Your skin (and wallet) will thank you later!!

Not washing your face before bed

When you're really tired, it's tempting to skip washing your face when all you want to do is fall into bed.

Cleansing your skin is important! We are exposed to so much dirt and pollution, and by the end of the day, we need to wash off the makeup, debris, and environmental pollutants that are sitting on our skin. Its always recommend cleansing twice daily and after sweating/exercise.
When that debris is left on the skin surface, it can lead to clogged pores, breakouts and dehydration, and also prevents other products in your routine from doing their job. Proper nighttime cleansing alone can dramatically improve your skin!

Waiting too long to see a dermatologist

Too often, patients wait until their acne has left scars or a cosmetic concern has worsened to now require more aggressive treatment—or more seriously when a growth has become cancerous.

Ignoring your neck

Don’t stop your product application at the jawline—keep the love going! Your facial skincare game may be on point, but ignoring the area directly below it, can be an absolute giveaway to sun damage or signs of aging.

Believing that SPF in makeup products count as sun protection

When makeup products list an SPF, this does not mean you are getting that level of sun protection. In fact, you would need to use 5-10 times the normal amount of makeup to get the level of SPF your makeup product claims to have. Furthermore, you would need to reapply that same amount of heavy makeup every two hours for continued sun protection.
Always remember to use a real sunscreen with at least an SPF of 30 prior to makeup.

Psychodermatologyበዐይን በማይታዩ ተህዋሳት እንደተወረሩ የተሳሳተ እምነት ያለው ሰው አጋጥሞት ያውቃል? የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች ቀደም ባሉት ጊዜያት በቆዳው ላይ የሚታዩትን አካላዊ...
26/12/2021

Psychodermatology

በዐይን በማይታዩ ተህዋሳት እንደተወረሩ የተሳሳተ እምነት ያለው ሰው አጋጥሞት ያውቃል?

የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች ቀደም ባሉት ጊዜያት በቆዳው ላይ የሚታዩትን አካላዊ መግለጫዎች ብቻ የሚያክሙ የነበረ ቢሆንም፣ ከጊዜ በኋላ አእምሯችን ለቆዳ ጤንነታችን የሚጫወተውን ሚና የሚመረምር የቆዳ ህክምና መስክ ተፈጥሩአል።

ሳይኮደርማቶሎጂ፡- በ‹አእምሮ› እና በቆዳው መካከል ያለውን ግንኙነት ወይም የቆዳ በሽታዎችን ሥነ-ልቦናዊ ተፅኖን የሚመመረምር ህክምና ሲሆን- አካላዊ ምልክቶችን በቀላሉ ማከም የችግሩን ምንጭ ማከም ላይሆን እንደሚችል እና የስነ-ልቦና ባለሞያን ማማከር ለዘለቄታው የተሳካ ሕክምና ለመስጠት አስፈላጊ የሚሆንባቸው ህመሞች ላይ ያተኩራል።

ለምሳሌ:
• ቐሚ የቆዳ ሕመምተኞች መሀከል; ከ30% እስከ 40% የሚሆኑት የአእምሮ ሕመም ያጋጥማቸዋል።
• ከ psoriasis ታካሚዎች መሀከል ፤44% የሚሆኑት ጭንቀት ህመማቸው ከመባባሱ በፊት እነደነበራቸው ሪፖርት ተደርጓል, አንዲሁም በተደጋጋሚ psoriasis ህመማቸው ከሚቀሰቅስባቸው መሀከል እስከ 80% የሚሆኑት ጭንቀት ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ይታመናል።
• የቆዳ ሕመም ባለባቸው ሕመምተኞች መካከል ያለው የአእምሮ ሕመም መስፋፋት የአንጎል ችግር ካለባቸው፣ ካንሰር እና የልብ ጉዳዮች ጋር ሲጣመር ይበልጣል።

ሳይኮደርማቶሎጂካል መዛባቶች በአራት ምድቦች ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡- ሳይኮፊዚዮሎጂካል መዛባቶች፣ የመጀመሪያ ደረጃ የአእምሮ ሕመሞች፣ ሁለተኛ ደረጃ የአእምሮ ሕመሞች እና የቆዳ ስሜታዊ ሕመሞች ናቸው።

1) ሳይኮፊዚዮሎጂካል መዛባቶች (Psychophysiological disorders) ፡ በስሜታዊ ውጥረቶች የሚባባሱ እውነተኛ የቆዳ በሽታዎች ናቸው። ምሳሌ ፡atopic dermatitis (አለርጂ), ብጉር ፥ psoriasis ወዘተ

2) የመጀመሪያ ደረጃ የአእምሮ ሕመሞች (Primary psychiatric disorders): በሌላ በኩል, እውነተኛ የቆዳ በሽታ ባይኖራቸውም ከባድ የስነ-አእምሮ ህመም አላቸው.
ምሳሌዎች፡ Delusion of Prasitosis - ሰውነታቸው በአንድ ዓይነት ፍጡር የተወረረ ነው ብለው በጽኑ ያምናሉ ፥
እንዲሁም Trichotillomania - አንድ ሰው ምንም አይነት የፀጉር ወይም የቆዳ ችግር ሳይኖርበት የራሱን ፀጉር የሚነቅልበት ህመም አይነት ነው።

3) ሁለተኛ ደረጃ የአዕምሮ ህመሞች (secondary psychiatric disorders): እውነተኛ የቆዳ ህመም: ስነልቦና ላይ የሚየደርሰውን ተፅእኖ Yተነትናል።ለምሳሌ፤ ለምፅ፥ ብጉር፥ላሽ እና የመሳሰሉት በታካሚው ስሜታዊ ጤንነት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ህመሞች ናቸው

4) የቆዳ የስሜት መቃወስ (Cutaneous sensory disorders) ፡- ያለ ምንም ግልጽ መንስኤ ደስ የማይል የመነካከስ፣ የማቃጠል እና የማሳከክ ስሜት ይመለከታል

የሳይኮደርማቶሎጂ አገልግሎት የቆዳ ችግር ላለባቸው ሰዎች ድጋፍ እና ህክምና ይሰጣል። ሕክምናው እንደህመሙ የተለያየ ሆኖ፤ ሰዎች አዳዲስ የአስተሳሰብ መንገዶችን እንዲማሩ ይረዳል, እንዲሁም እንደ ጭንቀት እና ድብርት የመሳሰሉ የስነ-ልቦና ምልክቶችን ይቀንሳል።

ለሚከተሉት ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይችላል-
• ስለ መልክ እና ውበት ያላቸው እምነት
• በውጥረት እና በቆዳ መታወክ መካከል ያለው ግንኙነት
• የቆዳ ችግርን መቋቋም
• ልማዶች (ለምሳሌ ማሳከክ፥ፀጉር መጎተት)
• በራስ መተማመን
• የማህበራዊ ግንኙነት ችሎታዎች
• የስነልቦና ጭንቀት (ለምሳሌ ጭንቀት፣ ድብርት)

What causes itching?Itching is a symptom of many health conditions. Some common causes are: •Allergic reactions to food,...
12/12/2021

What causes itching?
Itching is a symptom of many health conditions. Some common causes are:
•Allergic reactions to food, insect bites, pollen, and medicines
•Skin conditions such as eczema, psoriasis, and dry skin
•Irritating chemicals, cosmetics, and other substances
•Parasites such as pinworms, scabies, head and body lice
•Pregnancy
•Liver, kidney, or thyroid diseases
•cancers
What are the treatments for itching?
Most itching is not serious. To feel better, you could try:
•Keep your hands busy. To avoid continuous itching, it’s important to occupy your hands, so you’re not unconsciously scratching
•Avoid “itch triggers.”
•Cool off. A wet compress or cold shower can ease the itching.
•Take care of your skin. Dry skin will make itching worse. Don’t take long, hot showers or baths. Use a gentle cleanser/soaps, and stay away from perfumed products.
•Apply moisturizer to soothe your itchy skin.
•Try over-the-counter hydrocortisone cream or antihistamines, or lotion containing menthol…like calamine lotion
•Avoid wearing irritating fabrics, and exposure to high heat and humidity
Are you getting itchy yet?
If you are, it’s because, like yawning, itching can be contagious.
Reports of contagious itching where watching others scratch can cause a person to feel an itch are widespread. Indeed, a recent study showed that visual and auditory scratch-related stimuli during a lecture caused a significant increase in scratching behavior in the audience.
And they say: The nicest place to scratch is your ankle.
If you’re not getting relief, or your itching is getting worse, it might be time to see your doctor.
Tips for When You Itch
If you can’t take it and you simply must scratch, try not to use your fingernails. Instead, rub, pat, tap, or tightly hold the itchy area. You can also gently pinch your skin.
“Happiness,” said Ogden Nash, “is having a scratch for every itch”.

Address

In Front Of Logital Hotel
Hawassa
NONE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Girum Telederma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category