
23/09/2025
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ የክልል ጤና ቢሮ የድጋፍ ቡድን በወረዳዎች ድጋፍ አድርጎ አጠቃላይ ግብረ መልስ ተሰጠ።
*******13/1/2018*********
ቡድኑን የመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ምትክል ኃላፊ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል በዞኑ ውስጥ በሌሞ ሶሮና ምዕ/ሶሮ ወረዳ ላይ እስከ ጤና ኬላ ድጋፋዊ ክትትል መደረጉን አውስተው ዛሬ በምቀርበው ግብረ መልስ መነሻ ተጨማሪ ተቋማትን ማየት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመቀጠልም የክልሉ ጤና ቢሮ እናቶችና ህፃናት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሌጅሶ ከጤና ኬላ እስከ ጤና ጽ/ቤት ድረስ የታዩትን ደካማና ጠንካራ ጎኖችን በሥፋት ለመምሪያ ማናጅመንት አቅርበዋል።
በቀረበው ግብረ መልስ መነሻ ከቤቱ ሰፊ ሀሳብ ተነስቶ በቀጣይ ክትትል በሚደረግበት ሂደት ላይ በመግባባት ለይ ተደርሷል።
በመጨረሻም የመምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ደሣለኝ ሹጉጤ ድጋፉ በዓመቱ ጅማሮ ላይ እንደመሆናችን ለቀጣይ ሥራችን ጠቃሚ ነው ብለው በጥንካሬ የተለዩትን ለማስፋትና በድክመት የተለዩትን ደግሞ ለማረም መሰል ድጋፎች እንደምደረግ አንስተው የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።