14/08/2021
Anxiety disorders (የፍርሃት እና ጭንቀት ህመም)
አልፎ አልፎ ፍርሃት እና ጭንቀት ማጋጠሙ የተለመደ የሕይወት ክፍል ነው። ሆኖም ግን ከፍተኛ ፍርሃት እና ጭንቀት ህመም ያለባቸው ሰዎች ስለእለት ተዕለት ኑሮ ከመጠን በላይ እና በማያቋርጥ ሁኔታ ይጨነቃሉ።
ብዙውን ጊዜ ፣ የድንገተኛ ፍርሃት እና ድንጋጤ ህመም (panic attack) : ድንገተኛና በደቂቃዎች ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርስ የመሸበር ስሜት ነው።
እነዚህ የጭንቀት እና የፍርሃት ስሜቶች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ችግር ይፈጥራሉ ፣ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ይሆናሉ ፣ ከሚያጋጥመን ከለት በእለት ችግር ጋር የማይመጣጠኑ እና ለረጅም ጊዜ ሊቆዩ የሚችሉ ናቸው።
ምልክቶቹ በልጅነት ወይም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሊጀምሩ እና እስከ ጉልምስና ሊቀጥሉ ይችላሉ።
የተለመዱ የድንገተኛ ፍርሃት እና ድንጋጤ ህመም ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ።
~ ሊቆጣጠሩት የሚያስቸግር እና እረፍት የሌለው መረበሽ ወይም ውጥረት ሰሜት
~ ትልቅ አደጋ ሊመጣብኝ ነው የሚል ሀሳብ እና ጭንቀት
~ የልብ ምት መጨመር
~ በፍጥነት መተንፈስ (hyperventilation)
~ ላብ ማላብ፣ መንቀጥቀጥ
~ ምንም ሳይሰሩ ድካም ወይም የመዛል ስሜት
~ አሁን ከሚሰማን ጭንቀት ውጭ ስለማንኛውም ነገር ማተኮር ወይም ማሰብ አለመቻል
~ የእንቅልፍ ችግር
~ የጨጓራ ህመም
መቼ ሐኪም ማማከር ያስፈልጎታል?
• ፍርሃቶና ጭንቀቶ ከፍተኛ እንደሆነ ከተሰማዎት እና በስራዎ ፣ ማህበራዊ ግንኙነቶችዎ ወይም በሌሎች የሕይወትዎ ክፍሎች ላይ ተፅዕኖ ካስከተለ
• ፍርሃትዎ ወይም ጭንቀትዎ እርስዎን የሚረብሽ እና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ከሆነብዎት
• አልኮል ወይም ከአደንዛዥ ዕፅ ለመጠቀም የሚያስገድድዎት ከሆነ
• የራስን ሕይወት የማጥፋት ሀሳቦች ከመጡብዎት፣
አስቸኳይ ህክምና ያስፈልጎታል።