Jinka General Hospital Prosperity Unity

Jinka General Hospital Prosperity Unity Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jinka General Hospital Prosperity Unity, Hospital, Jinka.

የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የጠቅላላ ሀኪሚ(GP)ባለሙያዎችን ከዝህ በታች በተጠቀሰው ፈሰፈረት መሠረት አዉዳድሮ ለመቀጠረ ይፈለጋል ስለሆነም  መሠፈረቱን የሚታሟሉ እንደትመዘገቡ   ይሁን ።
22/12/2025

የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የጠቅላላ ሀኪሚ(GP)ባለሙያዎችን ከዝህ በታች በተጠቀሰው ፈሰፈረት መሠረት አዉዳድሮ ለመቀጠረ ይፈለጋል ስለሆነም መሠፈረቱን የሚታሟሉ እንደትመዘገቡ ይሁን ።

19/12/2025

የመንግሥት ሰራተኞች እና ጡረተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የጤና መድኅን ስርዓት ለመተግበር …

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግሥት ሰራተኞች እና ጡረተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማህበራዊ ጤና መድኅን ስርዓት ለመተግበር እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ጤና መድኀን አገልግሎት።

የኢትዮጵያ ጤና መድኀን አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ያምሮት አንዱዓለም ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ በ2017 ዓ.ም ከ13 ነጥብ 67 ሚሊየን በላይ ቤተሰብ በማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን ተመዝግቦ አገልግሎት እያገኘ ነው።

የህብረተሰቡ የጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው፤ በየዓመቱ ለአገልግሎት የሚመዘገቡ አባላት ወቅቱን ጠብቀው አባልነታቸውን እያደሱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በዚህም የአባላት እድሳት ምጣኔ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን አመልክተዋል።

የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን ደመወዝተኛ እና የጡረታ አበል የሌላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያካትት እንደሆነ አንስተው፤ በንግድ፣ በግብርና እና ሌሎች መስኮች ቋሚ ገቢ ሳይኖራቸው የሚተዳደሩትን የሚመለከት መሆኑን ገልጸዋል።

የጤና መድኅን ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለበት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ አስረድተዋል።

በመሆኑም የመንግሥት ሰራተኞች እና ጡረተኞችን የሚመለከተውን የማሕበራዊ ጤና መድኅን አገልግሎት ለማስጀመር እየተሰራ ነው ብለዋል።

በህክምና ሥራ ላይ ለተሰማሩ ዜጎች የመጀመሪያው የሙከራ ትግበራ እንደሚጀመር ጠቁመዋል።

በሄኖክ በቀለ

ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ:- https://youtu.be/a8uRKtDl3_k?si=WUkugQCuKDZ0r258

02/12/2025
23/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 14/ 2018
Marburg Virus Disease Daily update
Ethiopia
November 23/ 2025

21/11/2025
21/11/2025
ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች በቀረበው መስፈርት መሠረት ጠቅላላ  ሀኪም አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ። ስለሆነም መሠፈረቱን የሚታሟሉ እንደተመዘገቡ እንጋብዛለን...
19/11/2025

ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ
የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች በቀረበው መስፈርት መሠረት ጠቅላላ ሀኪም አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ። ስለሆነም መሠፈረቱን የሚታሟሉ እንደተመዘገቡ እንጋብዛለን ።

14/11/2025

የበሽታው መንስኤ መታወቁን ጤና ሚንስቴር አሳወቀ።
#አብክመጤናቢሮ

14/11/2025

ከጤና ሚኒስቴር
ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

13/11/2025

አስቸኳይ ዜና!
በደቡብ ኢትዮጵያ በቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ፈጣን ምላሽ ሰጠ!

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጠረጠረ የቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ ዙሪያ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልላዊ የጤና ባለስልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 8 ሰዎች በቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

WHO ለዚህ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት አስቀድሞ የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦

1. ባለሙያዎች፣ መድኃኒቶችና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዲሁም ለጤና ሰራተኞች የሚሆን የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE) ወደ ተጎዱ ከተሞች ተልኳል።

2. በወረርሽኙ የተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ ንክኪን የመከታተል (Contact Tracing) ሥራን ድርጅቱ ይደግፋል።

3. ሊኖር የሚችለውን ድንበር ዘለል ስርጭት ለመከላከል ከደቡብ ሱዳን WHO ቢሮ ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው።

4. የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ እንዳስታወቁት፣ ለአስቸኳይ ድጋፍ እንዲውል 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) የአሜሪካን ዶላር ከWHO የአደጋ ጊዜ ፈንድ ለኢትዮጵያ ተለቋል። ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ድጋፉን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

የWHO ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ጤና ባለስልጣናት መረጃውን በወቅቱ በማጋራታቸው እና ፈጣን ምላሽ በመስጠታቸው ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት ሙሉ ድጋፍ እንደማይለያቸው ቃል ገብተዋል።

Via WHO

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

12/11/2025

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ

Address

Jinka
954651

Telephone

+251919738384

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jinka General Hospital Prosperity Unity posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category