Bitemal Health Center

Bitemal Health Center Health worker

16/07/2025
12/07/2025
DOCTOR With Africa (CUAM) የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በኣሪ ዞን በባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ በብተማል ጤና ጣብያ በምግብ እጥረት ለተጎዱት ህፃናት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።...
12/07/2025

DOCTOR With Africa (CUAM) የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በኣሪ ዞን በባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ በብተማል ጤና ጣብያ በምግብ እጥረት ለተጎዱት ህፃናት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።

_ሰኔ 30/2017 ዓ.ም
{አርክሻ -ካይሳ}

DOCTOR With Africa (CUAM) የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በምግብ ዕጥረት ለተጎዱ ሕጻናት ማገገሚያ ማዕከል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ
ያደረጉ ።

ለብተማል ጤና ጣቢያ 300,000 ብር በላይ ግምት ያላቸው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለጤና ጣቢያው በአካል በቦታው በመገኘት ርክክብ መደረጉን የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ኢዮብ ዳዊት ገልጸዋል ።

ለተደረገው ድጋፍ የጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ኢዮብ ዳዊት በመመሪያው ስም ምስጋናቸውን አቅረበዋል ።

የባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የእናቶችእና ህፃናት ዳይረክቴር አቶ በላይነህ ዳይናቸው እና የብተማል ጤና ጣብያ ምክትል ዳይረክቴር አቶ ጴጥሮስ አመኑ ለተደረገው ደጋፍ በወረዳውና በጤና ጣብያዉ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

👉 ‼️
👇

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዛሬ 08/09/2017 ዓ.ም  ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት አንድት እናት  # አራት -መንቲያ - ህፃናት በቀ...
16/05/2025

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዛሬ 08/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት አንድት እናት # አራት -መንቲያ - ህፃናት በቀዶ ህክምና በሰላም ተገላገለች።

ወ/ሮ ደስታ ገጵ የጵላ ቀበሌ ኗሪ እናት የሆኑት በሰላም በቀዶ ህክምና መውለዷን የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም ዶ/ር ወንድመነህ ካሳሁን ገለፁ ።

ይህች እናት ከዚህ በፊትም ሁለት መንቲያ ልጆችን እንደወለደች እና አሁንም በድጋሚ 4 መንቲያ ህፃናት ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዘር መጀሪያ ደረጃ ሆስፒታል መውለድ ችላለች ። አሁን ህፃናቶቹ በጥሩ ሁኔታ አስፈላጊውን እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛል ።

መረጃው፦ከጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተወሰደ

የኣሪ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ በቢተማል ጤና ጣቢያ ማቆያ ላሉት እናቶች የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ ።የኣሪ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረ...
28/04/2025

የኣሪ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ በቢተማል ጤና ጣቢያ ማቆያ ላሉት እናቶች የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ ።

የኣሪ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ በቢተማል ጤና ጣቢያ ማቆያ ላሉት እናቶች የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደርጓል።

የዞኑ ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ርብቃ አለማየሁ እና ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ማሚቱ ሰይድ በጤና ጣቢያ ዉስጥ የእናቶችን ማቆያ ጎብኝት በማድረግ ለእናቶችና ህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ ልብሶች ድጋፍ አድርገዋዋል ።

የዞኑ ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ርብቃ አለማየሁ በንግግራቸው የምናደርገው ድጋፍ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል ።

አክለውም ተቋሙ ህብረተሰብን በማስተባበር እየሰጠ ያለው ድጋፍና እንክብካቤ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ስለተደረገልን በጎነት ስራችሁ እጅጉን በጤና ጣቢያው ስም አመሰግናለሁ!!!

ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም

 #በባካ  #ዳውላ ኣሪ ወረዳ   አጠቃላይ የባለሙያዎች ውይይት መድረክ መካሄዱ ተገለጸ።የውይይቱ ዋና አጀንዳዎች1ኛ የደም ልገሳ ፎሮግራም ና ግንዛቤ ማስጨበጥ 2ኛ የአግልግሎት አሰጣጥ ጥራትን...
25/04/2025

#በባካ #ዳውላ ኣሪ ወረዳ አጠቃላይ የባለሙያዎች ውይይት መድረክ መካሄዱ ተገለጸ።
የውይይቱ ዋና አጀንዳዎች
1ኛ የደም ልገሳ ፎሮግራም ና ግንዛቤ ማስጨበጥ
2ኛ የአግልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በተመለከተ
3ኛ ባለሙያዎች ታማሚዎችን በሥነ-ምግባር ተቀብሎ ማገልገልን በተመለከተ
4 ኛ የመንግስት ስራ ሰዓትን በተመለከተ እና ሌሎችም ጨምሮ ስሆን
5ኛ የወባ በሽታ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት እንዳለበት

በመጀመሪያ ስለደም ልገሳ ግንዛቤ ስሆን ግንዛቤውን የሰጡ ከጂንከ ደም ባንክ አገልግሎት ከሚሰጡት ባለሙያ ከሆኑት ስ/ር ማህሌት ታምራት የሰጡ ስሆን ደም መለገስ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉ አስረድተዋል::ደም የምለግስ ሰዉ 83% ከካንሰር በሽታ የመከላከል ዕድል በጣም ከፍተኛ ነዉ:: እና በስተመጨረሻም ከጤና ጣቢያው ጋር ሚያዚያ 29/ 2017 ዓ.ም የደም ልገሳ ፎሮግራም እንደሚያካሂዱ አስረድተዋል::
በውይይቱ ላይ የተነሱ ብዙ ሰፊ በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ስሆን የአግልግሎት አሰጣጥ የምለካው የህበረተሰቡ እርካታና ህብረተሰባችን በመልካም ሥነ-ምግባር ስናገለግል መሆኑ ተገልጿል::
ከዚህ በፍት የነበሩ ችግሮች ከግብዓት አቅርቦት ጋር ተያይዞ ያለው ችግሮች በሰዓት ከመግባት መዉጣት ጋር ያለው የነበረ ስሆን አሁን ግን ይህ ሁሉ ተቀርፎ አሁን ላይ በጤና ተቋማችን በቂ መድሀኒቶች በቂ የላብራቶሪ ምሪመራ እንዳሉ ስሆን አሁን ግን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ምንም ችግር እንደሌሌ ነዉ::
በጤናው ዘርፍ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እና CRC ባለሙያ ማለትም ሩህሩህ አገልጋይ ተንከባካቢ ባለሙያ በሥነ-ምግባር የታነፄ ለሁሉም ዜጋ አግልግሎት መስጠት እንዳለብንም ጤና ጣቢያዉ አጥብቆ ገልጿል።
በስተመጨረሻም ስለወባ በሽታ ግንዛቤ መስጠት ለህብረተሰቡ ስሆን ዝናቡን ተከትሎ የሚመጣ ግዛዊ ዉሃ ያቆሩ የወባ መራቢያ ቦታዎችን በማፋሰስ ; ቋሚ የሆኑ የወባ መራቢያ ቦታዎች ላይ ኪሚካሎችን በመርጨት እና ሁሉም ህብረተሰብ አጎበር በስነስርዓቱ ሰቅለው እንድጠቀሙ ማድረግ ነዉ ሚጠበቅብን!!!

!!!!

ሚያዝያ 17/8/2017 ዓ/ም

በኣሪ ዞን ባካ ዳውላ አሪ ወረዳ ቢቴማል ጤና ጣቢያ ከመደበኛ ሥራዉ ጎን ለጎን የጓሮ አትክልቶችን  የሽንኩርት ተከላ  ሥራዎችም እየተሠሩ ይገኛሉ***                ሜያዚያ 16/20...
24/04/2025

በኣሪ ዞን ባካ ዳውላ አሪ ወረዳ ቢቴማል ጤና ጣቢያ ከመደበኛ ሥራዉ ጎን ለጎን የጓሮ አትክልቶችን የሽንኩርት ተከላ ሥራዎችም እየተሠሩ ይገኛሉ
***
ሜያዚያ 16/2017 ዓ.ም
አርክሻ -ካይሳ

በቀን 16/8/2017 ዓ.ም የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ቢቴማል ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ የበልግ ወቅት ዝናብን በመጠቀም ከመደበኛዉ ሥራ ጎን ለጎን የጓሮ አትክልቶችን የሽንኩርት ተከላ ሥራን አከናዉነዋል።

ቀን 16/1/2017ዓ.ም በአሪ ዞን በባካ ዳዉላ አሪ  ወረዳ በዛሬው እለት በብተማል ጤና ጣብያ  በዓሉን በማስመለከት ከባካ ዳውላ አሪ ወረዳ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጽ/ቤት የመጡት እንግዳዎች...
26/09/2024

ቀን 16/1/2017ዓ.ም
በአሪ ዞን በባካ ዳዉላ አሪ ወረዳ በዛሬው እለት በብተማል ጤና ጣብያ በዓሉን በማስመለከት ከባካ ዳውላ አሪ ወረዳ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጽ/ቤት የመጡት እንግዳዎች እንኳን አደረሳችሁ በማለት ብተማል ጤና ማቆያ ላሉትለነፍስ ጡር እናቶች 10 ኪሎ ስኳር ስጦታ አበርክቷል ።

//የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና //

እንድሁም የአሊ ቀበሌ የሴቶችና ህፃናት ምትክል ሰብሳቢ በዛሬው ቀን ለእናቶች ቀለብ መግጃ የሚሆን 3000 ብር ስጦታ አበርክቷል::

26/09/2024

Address

Baka Dawula
Jinka

Telephone

+251991851425

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bitemal Health Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share