Leku General Hospital

Leku General Hospital Leku General Hospital is Government owned health organization located in sidama regional state , northern sidama zone it far from hawassa city in 26 km.

Leku General Hospital shared an inspiring quality improvement journey, which was published on ISQua–AfCOP!👏 Well done, L...
13/09/2025

Leku General Hospital shared an inspiring quality improvement journey, which was published on ISQua–AfCOP!

👏 Well done, LGH Team for your commitment on advancing quality care in Ethiopia and beyond!




We carry the spirit of the New Year through better care!
11/09/2025

We carry the spirit of the New Year through better care!

በሲዳማ ክልል  የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በሆስፒታሉ የተጀመሩ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ፣የአቅመ ደሞችን ቤት ማደስ፣ የጤና ም...
15/08/2025

በሲዳማ ክልል የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በሆስፒታሉ የተጀመሩ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ፣የአቅመ ደሞችን ቤት ማደስ፣ የጤና ምርመራና ትምህርት አገልግሎት ፣የደም ልገሳ ፣ የችግኝ ተከላ መርሃ -ግብሮች በዛሬው ውሎ

በሲዳማ ክልል  የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማዘመን እየሰራ ነውየለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማዘመን፣ተመራጭና ተወዳዳሪ የልዕቀት ማዕከ...
15/08/2025

በሲዳማ ክልል የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማዘመን እየሰራ ነው

የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማዘመን፣ተመራጭና ተወዳዳሪ የልዕቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ፡ ሆስፒታሉ እያካሄደ ባለው ዓመታዊ የማህበረሰብ እና የሠራተኞች ፎረም ላይ ተገልጿል ።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪና የሆስፒታሉ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ባጥሶ ዌዲሶ በመልዕክታቸው ፦ሆስፒታሉ ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ጭምር ተወዳዳሪና ብቁ እንዲሆን ለማድረግ፡ የተከናወኑ ተግባራት በጋራ ርብርብ ውጤታማ መሆናቸውን አስረድተዋል ።

ሆስፒታሉ ለተገልጋይ የሚሰጠውን አገልግሎት በማሻሻል፣ በዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከወረቀት ንኪኪ የጸዳ ማድረግ መቻሉ ፤ የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን የተገልጋዩን እንግት በመቀነስ እርካታን ከፍ ለማድረግ ያስቻለ መሆኑም ተብራርቷል ።

በዚሁ ወቅት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ እንደተናገሩት ፦ ሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ በማሻሻል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ለተከታታይ ሶስት ዙር በፌዴራል ደረጃ በመሸለም፤ ያከናወናቸው ተግባራት በዓርአያነት ይጠቀሳል ብለዋል።

ከፎረሙ ጎን ለጎን "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በሆስፒታሉ የተጀመሩ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ፣የአቅመ ደሞችን ቤት ማደስ፣ የጤና ምርመራና ትምህርት አገልግሎት ፣የደም ልገሳ ፣ የችግኝ ተከላ መርሃ -ግብሮች ተከናውነዋል ።

ከዚህ ፕሮግራም በተጨማሪ ከየኬዚ ቲሙ እና ዲፓርትመንቱ የዓመቱ ግንባር ቀደም ፈፃሚዎች ፣ በሀገር ሀቀፍ ደረጃ ሆስፒታሉን ላስጠሩ ፣ልዩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ እና ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የዕውቅና ፣ሰርተፍኬት ሜዳልያና የዋንጫ ሽልማት የመስጠት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።




28/05/2025

የኤም ፖክስ በሽታን በጋራ እንከላከል

14/05/2025






ዛሬ ጤና ሚኒስቴር እና አጋር ድርጅቶች ልዑካን ቡድን ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታልን  ጎብኝተዋል።ጉብኝቱም በዋናነት የእናቶች፤ ህፃናት እና የአፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት አሰጣጥ መነሻ ያደረገ ሲ...
07/05/2025

ዛሬ ጤና ሚኒስቴር እና አጋር ድርጅቶች ልዑካን ቡድን ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱም በዋናነት የእናቶች፤ ህፃናት እና የአፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት አሰጣጥ መነሻ ያደረገ ሲሆን የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ዮቴ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው፣ በሆስፒታሉም ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በተጨማሪም በሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ሆስፒታሉ በእናቶች ህጻናት እና አፍላ ወጣቶች ላይ እየሰራ ያለውን ስራ በሰፊው ቀርቦ፤ ጥምረት ለጥራት በሚል መርህ ቃል ከሆስፒታልም አልፎ ሌሎች ጤና ተቋማት ላይ እናቶች ህጻናት ጤና ላይ እየተሰራ ያለው መልካም ስራ ለቡድኑ በሰፊው ቀርቦዋል። በተጨማሪም ሆስፒታሉ የተለያዪ ምርጥ ተሞክሮችንና የአገልግሎት ጥራት ማሻሽያ ፕሮጀክቶች ኢግዝብዥን አቅርቧል። በመቀጠልም ልዑካን ቡድኑ የሆስፒታል መስክ መልከታ ካደረጉ በኋላ በሥራ ላይ የታዩ መልካም ተሞክሮ በማድነቅ ለሆስፒታሉ ማህበረሰብ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በስተመጨረሻም መልካም ተግባሮች መቀጠል እንዳለባቸው አንስተው መስተካከል የሚገባቸው አካባቢ ገንቢ የሆነ አስተያየት ሰጥተው፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም እንዲሁም አጋር ድርጅቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አንስተዋል።
ከጎብኝዎቹም
1.Sr. Zemezem Mohammed – Maternal Health Desk Head, Ministry of Health
2. Mr. Jemal Kassa – Country Director, Engender Health
3. Dr. Hailemariam Segni – President, Ethiopian Society of Obstetricians and Gynecologists (ESOG)
4. Mr. Abebe Kebede – Executive Director, Consortium of Reproductive Health Associations (CORHA)
5. Ms. Abigel Endale – Program Coordinator, Youth Network for Sustainable Development (YNSD)
እንድሁም ከተለያዩ ክልሎች እና አጋር ድርጅቶች የተወጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፍዎች ይገኙበታል።
29-08-2017 ዓ.ም
ለኩ

#ለኩአጠቃላይሆስፒታል




ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ !
20/04/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ !

ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል የ2017 ዓ.ም 3ተኛ ሩብ ዓመት  የቦርድ ስብሰባ አካሂደዋል።ሚያዝያ /9/2017/ዓ.ም/      ለኩ የሆስፒታሉ  አመራር የቦርድ አባላት የተቋሙን የዘጠኝ ወር ዕቅድ...
18/04/2025

ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል የ2017 ዓ.ም 3ተኛ ሩብ ዓመት የቦርድ ስብሰባ አካሂደዋል።
ሚያዝያ /9/2017/ዓ.ም/
ለኩ

የሆስፒታሉ አመራር የቦርድ አባላት የተቋሙን የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ገመገሙ፣
በወቅቱም የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሰፍ ዮቴ የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የሆስፒታሉን አጠቃላይ አፈፃፀም ሪፖርት እና ቀጣይ ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል።

ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ የተቀናጀና የተሳለጠ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን ህብረተሰብ እንዲሁም አገልግሎት ሰጭውን ባለሙያ ፍላጎት ለማርካት በበጀት አመቱ መጀመሪያ የታቀዱ ስራዎች አተገባበር ምን ይመስላል የሚለው በስፋት ተዳሷል።

በዋናነት የእናቶችና ህጻናት ህክምና አገልግሎት ፣ ድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ፣ ተኝቶ ህክምና አገልግሎት ተመላላሽ ህክምና አገልግሎት እንዲሁም የመድኃኒት አስተዳደር ስርዓት ምን ይመስላል የሚለው በስፋት ተዳሷል።

በመድረኩም የተገኙ የሆስፒታሉ ሥራ አመራር ቦርድ በሆስፒታሉ እየተሰራ ያለው መልካም ተሞክሮዎች በተለይ አገልግሎት አሰጣጥ ከማዘመን ጋር የተያያዘው Digital Health care ከሀገራችን አልፎ ለአፍሪካም መልካም ተሞክሮ የሚወሰድ መልካም ተግባር ነው በማለት አንስተዋል። ይህ ከዘመኑ ጋር የዘመነው አገልግሎት አሠጣጥ ለማህበረሰቡ ቀልጣፋና የተሳለጠ አገልግሎት ከመስጠት ረገድ የታካሚዎችን እንግልት እንደምቀንስም ከመድረኩ በሰፊው ተብራርቷል።

በወቅቱም የተገኙ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና በጉድለት የተለዩ ችግሮችን በተለይ በጥምረት ለምንሠራው የሆስፒታሎችና ለሎች ጤና ተቋማት ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ተሽከርካሪ ማጣት ፣ በሆስፒታሉ ከጥበት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለመፍታት እየተገነባ ያለውን G+3 ህንጻ ቶሎ ለማጠናቀቅ ችግሮችን ለቅሞ ለመፍታትና የእርምት እርምጃዎችን ለመውሰድ ያለመ ውይይት መሆኑም ተመላክቷል።

የክልሉ ፕረዝደንት ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪና የሆስፒታሉ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ባጥሶ ዌድሶ መድረኩን የመሩት ሲሆን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሰፍ ዮቴ፣ ሰሜናዊ ስዳማ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ብሩክ ሰለሞንን ጨምሮ ሌሎች የቦርድ አባላት ተገኝተዋል።

በመጨረሻም የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የቦርድ አባላትን ጊዜና ሁኔታ ሳይገድባቸው ያለምንም መቆራረጥ የሆስፒታሉን ሥራ ስለመገምገማቸው ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል
#ለኩአጠቃላይሆስፒታል




16/04/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Binalfew Mihret, Fasil Fayo, Sami Yegeta Lij, Jebose Nh, Mik Mitsha

LEKU GENERAL HOSPITAL The Medical Mission Team, Wide Horizon, had a highly impactful and memorable week at Leku General ...
16/03/2025

LEKU GENERAL HOSPITAL

The Medical Mission Team, Wide Horizon, had a highly impactful and memorable week at Leku General Hospital, benefiting both the hospital and the local community. They provided valuable capacity-building training in pediatric care, oncology, and mental health to a total of 58 staff members. In addition to the training, the team performed over 30 major surgeries and more than 16 minor surgeries within a short time frame. They also generously gave gifts to both staff and patients, displaying great humility. The hospital and community are deeply grateful for their contributions and the valuable lessons learned from the team.

Day 2.......Leku General Hospital and the surrounding community are benefiting greatly from this mission. The presence o...
12/03/2025

Day 2.......Leku General Hospital and the surrounding community are benefiting greatly from this mission. The presence of such a diverse and skilled team of professionals is an incredible asset. Their combined expertise in pediatrics, microbiology, oncology, surgery, mental health, and gynecologic care is truly comprehensive. It must make a significant impact on both staff training and the quality of care provided to the community. Training and giving precious care is continuing ...

Address

Leku, Sidama
Leku

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Leku General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Leku General Hospital:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram