Kadaba Medium Clinic Logia Afar

Kadaba Medium Clinic Logia Afar Kaddaba Fanti Kilink payllee Dayli Buxxa Kaya Dalli Getintama payalle kussa Eleaban mansafette ke p

11/09/2024
kadabba General Hospital Loading.....
15/01/2024

kadabba General Hospital Loading.....

10/09/2022

HAPPY NEW YEAR , WISH ALL BLESSKNG AND PROSPERITY IN THE COMING NEW YEAR DEAR ETHIOPIANS

25/01/2022

Maysaxxaga
Massakaxxale ni madruurway waak sugneeh mango adda ni madruurah essorook ugut abak
Dr Daniel intih specialist kaxxa'abba kilinikil taama qimbisem rufto luk sin naysixxige!!!

25/01/2022

በክሊንካችን ልዬ አይን ህክምናና ክትትል በአይን እስፔሻሊስት ሀኪም በቅርብ ቀን
ይጀመራል:: ይህ ለአከባቢ ማህበረሰብ መልካም ነገር ነው : ይምጡ : ይመርምሩ !🙏

12/05/2021

EID MUBARAK

Remadan kareem  for my musilim Friends!!
13/04/2021

Remadan kareem for my musilim Friends!!

10/03/2021

መረጃ ለጤናዎ !!

ቋቁቻ( Pityriasis versicolor)
===

ቋቁቻ በፈንገስ የሚመጣ ሲሆን ብዙ ግዜ ወጣቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነዉ።ይህ የ fungus አይነት በሁላችንም ሰዉነት የሚገኝ ሲሆን ለምን አንዳንድ ሰዎች ላይ ብቻ በሽታዉን እንደሚያመጣ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር የለም።

እሱም ገርጣ ገርጣ ወይም ጠቆር ጠቆር በሚሉ የቆዳ ለዉጥ ይታወቃል።
አብዛኛዉን ግዜ ደረትና ጀርባን የሚያጠቃ ሲሆን አልፎ አልፎ ፊት ፣ እጅና እግርን ልያጠቃ ይችላል።

ቋቁቻ ብዙ ግዜ በሞቃታማ የአየር ሁኔታ የሚከሠት ሲሆን የበለጠ ወንዶችን ያጠቃል።
አብዛኛዉን ግዜ ምልክት ባይኖረዉም አንዳንድ ግዜ ግን ልያሳክክ ይችላል። ይሁንና ቋቁቻ ከሰዉ ወደ ሰዉ አይተላለፍም።

ቋቁቻ በብዛት ሊከሰት የሚችል ከሰዉ ወደ ሰዉ የማይተላለፍ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ
ላይ ችግር ነዉ:: ፈንገሱ የቆዳ ተፈጥሮዊ መልክን በማሳጣት ትናንሽ፣ነጣ ወይም ጠቆር ያሉ መልካቸዉን የለወጡ ነገሮች በቆዳ ላይ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡

ሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ፣ወዛማ ቆዳ ካለዎት፣· የሆርሞን መለዋወጥ
የበሽታ መከላከል አቅማችን መዳከም ቋቁቻ እንዲከሰት ወይም የሚያደርጉ ነገሮች ሲሆን
ቋቁቻን በተለያዩ የሚቀቡና የሚዋጡ መዳንቶች ማከም ይቻላል።ሆኖም ግን ሁኔታዎች ሲመቻቹለት የመመላለስ ፀባይ አለው።

ቋቁቻ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ ችግር ስለሆነ የሚከተሉት መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት መድሃኒቶች በቆዳ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ሲሆን ቀሪዎቹ የሚዋጡ ናቸዉ፡፡
1.የፍሉኮናዞል እንክብል ወይም ፈሳሽ መድሃኒት
2. ኢትራኮናዞል( እንክብል፣ካፕሲዩል ወይም ፈሳሽ)
3. ኬቶኮናዞል( ክሬም፣ ጄል ወይም ሻንፖ) ናቸዉ፡፡

ምንም እንኳ ህክምናዉን በደንብ ቢከታተሉትና ህመሙ ቢሻሎትም ለሳምንታት ወይም ለወራት የቆዳዎ ቀለምዎ ሳይለወጥና እንደሻከረ ሊቀጥል ይችላል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ህመሙ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል( በተለይ በሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ወቅት)፡፡ ስለሆነም ኢንፌክሽኑ ተመልሶ እንዳይመጣ መድሃኒት በወር አንዴ ወይም ሁለቴ መዉሰድ ሊስፈልግ ይችላል፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

#

19/11/2020

የነርቭ ዘንግ ክፍተት (Neural Tube Defect)
በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ
በአንዳንድ ጨቅላ ህፃናት ላይ በጀርባቸው ላይ ያበጠ ነገር እንዲሁም የጭንቅላታቸው መጠን በጣም የገዘፈ ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ ይህም የነርቭ ዘንግ ክፍተት (Neural Tube Defect) ይባላል፡፡
ይህ ችግር ከላይኛው የአእምሮ ክፍል እስከ ታችኛው ህብለ ሰረሰር ድረስ የነርቭ ዘንግና መሸፈኛው የአፈጣጠር ችግር ሲኖርበት የሚከሰት ነው፡፡
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ግምት በየአመቱ እስከ 300ሺ በሚደርሱ ህፃናት ላይ ሞትና ጉዳትን የሚያስከትል ችግር ነው፡፡ በሀገራችንም የተከናወኑት ጥቂት ጥናቶች የችግሩን አሳሳቢነት ያመላከቱ ናቸው፡፡
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እ.ኤ.አ. ከ2016-2017 ድረስ ባካሄደው ጥናት በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ ሆስፒታሎች ከተወለዱ 10ሺ ህፃናት መካከል 131ዱ (131/10,000) ጨቅላ ህፃናት ከነርቭ ዘንግ ክፍተት ጋር መወለዳቸውን አስረድቷል፡፡
በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተደረገው ጥናት በአዲስ አበባ ባሉ 3 ሆስፒታሎች ውስጥ ከተወለዱ 10ሺ ህፃናት መካከል 126ቱ (126/10,000) ጨቅላ ህፃናት የነርቭ ዘንግ ክፍተት እንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡
የነርቭ ዘንግ ክፍተት ያለባቸው ህፃናት ተያያዥ የጭንቅላት መጠን በአእምሮ ፈሳሽ መሞላትና መጠኑ መጨመር (hydrocephalus)፣ የእግር አለመንቀሳቀስ መጣመምና ውስጣዊ አካላዊ ችግሮች ሊኖሩባቸው ይችላሉ፡፡

ለነርቭ ዘንግ ክፍተት አጋላጭ የሆኑ ነገሮች
-የፎሊክ አሲድ እጥረት
- እናትየው የምትወስዳቸው መድኃኒቶች የፎሊክ አሲድን የሚፃረሩ ከሆኑ
ለምሳሌ የሚጥል ህመም መድኃኒቶች
- ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ችግር ያለው የወለደች እናት በተከታታይ በዚሁ ችግር የተጠቃ ልጅ የመውለድ እድሏ ከፍተኛ መሆን ከመንስኤዎቹ መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የነርቭ ዘንግ ክፍተት ያለባቸውን ህፃናት ለማከም ከፍተኛ የሆነ ወጪ ይጠይቃል፡፡ በተጨማሪም የብዙ ባለሙያዎችን ርብርብ የሚፈልግና ፈታኝ ሲሆን የህክምና ውጤቱም በአብዛኛው ጥሩ አይደለም፡፡ በመሆኑም በዋነኝነት የእርጉዝ እናት የፎሊክ አሲድ አጠቃቀምን በማስተካከል መከላከል ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡
በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ ምግቦችን ለመውለድ የሚያስችል የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች አብዝተው መመገብ አለባቸው፡፡
እነዚህም በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ ምግቦች አትክልት ፣ፍራፍሬና የእንሰሳት ተዋፅኦ ናቸው፡፡
• ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ብርቱካን
• ቀይስር፣ አበባ ጎመን
• ባቄላ፣አተር
• እንቁላል እና የጉበት ስጋ በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ ናቸው ::

ለማርገዝ ያሰበች እናት ቅድመ እርግዝና ምክክር በማድረግ ከመጀመሪያው የእርግዝና ቀን ጀምሮ ለ3 ወራት የፎሊክ አሲድ እንክብሎችን መውሰድ ይኖርባታል፡፡ በተለይም ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ችግር ያለው ህፃን የወለደች እናት ከፍ ባለ መጠን መውሰድ ይጠበቅባታል፡፡
እንደ ችግሩ አሳሳቢነት በማህበረሰብና በአገር አቀፍ ደረጃ ስለነርቭ ዘንግ ክፍተት ግንዛቤ እና ስለፎሊክ አሲድ ጥቅም ብዙ አልተሰራም፡፡ ይህም የዚህ ችግር ተጠቂዎች ከእለት እለት ከፍ ባለ ቁጥር እንዲታዩ አድርጓል፡፡ በመሆኑም በማህበረሰብ ደረጃ የፎሊክ አሲድ ጥቅምና የነርቭ ዘንግ ክፍተት የመከላከል እውቀት ማስፋፋት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡
picture -wikipedia

"ስለ ቶንሲል የምናውቀው አና የምንሳሳተው ምንድን ነው?" - ዶ/ር ንጉሴ ጫኔ ፤ የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም- ቶንሲል ምንድን ነው?ቶንሲል ለብዙዎቻችን እንደሚመስለን በሽታ አይደለም። ቶንሲል...
30/10/2020

"ስለ ቶንሲል የምናውቀው አና የምንሳሳተው ምንድን ነው?" - ዶ/ር ንጉሴ ጫኔ ፤ የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም
- ቶንሲል ምንድን ነው?
ቶንሲል ለብዙዎቻችን እንደሚመስለን በሽታ አይደለም።
ቶንሲል ማለት ትንንሽ አበጥ ያሉ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ አካላት ስብስብ ነው። ይህም በክብ ቀለበት ከምላስ ጀርባ የላንቃን የጎን ግድግዳ እና የላንቃን ክዳንና የአፍንጫን የውስጠኛ ክፍሎች ያስተሳስራል።
- ቶንሲል ጥቅሙ ምንድን ነው?
በአፍም በአፍንጫም የሚገቡ ተዋህስያንን መዋጋት ነው። የሰውነትን በር ከጠላት መከላከያ ነው።
- ቶንሲል እና እንጥል አንድ ናቸው?
ሁለቱም በላንቃ አካባቢ ይገኛሉ። ግንኙነታቸው ግን ጉርብትና እንጅ በአገልግሎት አይገናኙም።
- Uvula/እንጥል
እንጥል ማለት ከላንቃ ላይ የተንጠለጠለ ማለት ነው። ከቶንሲል ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።
- የቶንሲል ህመም/tonsialiophayngitis?
ይህ የቶንሲል እና የላንቃ አካባቢ በተዋህስያን መወረር ነው።
- የህመም ምልክቶች
ትኩሳት ፣ ለመዋጥ መቸገር ፡ ራስ ምታት ፣ የአፍ መሽተት ፣ የአንገት ንፍፊት እብጠት ፣ ማንኮራፋት ፣ ሳል
የቶንሲል ህመም መተላለፊያ መንገዶች
1. በትንፋሽ ጠብታ
2. በንክኪ
- የባክቴሪያ ቶንሲል በብዛት የሚያጠቃው ማንን ነው?
የባክቴሪያ ቶንሲል ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናትን የሚያጠቃ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከ5-15 እድሜ ያሉት ይጠቃሉ። የቫይረስ ሲሆን ለጋ ህጻናትም ይጠቃሉ።
የቶንሲል ህመም ተያያዥ ችግሮች
1 ፡ መግል መቋጠር tonsiar, peritosilar or retropharyngeal abscess
2. የሳንባ ምች / የማጅራት ገትር
3. የልብ ህመም rheumatic heart disease ይህን ለመከላከል ቶንሲል እንዳመመን ወደ ጤና ተቋም መሄድ።
4. የኩላሊት ህመም PS glomerulonephritis
5. የቶንሲል መፋፋት adenotonsilar huperthrophy
- የቶንሲል ህመም ህክምና
መጀመሪያ የባክቴሪያ ወይስ የቫይረስ ነው የሚለውን መለየት ያስፈልጋል።
መለያ መንገዶች
1. የቫይረስ ከሆነ የጉንፋን ምልክት አብሮ ይኖራል ግን አንዳንድ ጊዜ እንደ ቫይረስ ጀምሮ ወደ ባክቴሪያ ሊቀየር ስለሚችል ጥንቃቄ ይፈልጋል።
2. መግል የያዘ ከሆነ የባክቴሪያ ምልክት ነው ግን ይህን በደንብ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል።
3. ድድ፣ ከንፈር ወይም ምላስ የቆሰሉ ከሆነ የቫይረስ ምልክት ነው።
4. የነጭ የደም ሴል እና ተያያዥ ምርመራ
መድሃኒት
1. የህመም ማስታገሻ
2. እንደ ቶንሲሉ ህመም መነሻ የተለያዩ ጸረ ባክቴሪያ አለበለዚያም ፀረ ቫይረስ መድሃኒት
3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ ረፍት ማድረግ።
4. ማር እና የውሃ ኢንፋሎት መታጠን
5. የብርቱካን ወይም ሎሚ ጭማቂ።
ለተጨማሪ መረጃዎች የሀኪም ዩቱብ ቻናልን ይከታተሉ:

Address

LOGIA AFAR
Logia
±251

Telephone

+251972118857

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kadaba Medium Clinic Logia Afar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram