Robe Donsa Mediumm Clinic

Robe Donsa Mediumm Clinic Robe donsa medium clinic to increase access to primary care services for patients in rural communiti

05/08/2021
01/08/2021
02/06/2021

3. የስኳር ህመም አይነቶች...Cooming soon⌚️

2. የሰኳር ህመም ምልክቶች እና ስሜቶች... የስኳር ህመም ምልክቶችና ስሜቶችበአለማችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች 2ተኛዉ አይነት የስኳር ህመም ( type 2 diabetes) ቢኖርባቸዉም፣ ...
02/06/2021

2. የሰኳር ህመም ምልክቶች እና ስሜቶች... የስኳር ህመም ምልክቶችና ስሜቶች
በአለማችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች 2ተኛዉ አይነት የስኳር ህመም ( type 2 diabetes) ቢኖርባቸዉም፣ ህመሙ እንዳለባቸዉ ሳያዉቁ ይኖራሉ። ይህም ማለት ህመማቸዉ ሳይታወቅላቸዉና ምንም አይነት የህክምና እርዳታ ሳያነኙ ለአንተ ይኖራሉ ማለት ነዉ።
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
ብዙ ሰዎች የስኳር ህመምን ምልክቶችና ስሜቶችን ሳያሳዩ ወይም ምልክቶቹ በጣም አነስተኛ ስለሚሆኑ፣ ትኩረት ሳይሰጣቸዉ ስለሚቀሩ ነዉ። በሌላ ጊዜ ደግሞ፣ የህመሙ ስሜት ቢሰማቸዉም ያን ያህል አስጊ ስለሚመስላቸዉ ወደ ህክምና ሳይሄዱ ይቀራሉ። ስለሆነም ታማሚዎቹ በስኳር ህመም ምክንያት በሚከሰቱ ተያያዥ በሸታዎች፤ ለምሳሌ የአይን እይታ ብዥታ የወጣቶች ጫፈ መደንዘዝ፤ አጋጥሞአቸዉ ወደ ህክምና እስኪሆዱ ድረስ ለስኳር ህመማቸዉ ህክምና ሳያደርጉ ለረዥም አመታት ይቆያሉ።

የስኳር ህመምን በቶሎ ማወቅ በህመሙ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ውስብስብ አካላዊ ጉዳቶችን ለመከላከል ይረዳል። እንደ (National Inistitue of Diabetes and Digestive & Kidney Diseases) ጥናት፤ አርባ አሞስት አመት ከዛ በላይ የሆናቸዉ አዋቂዎች፤ የስኳር ህመም ስሜት ባይሰማቸዉ እንኳን፣ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ከአርባ አምስት አመት በታች የሆኑ ሰዎች ደግሞ፣ የህመሙ ስሜቶች ከተከሰቱባቸው ወይም የስኳር ህመም የመከሰቱ ስጋት ከፍተኛ ከሆነ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

ከቅርብ አመታት ወዲህ ቅድመ የስኳር ህመም (prediabetes) የሚለውን የህክምና ቃል በተደጋጋሚ እንሰማለን። ይህ ቃል አንድ ሰዉ በ2ተኛዉ አይነት የስኳር ህመም (type 2 diabetese) የመያዝ ስጋቱ ከፍተኛ እንደሆነ ለመግለፅ የሚጠቅም ቃል ነዉ። ደግነቱ እንደዚህ ያሉ ሰዎች ፤ የኑሮ ዘይቤአቸዉን፤ ማለትም አመጋገብን ጤናማ በማድረግ፣ ቀለል ያሉ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን በማዘዉተርና ፣ ከመጠን በላይ የሆነ የሰውነት ክብደትን በመቀነስ፣ የስኳር ህመም መከሰቻ ግዜን መዘግየት ይቻላል።

ስለሆነም፥ እርሶም ሆኑ የቤተሰብ አባልዎ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት አንዱ ወይም ከዛ በላይ የህመሙ ስሜቶች የሚሰማዎ ከሆነ ባስቸኳይ ወደ ሀኪም ዘንድ በመሄድ ምርመራ ሊያደርጉ ይገባል

1) ከፍተኛ የሆነ የርሀብ ስሜት
2) ቶሎቶሎ ሽንት መሽናት
3) የማይቋረጥ የሀ ጥማት
4) ተደጋጋሚ የሆነ የሰውነት መዛል ሰሜት
5) የእይታ መዛባት ( ብዥታ)
6) ያልተጠበቀ ፈጣን የሰውነት ክብደት መቀነስ
7) የእጅና የእግር ጣቾች መደንዘዝ
8) በሰዉነት ላይ የሚከሰቱ ቁስሎች በቶሎ አለ መዳን
9) በተደጋጋሚ በተለያዩ በሽታ አምጪ ተዋህስያን መጠቃት

1. የስኳር ህመም ማለት ምንድን ነው?የስኳር ህመም ዘወትር ከምንመገበው ምግብ የምናገኘውን ስኳር ሰውነታችን በአግባቡ ወደ ሀይል እንዳይቀይር የሚያደርግ ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ነው።ጤነኛ ሠዎ...
02/06/2021

1. የስኳር ህመም ማለት ምንድን ነው?

የስኳር ህመም ዘወትር ከምንመገበው ምግብ የምናገኘውን ስኳር ሰውነታችን በአግባቡ ወደ ሀይል እንዳይቀይር የሚያደርግ ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ነው።

ጤነኛ ሠዎች ስኳር ወደ ሴሎች ዘልቀው እንዲገቡና እነደ ሀይል ምንጭነት እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችለው አስፈላጊ የሆነ ኢንሱሊን የተባለው ንጥረ ነገር በጣፊያ ውስጥ ይመረታል።

ከስኳር ህመም ጋር የሚኖሩ ሰዎች አንድም ጣፊያቸው ኢንሱሊንን በበቂ ሁኔታ አያመርትም ወይም ደግሞ ሰውነታቸው የተመረተውን ኢንሱሊን በአገባቡ መጠቀም አይችልም። ይህም ማለት ሰውነታቸው የቀን ተቀን ተግባሩን ለመከወን የሚያስፈልገውን ሀይል አያገኝም ማለት ነዉ ። ስለዚህ የስኳር ህመምን፣ አንድ ሰዉ የሚያስፈልገዉን ሀይል ከሚመገበዉ ምግብ መገኘት አለመቻል ብለን ልንገልፀዉ እንችላለን...

Tajaajila hawwaataa fi qulquulina qabu yoo barbaaddan filannoon kessan Kilinka Keesaan haa ta'u.Labooratorii guutu fi Al...
01/06/2021

Tajaajila hawwaataa fi qulquulina qabu yoo barbaaddan filannoon kessan Kilinka Keesaan haa ta'u.
Labooratorii guutu fi Altiraasawuundii ammaayyaa waliin
Iddoon: Magaala Roobee Ganda Caffee Donsa

ለእርጉዝ ሴቶች ፈፅሞ የተከለከ 10 ምግቦች1. ጉበትቫይታሚን ኤ ህፃኑ በማህፀን ውስጥ ለሚኖረው እድገት አስፈላጊ ነው። ይህን ቫይታሚን እርጉዝ ሴቶች ከፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ሥጋ እና እንቁላል...
26/05/2021

ለእርጉዝ ሴቶች ፈፅሞ የተከለከ 10 ምግቦች
1. ጉበት
ቫይታሚን ኤ ህፃኑ በማህፀን ውስጥ ለሚኖረው እድገት አስፈላጊ ነው። ይህን ቫይታሚን እርጉዝ ሴቶች ከፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ሥጋ እና እንቁላል ያገኙታል። ነገር ግን ከመጠን በላይ የሆነ ቫይታሚን ኤ ለህፃኑ መጥፎ ሲሆን በወሊድ ጊዜ ችግር ያስከትላል።
2. ቡና
ካፌይን ትልቅ ትኩረት የምትሰጭው ጉዳይ ነው። ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና በእርግዝና ወቅት መጠጣት ከማስጨንገፍ/ ማስወረድ ጋር ይያያዛል።
3. በሂደት ያለፈ ሥጋ (Processed Meat)!
በፍጥነት የሚደርስ እና ቀላል ምግብ መመገብ ስናስብ የአብዛኛዎቻችን ምርጫ ሳንድዊች ነው። ነገር ግን እርጉዝ ከሆንሽ ሳንዱዊቹ ከምን ከምን እንደተሰራ በቅርበት መመልከት አለብሽ። ምክንያቱም ሊስቴሪያ (Listeria) ለተባለ ባክቴሪያ ሊኖረው ይችላል የሚል ስጋት ስላለ ነው። ይህ ባክቴሪያ በጣም በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ እድገቱን የሚቀጥል ብቸኛ ባክቴሪያ ነው።
4. ሳላድ
ሳላድ ከትኩስ አትክልትና ፍራፍሬ የሚዘጋጅ ነው። ይህም ቁጥር አንድ ተመራጭ ጤናማ ምግብ ያደርገዋል። ነገር ግን በአትክልት ቤት፣ ጁስ ቤት እና ካፍቴሪያ ውስጥ ሳላድ መመገብሽን አቁሚ ምክንያቱም አትክለቶቹ የሚቀመጡበት የሙቀት ሁኔታ፣ የተዘጋጁበት ሰዓት የምግቦቹን ለጤና ተስማሚነት ስለሚወስን ነው። ስለዚህ በቤትሽ ውስጥ ሰርተሽ መመገቡ ተመራጭ ነው።
5. ጁስ (ፓስቸራይዝድ ያልሆነ)!
ጁስ መጠጣት አትክልቶች እና ፍራፍሬዎችን በምግብ ገበታሽ ውስጥ በቀላሉ የምታካትችበት መንገድ ነው ነገር ግን ሁሉም ጁሶች ለአንቺ ንጽህና ጤናማ አይደሉም። ምክንያቱም ኢሸርሺያ ኮላይ ወይም ሊስቴሪያ (E. coli or Listeria) የተባሉ ባክቴሪያዎችን በውስጣቸው ሊይዙ ስለሚችሉ ነው።
6. በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ሥጋ እና ጥሬ የአሳ ሥጋ!
እርጉዝ በምትሆኝበት ጊዜ ጥሬ ሥጋ እና ጥሬ የአሳ ሥጋን ቻው ብለሽ መሰናበት አለብሽ። ባክቴሪያ እና ሌሎች በሽታ አምጪ ህዋሶች በደንብ ባልበሰለ ወይም በጥሬ ሥጋ ላይ እና በባህር ውስጥ ምግቦች ውስጥ መኖር ስለሚችሉ ነው።
7. በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ እንቁላል!
እንቁላል የፕሮቲን፣ ቫይታሚን እና ሜኔራል መገኛ ምንጭ ነው። ነገር ግን እርጉዝ ከሆንሽ የምትመገቢው እንቁላል በደንብ መብሰሉን ማረጋገጥ አለብሽ። በትክክል ካልበሰለ ግን ሳልሞኔላ (Salmonella) ለተባለ ባክቴሪያ የመጋለጥ ዕድል አለሽ።
8. የወተት ምርቶች (ፓስቸራይዝድ ያልሆኑ)
እርጉዝ ሴት በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ የወተት ምርቶችን ማግኘት አለባት። በውስጣቸውም ካልሲየም፣ ፕሮቲን እና ቫይታሚን ዲ ሲይዙ የሚወለደውን ህፃን ታዳጊ አጥንት፣ ጥርስ፣ ልብ እና ነርቭ በመገንባት ይጠቅማሉ። ነገር ግን ሁሉም የወተት ምርቶች ለአንቺ ምግብነት መልካም አይደሉም ስለዚህ ጥሬ ወተት እና ሌሎች ጥሬ የወተት ምርቶችን መጠቀም የለብሽም።
9. ከፍተኛ ሜርኩሪ ያለው አሳ!
እርጉዝ የሆነች ሴት ከፍተኛ የሆነ ሜርኩሪ ያላቸውን አሳዎች መመገብ ማቆም አለባት። ይህ ኬሚካል በሰውነትሽ ውስጥ የመከማቸት ባህሪ ስላለው የነርቭ ሥርዓትሽን ሊጎዳው ስለሚችል ነው።
10. አልኮል!
ብዙ ኤክስፐርቶች እንደሚስማሙት አንድ እርጉዝ የሆነች በእርግዝናዋ ወቅት የአልኮል መጠጥ መጠጣት የለባትም የዚህም ምክንያት ልጅ ላይ የሚከሰተውን ፌታል አልኮሊክ ሲንድረምን (Fetal Alcohol Syndrome) ለመከላከል ሲባል ነው።
ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።Share share🤩

የጀርባ ህመም መነሻ 10 ምክንያቶችመነሻው ምን እንደሆነ በዉል ሳያዉቁት በጀርባ ህመም ተሰቃይተዋል?የጀርባ ህመም በአደጋ ብቻ ላይከሰት ይችላል የአቀማመጥ ሁኔታ የሚጠቀሙት ጫማ ከመጠን ያለፈ...
26/05/2021

የጀርባ ህመም መነሻ 10 ምክንያቶች
መነሻው ምን እንደሆነ በዉል ሳያዉቁት በጀርባ ህመም ተሰቃይተዋል?
የጀርባ ህመም በአደጋ ብቻ ላይከሰት ይችላል የአቀማመጥ ሁኔታ የሚጠቀሙት ጫማ ከመጠን ያለፈ ዉፍርትና ከባድ ነገሮችን ማንሳት የላይኛዉና ታችኛው ጀርባ ህመም ያስከትላል።
የጀርባ ህመም የሚያስከትሉ መነሻ ምክንያቶችን በዝርዝር እንመልከታቸው፦
1. የቢሮ ወንበር
የቢሮ ወንበርዎ ለጀርባ ህመም ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋሉ ሲቀመጡ ጎበጥ የሚሉ ከሆነ ጀርባዎ ላይ ጫና ያደርጉበታል አከርካሪ ሊጋመንታችን ከአቅም በላይ ይለጠጥና ዲስካችን የጀርባ አጥንታችን እንዲወጠር ያደርጋል ከጊዜ ብዛት የጀርባ አጥንታችንን በመጉዳት ለጀርባ ህመም ይዳርገናል።
2. የሚያደርጉት ጫማ
ጫማ ለጀርባዎ ጤንነት ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል የማይገባ/ትክክል ያልሆነ ጫማ አቋምዎን በማዛባት ማዕከላዊ የግራቪቲ ቦታን ያዛባል ይህም በታችኛው የጀርባ ክፍልዎ ላይ ህመም ይፈጥራል።
3. የሚተኙበት ፍራሽ
የሳሳ (ስስ) ፍራሽ መጠቀም የታችኛዉን የጀርባ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል በተጨማሪም የአከርካሪ አጥንቶችን እንዲዛቡ በማድረግ በጡንቻዎች እና የአከርካሪ መገጣጠሚያዎች ላይ ዉጥረት ይፈጥራል።
4. የጀርባ ቦርሳ
የሚይዙት የጀርባ ቦርሳ ትልቅ ከሆነ ብዙ እቃዎችን የመያዝ እድል ይኖርዎታል ተጨማሪ ሸክም በጀርባዎ ላይ መጫን ትልቁ የጀርና ህመም ምክንያት ነው።
በአንድ በኩል ያለዉ የሰዉነት ክፍልዎ ላይ ሸክም መጨመር የአከርካሪ አጥንቶች እንዲጎብጡ በማድረግ የጀርና ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።
5. በሆድ በኩል መተኛት
በሆድ በኩል ተደፍተዉ ሲተኙ በጀርባዎና በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ይጨምራል በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ጨመሩ ማለት ደግሞ የሙሉ ሰዉነትዎን ቅርጽ ያዛባዋል ጭንቅላትዎን ወደ ጎን ሲያዞሩት ደግሞ ጭንቅላትዎንና አከርካሪዎት ከመደበኛ አቅጣጫዎ ውጪ አደረጉት ማለት ነው።
6. ትከሻ ወይም አንገት ለረጂም ሰዓት አንገትን አዘንብሎ (ደፍቶ) መቆየት ወይም መጓዝ በትከሻዎቻችን መሀል ያሉትን ጡንቻዎች እንዲዝሉ በማድረግ የላይኛው ጀርባ ክፍል እና የአንገት ህመም ያስከትላል።
7. ላኘቶኘና ስማርት ስልኮች
በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎቻቸው ፍቅር ስለወደቁ በነዚህ ሰዎች ላይ የጀርባ ህመም የተለመደ ነው።
በስራ በተጠመድበት ወቅት ስልክዎትን በትከሻዎና በጆሮዎ መሀል በመያዝ ለረጂም ጊዜ ማውራት የአንገት ህመም ያስከትላል።
8. ከመጠን ያለፈ ውፍረት
ከሌሎች በሽታዎች በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለጀርባ፣ መገጣጠሚያ እና ጡንቻዎች ህመም ያጋልጠናል።
አብዛኛዎቹ በሚኖራቸው ውፍረት በዳሌና በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም ያጋጥማቸዋል።
9. እግርን አጣምሮ መቀመጥ
እግርዎን አጣምረው በሚቀመጡበት ጊዜ የአከርካሪ አጥንትዎ ቀጥ ማለት ይሳነዋል ይህም በዳሌ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ከመጠን በላይ እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል።
በተጨማሪም የደም ዝውውር በመስተጓጐሉ ምክንያት ቫሪኮስ ቬይን (Varicose vein) ለተባለ በሽታ ያጋልጣል።
10. ሲጋራ ማጨስ
በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ወደ ዲስክ (Disc) የሚሄደውን የደም ዝውውር በመቀነስ የአከርካሪና ጐን አጥንት ችግር ያስከትላል።
በተጨማሪም ካልሲየም በአግባቡ ከሰውነታችን ጋር እንዳይዋሀድ በማድረግ የአጥንት እድገትን ይገታል በመሆኑም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች በአንድ እጥፍ የጀርባ ህመም ችግር ያጋጥማቸዋል።

ፎሮፎር የሚፈጠርበት ምክንያት፣ህክምናውና ጠቃሚ ምክሮችበጭንቅላታችን ቆዳ ላይ የሚገኙ ሴሎች ተፈጥሮአዊ በሆነ ዑደትበየጊዜው እየሞቱ በአዳዲስ ሴሎች እየተተኩ ይሄዳሉ፡፡ይህ የሴሎች የመተካከት ...
26/05/2021

ፎሮፎር የሚፈጠርበት ምክንያት፣
ህክምናውና ጠቃሚ ምክሮች
በጭንቅላታችን ቆዳ ላይ የሚገኙ ሴሎች ተፈጥሮአዊ በሆነ ዑደት
በየጊዜው እየሞቱ በአዳዲስ ሴሎች እየተተኩ ይሄዳሉ፡፡
ይህ የሴሎች የመተካከት ሂደት በጤነኛና የፎሮፎር ችግር በሌለባቸው ሠዎች ላይ እስከ
1 ወር የሚደርስ ጊዜን ሊወስድ ይችላል በዚህ ጊዜ ውስጥም የሞቱት
ሴሎች ቀስ በቀስ ከቆዳ ላይ እየተወገዱና እየተተኩ ይሄዳሉ፡፡
ነገር ግን
በተለያዩና በእርግጠኛነት ይህ ነው በማይባል ምክንያት አዳዲስ የጭንቅላት ቆዳ ሴሎች በብዛትና በፍጥነት እየተፈጠሩ ይሞታሉ እነዚህ ሴሎች ከትክክለኛው ተፈጥሮአዊ የመተካከያ በጣም ባነሠ ጊዜ ውስጥ
ስለሚፈጠሩና ስለሚሞቱ እየተገፉ ወደ ላይኛው የጭንቅላታችን የቆዳ
ክፍል በብዛት ይወጣሉ በቆዳችን ላይ ባለው ተፈጥሮአዊ ቅባት
ምክንያትም እነዚህ የሞቱ ሴሎች እርስ በእርሳቸው በመጠባበቅ በመጠን እያደጉ ነጫጭ ርጋፊዎችን በመፍጠር በፎሮፎር መልክ ከፀጉራችን ላይ
ይረግፋሉ፡፡
ይህ የሞቱ ሴሎች ከጭንቅላት ላይ የመርገፍ ሂደት በጤነኛና ፎሮፎር በሌለባቸው ሠዎችም ላይ የሚከሠተ ቢሆንም አዲስ የሚፈጠሩና የሚሞቱት ሴሎች መጠን ተመጣጣኝ ስለሆነ ሣይስተዋሉ ከፀጉር ላይ
ይወገዳሉ፡፡
የፎሮፎር ችግር ባለባቸው ሠዎች ላይ የሚስተዋለው በከፍተኛ
መጠን የጭንቅላት የቆዳ ሴሎች መፈጠርና መሞት እንዲከሠት
ከሚያደርጉ ምክንቶች ውስጥ Malassezia (ማላሴዚያ) የተባለው
የፈንገስ አይነት አንዱ እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያሣያሉ ይህ ተዋህሣያን
ጉዳት ሳያስከትል በጭንቅላታችን ቆዳ ላይ የሚኖር ሲሆን በተለያዩ
ምክንያቶች ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ በመራባትና ተፈጥሮአዊውን
የቆዳችንን ቅባት በማብላላት የሚፈጥረው ኬሚካል ቆዳችን እንዲቆጣና
የተለያዩ ለውጦች እንዲከሠቱ በማድረግ ከላይ ያየነውን ያልተመጣጠነነና
ጊዜውን ያልጠበቀ የሴሎች መተካካት እንዲኖርና ፎሮፎር እንዲፈጠር
ምክንያት ይሆናል፡፡
ፎሮፎር በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሠት ችግር ቢሆንም በበለጠ
መልኩ ግን ወጣቶችና ጐልማሶች ለችግሩ ተጋላጮች ናቸው የተለያዩ
ጥናቶች ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በፎሮፎር እንደሚጠቁ አሣይተዋል፡፡
ፎሮፎር እንዲባባስ
የሚያደርጉ ምክንያቶች
ፎሮፎር ከላይ ባየነው መልኩ መፈጠር ከጀመረ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች
አማካኝነት እየተባባሠ ሊሄድ ይችላል ከእነዚህም ውስጥ
በተለያዩ የፀጉር መንከባከብያ ምርቶች ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ
ኬሚካሎች በተለይም በጄሎች፣ እስኘሬዎች፣ ሻምፖዎችና ቅባቶች ውስጥ
የሚገኙ ኬሚካሎች ከቆዳችን አይነት ጋር ላይስማሙ ስለሚችሉ
አለርጂኮችን ይፈጥራሉ በዚህም ምክንያት የጭንቅላት ቆዳ ላይ መቅላት፣
መቁሠልና ማሣከክ የመሣሠሉት ሁኔታዎች ይኖራሉ ይህም ፎሮፎርን
ለማባባስ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይታወቃል በመሆኑም እነዚህን
ምርቶች ስንጠቀም እንደቆዳችን አይነት የሚስማማንን በአግባቡ መርጠን
መሆን ይኖርበታል
በተፈጥሮ የጭንቅላታችን ቆዳ በጣም ደረቃማ ወይም ቅባታማ
መሆን ችግሩን እንደሚያባብሠው የተለያየ ጥናቶች ያሣያሉ በመሆኑም
እነዚህን የቆዳ ችግሮች ለመቆጣጠር የቆዳ ህክምና ባለሙያ በማማከር
አስፈላጊውን ምክርና ህክምና ማግኘቱ የፎሮፎር ችግር እንዳይባባስ
ይረዳል፡፡
ከአየር ንብረት ጋር ተያይዞ ቀዝቃዛማ አየር ችግሩን ሊያባብሠው
ይችላል በተለይም በዚህ የአየር ንብረት ወቅት ፀጉርን አጅለው የሚሸፍኑ
ከፍያዎችና ስካርፎችን መጠቀም የችግሩን መጠን ከፍ እንደሚያደርገው
ጥናቶች ያሣያሉ፡፡
ከቀዝቃዛ አየር በተጨማሪም ከፍተኛ ሙቀትም
የችግሩን መባባስ ያስከትላል፡፡
የተለያዩ ከቆዳ ጋር ተያይዘው የሚከሠቱ ህመሞች በተለይም
seborrheic dermatitis (ሴቦሪክ ዳርማታይቲስ)፣ Eczema
(ኤክዚማ)፣ Psoriasis(ሶሪያሲስ) የመሣሠሉት ፎሮፎርን ያባብሣሉ
ከነርቭ ጋር ተያይዘው የሚከሠቱ ህመሞች እንዲሁም
ፖርኪንሠኒዝም (parkinsonism) ያለባቸው ሠዎች ከሌላው በተለየ
መልኩ ለችግሩ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው በተጨማሪም
የሠውነትን በሽታ የመከላከል አቅም (Immunity) የሚጐዱ ህመሞች
ያሉባቸው ሠዎችም ችግሩ ሊባባስባቸውና ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡
ደካማና ተከታታይነት የሌለው የፀጉር ንፅህና አጠባበቅ ለፎሮፎር
መባባስ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው፡፡
በየጊዜው በሚስማሙን
የፀጉር ንፅህና መጠበቂያዎች አማካኝነት ፀጉራችንን መታጠብና ማፅዳት
ይኖርብናል በተለይም ከፍተኛ ላብን ከሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች በኋላ
በአግባቡ የፀጉርን ንፅህና መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
አመጋገብ፡- በቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ (Vitamin B complex)
እና ዚንክ የበለፀጉ ምግቦችን አዘውትሮ አለመመገብ ችግሩን ሊያባብሠው
ይችላል በአንፃሩ ስኳርን አብዝቶ መጠቀም ደግሞ ፎሮፎርን ለመቆጣጠር
አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር የተለያዩ ጥናቶች አሣይተዋል፡፡
ጭንቀት፡- ጭንቀት በጤናችን ላይ የተለያዩ ችግሮች እንዲከሠቱ
የሚያደርግ መሆኑ ይታወቃል ከዚህም ጋር ተያይዘው በሚከሠቱ የተለያዩ
ኬሚካላዊ ለውጦች ምክንያት ፎሮፎርን እንዲባባስ የማድረግ አቅም
አለው፡፡
ፎሮፎርን ለመቆጣጠር
የሚያስችሉ መንገዶች
የፎሮፎር ችግርን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም በተለያዩ መንገዶች
በደንብ መቆጣጠር ይቻላል የመጀመሪያው መንገድ የፀጉርን ንፅህና
በአግባቡ መጠበቅ ሲሆን ከፀጉራችን አይነት ጋር ተስማሚ የሆኑ
መታጠቢያ ሳሙናዎችና ሻምፖዎችን አንዲሁም የፀጉር ቅባቶችን
በመምረጥ መጠቀም ይኖርብናል ወዛም ቆዳና ቅባትማ ፀጉር ያላቸው
ሠዎች ደረቃማ ቆዳ ካላቸው ሠዎች የተለየ የፀጉር ንፅህና
መጠበቂያዎችን መጠቀም ያለባቸው ሲሆን ለፀጉሬ አይነት የትኛው
ይስማማኛል የሚለውን ለመምረጥ በምርቶቹ ላይ የሚጻፈውን ማብራሪያ
በደንብ ማንበብና መረዳት ይኖርብናል ይህን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ
ባለሙያዎችን ጠይቆ መረዳትና መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
ተጨማሪ
መዋቢያዎችን ለፀጉራችን የምንጠቀም ከሆነ ለተወሠነ ጊዜ ማቆምና
ለውጡን ማየት ይኖርብናል በተጨማሪም የሚከተሉት ነጥቦች ተጨማሪ
የመቆጣጠሪያ መንገድን ሊፈጥሩልን ይችላሉ።
• የምንወስደውን የዚንክ (Zinc) መጠን ከፍ ማድረግ፡- ዚንክ ለፎሮፎር
ምክንያት የሆነውን ፈንገስ ለማጥፋት ከማስቻሉም ባሻገር የጭንቅላታችን
ቆዳ የሚያመነጨው ቅባት ተመጣጣኝ እንዲሆን በማድረግ ፎሮፎርን
ይቆጣጠራል፡፡
ዚንክን ከአሣ፣ የስብ መጠኑ ትንሽ ከሆነ ስጋ፣ ከስንዴ፣
ከለውዝ፣ ከዱባፍሬ፣ እንዲሁም ከአጃ ልናገኘው እንችላለን
• በቫይታሚን ቢ ኮምኘሌክስ (vitaminB complex) የበለፀጉ ምግቦችን
አዘውትሮ መጠቀም ፎሮፎርን ለመቆጣጠር እንደሚያስችል የተያዩ
ጥናቶች ያሣያሉ
ወተትና የወተት ተዋጽኦዎች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ጥራጥሬዎች
እንዲሁም አሣ፣ ጉበት ጥሩ ምንጮች በመሆናቸው በአመጋገባችን ውስጥ
አካተን
መጠቀም ይኖርብናል በተጨማሪም በአሣ ውስጥ የሚገኘው ኦሜጋ 3
(Omega 3) የተባለው ጠቃሚ የቅባት አይነትም ተጨማሪ የመከላከል
ጥቅምን
ያጐናጽፋል
• የምንጠቀመውን የስኳር መጠን መቀነስ ፡-ከፍተኛ መጠን ያለው ስኳር
መጠቀም የተለያዩ የፈንገስ አይነቶች እንዲራቡ ምቹ ሁኔታን ሊፈጥር
ስለሚችል ብሎም ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮችን ስለሚያስከትል
በመጠን መጠቀሙ ይመከራል
• ጭንቀትን ማስወገድ፡- የተለያዩ የስነልቦናና የጤና ባለሙያዎችን
በማማከር የጭንቀት ምንጮችን ለማስወገድ መሞከር ይኖርብናል ይህንን
ማድረጉ በብዙ ሠዎች ላይ ፎሮፎርን በአግባቡ ለመቆጣጠር ማስቻሉ
ይታወቃል፡፡
• ፀጉርን በኮፍያና በሻሽ ወይም በተለያዩ ነገሮች ጥብቅ አድርጐ መሸፈን
ፎሮፎር እንዲባባስ ያደርጋል ፀጉራችን በቂ የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኝና
እንዲናፈስ ማድረግ የበለጠ ጠቀሜታ አለው፡፡
ለተለያዩ የፀጉር እንክብካቤ
የምንጠቀምባቸው ምርቶች በውስጣቸው አልኮል የማይዙ ቢሆን
ተመራጭ ነው ምክንያቱም አልኮል የጭንቅላት ቆዳ እንዲደርቅና ችግሩ
እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል፡፡
• በፎሮፎሩ ምክንያት የሚፈጠር ማሣከክ ሲኖር ቆዳን በሚጐዳና በከፍተኛ
ሁኔታ በጥፍር ማከክ ቁስለትና ተያያዥ ኢንፌክሽኖች እንዲፈጠሩ ሊያደርግ
ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
• በነጭና ቀይ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኘው Alicin (አሊሲን) የተባለው
ንጥረ ነገር ፀረ ፈንገሣዊ ባህሪ ስላለው በምግብ ስርዓታችን ውስጥ
ማካተቱ ተጨማሪ ጥቅም አለው፡፡
ውድ አንባብያን እነዚህንና የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመን ፎሮፎሩ ለውጥ
ካላመጣ ወይም እየተባባሠ ከሄደ ለፎሮፎር ህክምና ተብለው የሚዘጋጁ
ሻምፖዎችን መጠቀም ይኖርብናል እነዚህ የህክምና ሻምፖዎች
በውስጣቸው የተለያዩ አይነት የመድኃኒት ይዘት ያላቸውን ኬሚካሎችን
የሚይዙ ሲሆን በህክምና ባለሙያዎች አማካኝነት ታዘው ጥቅም ላይ
ይውላሉ፡፡
ሻምፖዎቹ በተለያዩ መንገዶች ፎሮፎርን የሚቆጣጠሩ ሲሆን
የጭንቅላት ቆዳ ሴሎችን የመብዛት ሂደት በመቀነስ፣ የሚመነጨውን
የቅባት መጠን በማስተካከል፣ በሚሞቱ ሴሎች መካከል የሚፈጠረውን
መጠባበቅ በማስቀረት በቀላሉ ከቆዳ ላይ ተላቀው እንዲረግፉ
በማድረግና Malassesia(ማላሴዝያ) የተባለውን ፈንገስ በማጥፋት
የፎሮፎር ችግርን በዘላቂነት ለመቆጣጠር ያስችላሉ፡፡
እነዚህ ሻምፖዎች
ከታዘዙልን በኋላ በትዕዛዙ መሠረት በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል
በተነገረን መጠንና የአጠቃቀም ጊዜ ተከታታይነት ባለው መልኩ መጠቀም
ከፍተኛ ለውጥን ያመጣል፡፡
ፎሮፎሩን በደንብ ለመቆጣጠር ረዘም ያለ
ጊዜን ሊወስድብን ስለሚችል በአግባቡ ሣንሠላች ተፈላጊው ለውጥ
እስኪመጣ ድረስ መጠቀም ይኖርብናል፡፡
የሻምፖዎቹ አጠቃቀም
– በመጀመሪያ ከመታጠባችን በፊት ፀጉርን በደንብ ማበጠሩ ፎሮፎሩ
እንዲረግፍና በሻምፖዎቹ ስንታጠብ በቀላሉ እንዲወገድ ይረዳናል፡፡
– በመቀጠል በሚስማማን የማፅጃ ሳሙና ወይም ሻምፖ ፀጉርና
የጭንቅላት ቆዳን በደንብ ማጠብና ማፅዳት ይኖርብናል፡፡
– የታዘዘልንን የህክምና ሻምፖ በታዘዘልን መጠን የጭንቅላት ቆዳችንን
በደንብ መቀባትና ፀጉርን እየከፋፈቱ ውስጥ ውስጡን በደንብ ማዳረስ
ያስፈልጋል፡፡
ሻምፖውን ለተነገረን ደቂቃዎች ያህል የጭንቅላት ቆዳችን ላይ
በጣቶቻችን እያሸን ማቆየት፡፡
ከተባልነው ደቂቃ በላይ ሻምፖዎቹን
በጭንቅላት ቆዳ ላይ ማቆየቱ የማቃጠል ስሜትን ሊፈጥርና ቆዳችንንና
ፀጉራችንን ሊጐዳ ስለሚችል በታዘዝነው መሠረት ብቻ መጠቀም
ይኖርብናል፡፡
ልክ የያዝነው ደቂቃ ሲያበቃ ፀጉራችንን በድጋሜ መታጠብ
ይኖርብናል ሻምፖውን ከፀጉራችን ላይ ስናፀዳ ወደ አይናችን እንዳይገባ
መጠንቀቅ ያስፈልጋል ፡፡
በመጨረሻ ፀጉርን በአግባቡ ማድረቅ ይገባል፡፡
እነዚህን የህክምና ሻምፖዎች መጠቀም ከጀመርን በኋላ የሚታይ
ተጨባጭ ለውጥ በተወሠነ ጊዜ ውስጥ ሊመጣ ይችላል፡፡
ነገር ግን ይህ
ማለት ፎሮፎሩ ሙሉ ለሙሉ ጠፋ ማለት ስላልሆነ ሻምፖዎቹን መጠቀም
ማቋረጥ የለብንም ፎሮፎሩን በአግባቡ ከተቆጣጠርነው በኅላም ቢሆን
ለተወሠነ ጊዘ ያህል መቀጠል ይኖርብናል፡፡
የፎሮፎሩ መጠን እየቀነሠ
ሲመጣ የምንጠቀመውን የሻምፖ መጠንም ሆነ ድግግሞሽ እየቀነስን
መምጣት እንችላለን፡፡
ሻምፖውን እየተጠቀምን ፎሮፎሩ ለውጥ ካላመጣ
ወደ ሀኪማችን በመሄድ ሌላ አይነት ሻምፖ እንዲቀየርልን ማድረግና መሞከር ይኖርብናል ምክንያቱም የተለያዩ ሻምፖዎች በተለያዩ መንገዶች ስለሚሠሩ አንዱ ያልተቆጣጠረልንን ሌላኛው ሊቆጣጠረው ይችላልና፡፡
እነዚህን የህክምና ሻምፖዎች ስንጠቀም የተለያዩ የአለርጂክ ምልክቶች ማለትም የተቀባነው ቆዳና አካባቢው ላይ መቅላት፣ ማበጥ መቁሠል
የመሣሠሉት ሁኔታዎች ከተከሠቱ በተጨማሪም የፀጉር መሠባበር እንዲሁም መነቃቀል ሁኔታዎች ካሉ በአፋጣኝ ሻምፖዎቹን ማቆምና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ መፍትሔ ማግኘት ይኖርብናል።

Did you know that Tonsil pain can lead to heartache and death?Do you know that the heart disease that happens to childre...
26/05/2021

Did you know that Tonsil pain can lead to heartache and death?
Do you know that the heart disease that happens to children aged 5 to 15 if it is not treated correctly, do you know that Tonsil infection will happen? I told you that Tonsil needle is near, I have told you that I have read a drug.
Father brought a 3 year old and told his son it's a tonic infection and he said yes he likes to suck snow. Using cold food or drinks, or even if it doesn't get a severe sun heat, do you know that it is a dangerous health problem to the community?
What is the cause of it?
Eating fatty foods in the sun is a health problem associated with bacteria and viruses.
Tonsil nominees in our throat are called Tolsilite when they are angry and angry.
These are bacteria and viruses that make our tonsils angry and burn.
Tonsil pain (tonsilitis) is the most common type of pain that most of us experience.
A child can be attacked by tonsil about eight times a year or tonsilitis.
The disease caused by tonsil disease or bacteria will start to see symptoms of the disease in the second three days after it has caused our tonsils.
What are the symptoms of Tonsil pain?
Tonsil pain is mostly attacking children and it may show the following signs.
• Tonsil's sting and madness
• Tonsil's debate
• living / swallowing pain during food time
• The fever of the fever
• The occurrence of candidates with neck pain and neck pain
• The change of the sound
• Bad breath smell
• Stomach pain (especially in their younger ages)
• Neck pain / Strength
• It's a headache.
On children who can't express their pain
• When they go out you have pain, you have to go out
• Refusing to eat food
• Unusual weakness are the symptoms of the pain.
How do you know if your child has tonsil infection?
When the sick person opens his mouth, the neck is seen on the left and right knee walls.
These Tonsil Candidates on the left and right wall sometimes high and can close their throat completely.
Battery-born tonsilitis can be seen in addition to the regular symptoms of the disease in the walls of the white cheese cheese / scars.
Tonsil pain is a kind of disease that transcends from human to human and attacks children more.
What is the risk of not treating tonsilitis in the season or nine days?
Stretchox Popegins can cause a person who is suffering from kidney disease that can lead to death if he doesn't get treatment from kidney failure (kidney failure) to heartache and death.
If a person who is infected with bacteria gives birt

10/04/2021

---_______--______-

ኮሌስትሮል ምንድነው?

-- -- -- ————
ኮሌስትሮል ማለት በደማችን ውስጥ የሚገኝ ስብ ወይም ቅባት መሰል ንጥረ-ነገር ነው፡፡ ሰውነታችን ስራን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስራት ኮሌስትሮልን ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከመጠን ያለፈ ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

የኮሌስትሮል መጠን በየእድሜው ምን ይመስላል?

19 አመት እና ከዛ በታች፡- አጠቃላይ ኮሌስትሮል ከ170 ሚሊ.ግ/ዴሲ.ሊ በታች

ወንድ 20 አመት እና ከዛ በላይ፡- አጠቃላይ ኮሌስትሮል ከ125-200 ሚሊ.ግ/ዴሲ.ሊ

ሴት 20 አመት እና ከዛ በላይ፡- አጠቃላይ ኮሌስትሮል ከ125-200 ሚሊ.ግ/ዴሲ.ሊ

የኮሌስትሮል ምርመራ በየስንት ጊዜው መደረግ አለበት?

19 አመት እና ከዛ በታች፡- በየ5 አመቱ መመርመር ሲኖርባቸው ነገር ግን የመጀመሪያው ምርመራ ከ9-11 አመታቸው ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡

20 አመት እና ከዛ በላይ፡- በየ5 አመቱ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል ሆኖም እድሜያቸው ከ45-65 የሆኑ ሰዎች ግን በየ1/2 አመቱ ቢመረመሩ ይመረጣል፡፡

የኮሌስትሮል መጠንን ምን ሊጨምረው ወይም ሊቀንሰው ይችላል?

አመጋገብ፡- አትክልት እና ፍራፍሬ መጠኑን ሲያተካክለው ቅባ ነክ ምግቦች መጠኑን ይጨምሩታል፡፡

የሰውነት ክብደት፡- በአማካይ ጤናማ ክብደት ያላቸው ሰዎች ለኮለስትሮል ተጋላጭነታቸው አነስተኛ ሲሆን ወፍራም የሆኑ እንደሆን ደግሞ ተጋላጭነቱ ይጨምራል

አካላዊ እንቅስቃሴ፡- በእለት ውሏቸው እንቅስቃሴ ማድረግ የሚያዘወትሩ ሰዎች በአማካይ እንቅስቃሴ ከማያደርጉ ሰዎች ለዚህ በሽታ ተጋላጭነታቸው በእጅጉን ያነሰ ነው፡፡

እድሜ፡- ከወጣቶች ይልቅ በጎላማሶች ላይ ችግሩ በብዛት ይስተዋላል፡፡

ጾታ፡- በብዛት በሴቶች ላይ ይስተዋላል

እጾችን መጠቀም፡- ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች አንጻር ለዚህ ችግር በጣም ተጋላጭ ናቸው፡፡

የኮሌስትሮል ታማሚ ከሆኑ እነዚህ ተግባራዊ ያድርጉ

ውሀ በሎሚ ይጠጡ

በቀን ለ30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ያድርጉ

ራሶትን ከጭንቀት ያርቁ

ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች ከእለት ምግቦት ይቀንሱ

የሚታዘዝሎትን መድሀኒት በአግባቡ ይውሰዱ፡፡

የኮሌስትሮል ችግር በቀላሉ የሚታይ በሽታ አይደለም ምክንያቱም የልብ ችግርን ስለሚያከትል ነው፡፡

Address

Baalee, Roobee
Robe

Opening Hours

Monday 03:00 - 12:00
Tuesday 03:00 - 12:00
Wednesday 03:00 - 12:00
Thursday 03:00 - 12:00
Friday 03:00 - 12:00
Saturday 03:00 - 12:00
Sunday 08:00 - 23:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Robe Donsa Mediumm Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram