
17/02/2025
ፅንፈኛ በአንድነት ሞት ይደግሳል ከዛም በአንድነት ነጠላውን ዘቅዝቆ ሙሾ አውራጆቹን ከፊት አሰልፎ ለቅሶ ይቀመጣል። #ህዝብ ሲያርድ እና ሲያሳርድ ያልተሰማው ርህራሄ በሞቱት መቃብር ላይ ቆሞ እያነባ በሬሳ #ፖለቲካ ይሰራል።
በጣም የሚገርመው በምንም የማይግባቡ እርስ በእርሳቸው በጥላቻ የሚተያዩ አካላት የጋራ ጠላታችን ነው የሚሉትን አካል ለማጥቃት ለህዝብ መደገሳቸው እና ነጠላ ዘቅዝቆ በአንድነት ጮክ ብሎ ማልቀሳቸው ነው።
ህዝቡ እስከ መች ነው እነዚህን የደም ነጋዴዎች የምታገሰው? እስከመቼስ ነው ለእነሱ የፖለቲካ ንግድ ስባል የህዝብ እልቂት የሚቀጥለው?
ለሁላችን የማንቂያ ደውል ይሁነን!!