W/soddo Health professional association

W/soddo Health professional association media / news about health care and update and credible share WHO based information to the community

29/08/2025
29/08/2025

ከባለይዞታና ከባለይዞታ ልጆች ጋር ተያይዞ በህገ ወጥ መንገድ ሊተላለፍ የነበረ 35 ሺ ካሬ መሬት ማዳን መቻሉን የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ገለጸ

ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም

በዚህም ወደ 35 ቢሊየን ብር ማዳን መቻሉም ተመላክቷል

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በከተማው እየተካሄዱ ያሉ የመልካም አስተዳደርና ልማት ስራዎችን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

እንደ ከንቲባዋ ገለፃ በከተማው ከባልይዞታና ባለይዞታ ልጆች ጋር በተያያዘ ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን የማጣራት ስራ በመስራት 35 ሺህ ካሬ ሜት መሬት ወደ መሬት ባንክ መመለሱን ተናግረዋል።

ይህም ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ የነበረን የህብረተሰብን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የፈታ ነው ብለዋል።

መሬትን ህጋዊ በሆነ መንገድ ለህብረተሰቡ በማስተላለፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ የገቢ ግብርን ለመሰብሰብ የጎላ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።

እስካሁን እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን እንደነበር ያነሱት ከንቲባዋ ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠይቀዋል።

28/08/2025

የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ‼️
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተወሰኑ አገልግሎቶች ላይ ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የአገልግሎት ክፍያ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

28/08/2025
22/04/2024

ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት

ጉዳዩ፡- የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአገልግሎት ክፍያን ስለማሳወቅ፤

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ለሚስጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዝርዝር እንድታሳውቁን መጋቢት 23/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ መጠየቃችን ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የመውጫ ፈተናውን #ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች ለሚያገኙት የአገልግሎት ክፍያ በአንድ ተማሪ 👉500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 እስከ ሚያዚያ 15/ 2016 ዓ. ም ድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንድታደርጉ እያሳወቅን የተከፈለበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ (antedefar@gmail.com & lakbt2013@gmail.com) እንድትልኩልን እናሳስባለን።

[ትምህርት ሚኒስቴር

24/04/2023

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ የ ምዝገባ ተጀምሮአል::
****

መመሪያ/Instruction/
1. በዚህ የኦንላይን ሲስተም መመዝገብ የሚቻለው ከሚያዚያ 16 - 25/2015 ዓ.ም ብቻ ነው።
2. አመልካቾች በዚህ የኦንላይን ሲስተም ለመመዝገብ ኮምፒውተር መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡ (በሞባይል ስልክ ለመመዝገብ መሞከር ምዝገባውን ያልተሟላ ሊያደርገው ይችላል፡፡)
3. ሁሉም ተመዛኞች (አዲስም ሆነ ነባር ተመዛኞች፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋም ተመራቂዎች) ፈተናውን ለመውሰድ በዚህ የኦንላይን ሲስተም መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህ የኦንላይን ሲስተም ለመመዝገብ ተመዛኞች መደበኛ የኢሜይል (email) አድራሻ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ (የ email አድራሻውንና ይለፍ ቃሉን በጥንቃቄ መያዝ ይኖርባቸዋል)
4. አዲስ አመልካቾች ለመመዝገብ ጉርድ ፎቶ፤ መታወቂያ(ማንኛውም መታወቂያ) ወይም ፓስፖርት እና ዲግሪ ሰርቲፊኬት ስካን አድርገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ፈተናውን በድጋሜ (Re-Exam) የምትወስዱ ተመዛኞች ምንም ዓይነት ዶክመንት ማያያዝ (Attach ማድረግ) አይጠበቅባችሁም፡፡
5. የግል ትምህርት ተቋም ተመዛኞች የትምህርት ማስረጃችሁን ህጋዊነት እና ትክክለኛነት በፌደራል ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል ማረጋገጥ (Authenticate ማስደረግ) የሚኖርባችሁ ሲሆን፣ Authenticate ካስደረጋችሁ በኋላ ስማችሁ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ወደ ጤና ሚኒስቴር እንዲተላለፍ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡
6. በምዝገባ ሂደት ወቅት ስማችሁ እንዳልተመዘገበ ወይም እንደሌለ የሚገልጽ መልዕክት ከተመለከታችሁ፣ ቀጥሎ በቢጫ ሰንጠረዥ ውስጥ ከሚያመጣላችሁ ዝርዝር ውስጥ ስማችሁን በመፈለግ በስማችሁ ትይዩ የተገለጸውን የትምህርት ተቋም (institution) ከታች ባለው የምዝገባ ሳጥን ላይ Institution / የተማሩበት ተቋም የሚለው ላይ በድጋሚ መርጣችሁ በማስገባት Next/ቀጥል የሚለውን በመጫን ምዝገባውን መቀጠል ይቻላል፡፡
7. ተመዛኞች የብቃት ምዘና ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉበትን የፈተና ጣቢያ ከተዘረዘሩት አማራጮች ውስጥ መምረጥ ይኖርባችኋል ፡፡
አዲስ ተመዛኞች ፎርሙን ሞልተውና ማስረጃዎቻቸውን upload አድርገው Submit ካሉት በኋላ ምዝገባቸው የሚጠናቀቀውና Registration ID የሚሰጣቸው ሲስተሙ የማስረጃ ማጣራት (Cross Checking) ስራ ካከናወነ በኋላ ስለሆነ ምዝገባውን ካከናወኑ ከ 72 ሰዓት(3 ቀናት) በኋላ hple.moh.gov.et ላይ ኢሜይልና ፓስወርድ በማስገባት Registration ID መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ (ምዝገባውን እስከመጨረሻው አጠናቅቆ Registration ID ያልወሰደ ተመዛኝ እንደተመዘገበ አይቆጠርም)
ተመዛኞች ምዝገባቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሲስተሙ የሚሰጣቸውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration ID) መዝግበው /ፕሪንት አድርገው/ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፦
- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ለመመዝገብ ተጨማሪ ዝርዝር ሂደቱን እና እንዴት እንመዝገብ ላላችሁ ዝርዝር አመዘጋገብ ሂደቱን ማየት ትችላላችሁ 👇
https://youtu.be/xpzpJ_WQnvY

14/08/2022
28/03/2022

የምደባ ጥሪ
አማራ ክልል ጤና ቢሮ ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ ጠቅላላ ሀኪሞች በሙሉ ለቋሚና ኮንትራት

ለተከታታይ የስራና ጤና ነክ መረጃዎች
በTelegram- t.me/healthinovation
በGroup t.me/HIVN19
በFb fb.com/andualemsew/ ይከታተሉን

28/03/2022
21/03/2022

እንኳን ደስ ያለን ! ደስ አላችሁ ! ታላቅ የድል ብሥራት !
======************************
**********************************************
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተደረገዉ ኢንስፔክሽን ተፈላጊዉን ሙያዊ ፤ ድርጅታዊና ሌሎች መስፈርቶችን ማሟላቱ ተረጋግጦ ይህ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከፌደራል ጤና ሚኒስቴር ተሰጥቷል ፡፡

“የተሻለ የጤና አገልግሎት ለህዝባችን እዉን ለማድረግ በትጋት እንሰራለን” የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አባላት::

16/03/2022

Address

Sodo

Telephone

+251924701628

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when W/soddo Health professional association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category