
14/09/2024
መልዕክቱ ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ ሼር በማድረግ ተባበሯቸው
'' ስለ ወላይታ ሶዶ ጤና ተማሪዎች ጠይቁልን እድሜ እየገበርን ነው በመመረቂያ ሰዓታችን ገና ከአንድ ዓመት በላይ የሚያቆይ የትምህርት ጊዜ ቆይታ አለብን እንዲም ሆኖ በየ ሰበቡ እያስወጣ ለሚያቆየን + ኋላ ቀርተን ሳለ የሌላው ዩኒቨርሲቲ የጤና ግቢ ተማሪ በሚማርበት ሰዓት እኛ ለ3ት ወር ቤት ለተዘፈዘፍነው + የኣዕምሮ ጭንቀት ውስጥ ላለነው + ከጓደኞቻችን /ከባቻችን ከአንድ ዓመት በላይ ወደኋላ ቀርተን ላለነው + ገብተንም እንዴትናቹ
ለማንባለው እንደ በሶ በተበጠበጠ ሽሮ ለምንኖረው + ኣመት ላመት በበጀት ኣለቀ እየተሳቀቅን ላለነው + በዚህ ሰዓት ሁላችንም ከጓደኛ ተለይተን ብቻችን ለቀረነው + ለቤተሰቦቻችን መች ትመረቃላቹ ጥያቄ ዛሬ ከ4ት ዓመት በኋላ መልስ ለሌለን ለእኛ ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ካምፓስ ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ድምፅ ሁኑን ድረሱልን ከባድ ምሬት ውስጥ ነን ክብድ ብሎናል እባካቹ ጠይቁል.......😢😢😢😭😭😭😭😭
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
እኛ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ካምፓስ ጤና ሳይንስ ተማሪዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በተለያዩ ሀገራዊ ችግሮች ምክንያት ሲባክንብን የነበረው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሊያካክስልን ሲገባ ግቢው በግድየለሽነት አዘግይቶ እየጠራንና አስቀድሞ ከግቢ እንድንወጣ በማድረግ መመረቅ ካለብን ጊዜ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲባክንብን ወይም ወደኋላ እንድንቀር አድርጎናል።
👇👇👇👇👇👇👇👇
አሁን ላይ ያለንበት ሁኔታ በዝርዝር ለመመልከት ያክል
የ2012 ባች የpharmacy ዲፓርትመንት ተማሪዎች ዘንድሮ 2016 ዓ.ም መመረቅ ሲገባን ገና 5ኛ ዓመትን አልጀመርንም
የ2013 ባች በ4 ዓመት የምረቃ ፕሮግራም መሰረት ዘንድሮ 2016 ዓ.ም መመረቅ የነበረብን የሁሉም ዲፓርትመንት የጤና ተማሪዎች ገና 3ኛ ዓመትን አልጨረስንም
የ2014 ባች አጠቃላይ የሁሉም ዲፓርትመንት ጤና ተማሪዎች ዘንድሮ 3ኛ ዓመትን ማጠናቀቅ ሲኖርብን ገና አልጀመርንም
የ2012 ባች የMedicine ዲፓርትመንት ተማሪዎች ዘንድሮ 5ኛ ዓመትን ማጠናቀቅ ሲኖርብን ገና አልጀመርንም
የ2013 ባች የpharmacy እና Medicine ዲፓርትመንት ተማሪዎች ዘንድሮ 4ኛ ዓመትን ማጠናቀቅ ሲኖርብን ገና 3ኛ ዓመትን አልጨረስንም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ስለሆነም ከሌላው ዩኒቨርሲቲ አቻ ባቾቻችን ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ተመርቀን እንደ ሀገር እኩል ተወዳድረን የስራ እድል ማግኘት የምንችልበትንና ወደፊት የሞያ እድገት ደረጃችን ማሻሻል የምንችልበትን ጊዜ በከንቱ መባከኑን ተከትሎ እየደረሰብን ያለው የስነ ልቦና ጫና እና እያመለጠን ያለው የስራ እድል እንዲሁም እስካሁን አስተምረው የእኛን ወግ ማዕረግ ለማየት በጉጉት እየጠበቁ የሚገኙት ቤተሰቦቻችን የእኛ ከምረቃ መዘግየት እያሳደረባቸው ያለውን የሞራል ውድቀት እና የኢኮኖሚ ብክነት ከግምት በማስገባት የሚመለከተው አካል ተገቢውንና ፈጣን የመፍትሔ ምላሽ እንዲሰጠን ስንል በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን። ''
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ካምፓስ ጤና ሳይንስ ተማሪዎች
ለበለጠ መረጃ በTelegram group and channel ቤተሰብ ይሁኑ
t.me/HSM077
t.me/WsuHealthOfficers