WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ

WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ Former, the college was called “Otona Hospital” established in 1928 as Small Clinic ; now WSU,CHSM

Wolaita Sodo University College of health science and medicine was established in 1928 as small clinic by Dr Thomas Lambe , missionary. Served for 50 years as primary hospital and for 30 years as general hospital. The hospital amalgamated with Wolaita Sodo University in 2004 E.C with academic responsibility ,demand driven research ,community service and quality clinical services . VISION

The college aspires to be one of the top five colleges of Health Science and Medicine in teaching, demand driven research and community services and quality clinical services nationally and well- well organized college in East Africa by 2020 E.C

MISSION

The college committed to work being engaged in provision of effective teaching and learning , research and community services as well as quality clinical services to the society and to provide its innovative educational philosophy of community based education (CBE) in areas of excellent in academic and professional competence , research adoption ,innovation and knowledge /technology transfer

STRATEGIC THEMES

• Excellent in academic and professional competence
• Excellent in research adoption , innovation and knowledge /technology transfer
• Excellent in quality clinical service
• Excellent in service in different aspects of administration and development issues

19/11/2025
18/11/2025
በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቅድመ ጥንቃቄ   ገለፃ ተሰጠ ።።።።።።።።   ኮ.ሕ.ግንኙነት 09/03/2018 ።።።።።።። ከመንግሥት በሚሰጡ አቅጣጫዎች መነሻ ተቋሙ ለበሽታው ምላሽና የጥንቃቄ እ...
18/11/2025

በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቅድመ ጥንቃቄ ገለፃ ተሰጠ ።

።።።።።።። ኮ.ሕ.ግንኙነት 09/03/2018 ።።።።።።።

ከመንግሥት በሚሰጡ አቅጣጫዎች መነሻ ተቋሙ ለበሽታው ምላሽና የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንደሚወስድ
ተመላክቷል ።
----------
ዶክተር ወኪል ወልዴ ፦ በምክትል ፕረዚዳንት ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ግንዛቤና የጥንቃቄ እርምጃዎች በተገቢው እዲወሰዱ ለማድረግ ያለመ ገለፃ እንደሆነ ተናግሯል ።

ቫይረሱ፥ በገዳይነቱ የሚታወቅ በመሆኑ ከመንግሥት በሚሰጡ አቅጣጫዎች መነሻ፦ ተቋሙ የመጀመሪያውን ለቫይረሱ ምላሽና የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንደሚወስድ
አሳውቀዋል ።

መላው ስታፍ፣ የሆስታላችን ደንበኞችና ማሕበረሰባችን በሙሉ የጥንቃቄ ሥራዎችን ለመሥራት በተለይም የሰው ፊሰት በተገቢው ለመቆጣጠር ትብብር እንዲያደርጉና የመከላከያ ዘዴዎች በመከተል እንዲከላከል አጽንኦት ሰጥተዋል ።

ዶክተር ኢዮስያስ አብረሃም ፥ በሆስፒታሉ የውስጥ ዴዌ ሕክምና ስፔሻሊስት ፤ የበሽታውን ምንነት ፣ ምልክቶችን ፣ መተላለፊያና መከላከያ ዘዴዎችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል ።

በውይይቱ ፥ተገቢው የመከላከል ሥራዎች እየተሰሩ መደበኛው የሕክምና አገልግሎት አሠጣጥ እንደማይቋረጥ ተገልጾ ፤ በቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ፣ በታካሚ ቅብብሎሽ፣ በግንዛቤ መፍጠር ፣ በግብዓት ማሟላት እንዲሁም በሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች አስተያየትና ጥያቄ ተነስቶ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

።።። ጥንቃቄ ይጠብቃል ።።።።።
።።።ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኘነት ።።
።።። ሕዳር 09/2018። ዓ.ም።።።

15/11/2025
ሰሞኑን ጅንካ  አካባቢ በተከሰተው ተላላፊ በሽታ ዙሪያ ቅድመ ጥንቃቄ ኦሬንተሽንና ውይይት ተካሂዷል። =============ተላላፊ በሽታው በአሁኑ ሰዓት አደጋው አስጊ ባይሆንም በኃላፊነት የቅ...
14/11/2025

ሰሞኑን ጅንካ አካባቢ በተከሰተው ተላላፊ በሽታ ዙሪያ ቅድመ ጥንቃቄ ኦሬንተሽንና ውይይት ተካሂዷል።
=============
ተላላፊ በሽታው በአሁኑ ሰዓት አደጋው አስጊ ባይሆንም በኃላፊነት የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ሊሠሩ ይገባልም ተብሏል ።
----------
ዶክተር ወኪል ወልዴ ፦ በምክትል ፕረዚዳንት ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፥ የበሽታውን የስርጭት አዝማሚያ እያየን መላውን ስታፍ እንዲሁም ማሕበረሰባችንን የማስገንዘብ ሥራ እንሰራለን ብለው፤ ጤና ባለሙያዎች በተገቢው ግለ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ስርጭቱን መግታት ይገባል ብለዋል ።

ኢፌዴሪ ጤና ሚንስቴር ፣የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ባለድርሻ አካላት በሚሰጡን Case definition መሠረት የምንሠራው ሥራ ይኖራል ያሉት ዶክተር ወኪል፤ በአሁኑ ሰዓት አደጋው አስጊ ባይሆንም በኃላፊነት የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ሊንሠራ ይገባል ብሏል ።

ከክሊኒካል ካውንስል አባለት ቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ዙሪያ ፣ አስፈላጊ ግብዓት እንዲሁም ላይዜንና ሪፌራል ቅብብሎሽ ሥራ ተግባቦት ዙሪያ አስተያየትና ጥያቄ ተነስቶ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

።።።ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኘነት ።።

።።። ሕዳር 05/2018። ዓ.ም።።።

በወቅታዊ ሄሞራጅክ ፈቨር ( Hemorrhagic Fever ) በሽታ ቅድመ ጥንቃቄን አስመልክቶ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል =============በሽታውን አስመልክቶ የኢፌዴሪ ጤና ሚንስ...
13/11/2025

በወቅታዊ ሄሞራጅክ ፈቨር ( Hemorrhagic Fever ) በሽታ ቅድመ ጥንቃቄን አስመልክቶ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል =============
በሽታውን አስመልክቶ የኢፌዴሪ ጤና ሚንስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በትኩረት እየተከታተሉ ቢሆንም ተቋማዊ የጥንቃቄና የዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት አስቻይ ውይይት ተካሂዷል ።
-------
ዶክተር ወኪል ወልዴ ፦ በምክትል ፕረዚዳንት ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፥ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ሲከሰት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በትኩረትና በቅንጅት የሚሰራ ቢሆንም እንደተቋም ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን መሥራት ወሳኝ ነው ብለዋል ።

ዶክተር አክለው ፤ አስፈላጊውን ግብዓት ለማሟላት (PPE) ፣ የግንዛቤና የጥንቃቄ ሥራዎች በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

በውይይቱ የሁሉም ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈው በጋራ መግባባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ።

ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኘነት
ሕዳር 04/2018 ዓ.ም

12/11/2025

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

ከአምስት መቶ ሺህ ብር በላይ  ዋጋ ያለው ለሕክምና አገልግሎት የሚውል  ድጋፍ ተደረገ ።=========የኢትዮጵያ ስኳር ሕሙማን ማሕበር ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንሰና ሕክምና ኮሌጅ ...
08/11/2025

ከአምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያለው ለሕክምና አገልግሎት የሚውል ድጋፍ ተደረገ ።
=========
የኢትዮጵያ ስኳር ሕሙማን ማሕበር ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንሰና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያለው ለሕክምና አገልግሎት የሚውል ማቀዝቀዣ ድጋፍ አደረገ
==========
ሲስተር ሰላማዊት ገብረ ሀና በሆስፒታሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሕክምና ክፍል አስተባባሪ ድጋፉ፥ ከኢትዮጵያ ስኳር ሕሙማን ማሕበር ጋር ባደረጉት መልካም ግንኘነት ተጻጽፈው ያመጡት ድጋፍ እንደሆነ ተናግረዋል ።
ሲስተር ሰላማዊት፥ ማሕበሩ የስኳር በሽታን መከላከልና መረጃ ላይ የተመሠረተ የሕክምና እንዲሁም የምክር አገልግሎት አባላቱ እንዲያገኙ በትኩረት እየሠራ ይገኛልም ብለዋል ።

ድጋፉን ዶ/ር ተገኝ ባሼ ፥ በሆስፒታሉ የጤና አገልግሎት ምክትል ኮርፖሬት ዳይሬክተር ፥ ማሕበሩ ያደረገውን አብርቶ አመስግነው ተረክበዋል ።

ዕውቀትን በተግባር!
የተሻለ የጤና አገልግሎት ለሕዝባችን!

ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ቡድን
ጥቅምት 29, 2018 ዓ.ም

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነጻ የጡት ካንሰር ምርመራና የምክር አገልግሎት    መሰጠት ተጀመረ ።=====================👉 የጡት ካንሰር በሽታን ቀድሞ ማወቅ ከሞት ይታደጋል ።=====...
03/11/2025

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነጻ የጡት ካንሰር ምርመራና የምክር አገልግሎት መሰጠት ተጀመረ ።
=====================
👉 የጡት ካንሰር በሽታን ቀድሞ ማወቅ ከሞት ይታደጋል ።
==============
ጥቅምት ፥ አለም አቀፍ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በመሆኑ ፤የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፥ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራና የምክር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ዶክተር ተገኝ ባሼ በሆስፒታሉ የጤና አገልግሎት ምክትል ኮርፖሬት ዳይሬክተር በፕሮግራሙ መክፈቻ ተናገሩ ።

ዶክተር ተገኝ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ የሚሰጠውን ነፃ አገልግሎት ወገኖቻችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ መረጃውን በማጋራት እንዲተባበሩም አሳስበዋ።

👉የኮሌጁ ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ .... ግንኙነት
።።። ጥቅምት 24/2018። ዓ.ም።።።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች እየገቡ ነው!! በ2017 ዓ.ም በአቅም ማሻሻያ (ሪሜዲያል) መርሀ-ግብር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተ...
31/10/2025

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች እየገቡ ነው!!

በ2017 ዓ.ም በአቅም ማሻሻያ (ሪሜዲያል) መርሀ-ግብር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በአንደኛ አመት ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የሠላም አምባሳደር ወደሆነው ዩኒቨርሲቲያችን በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

የዩኒቨርሲቲው እና የአካባቢው ማሕበረሰብም ደማቅ አቀባባል እያደረገላቸው ሲሆን፤ መደበኛ የምዝገባ ሂደት የሚከናወነው ጥቅምት 21 እና 22/ 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል!!

ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን አረንጓዴ፣ ጽዱ፣ ሠላማዊ፣ ሕብረብሔራዊ እና ተወዳዳሪ ወደ ሆነው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ!!

Wolaita S**o University

።።።።።። ማስታወቂያ !።።።።።።። ለወላይታ ሶዶ ከተማና አካባቢው ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ለሆኑ እናቶቻችንና እህቶቻችን በሙሉ ፤=====================👉 የጡት ካንሰር በሽ...
30/10/2025

።።።።።። ማስታወቂያ !።።።።።።።

ለወላይታ ሶዶ ከተማና አካባቢው ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ለሆኑ እናቶቻችንና እህቶቻችን በሙሉ ፤
=====================
👉 የጡት ካንሰር በሽታን ቀድሞ ማወቅ ከሞት ይታደጋል ።
==============
ጥቅምት ፥ አለም አቀፍ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በመሆኑ ፤ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (ኦቶና) ፥ ከጥቅምት (21- 30/2018 ዓ.ም) ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራና የምክር አገልግሎት ይሰጣል ።

👉 ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ከጥዋቱ 2 : 00 ሰዓት ጀምሮ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ የሚሰጠውን ነፃ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራና የምክር አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ ።

ውድ የማሕበራዊ ትስስር ገጻችን ቤተሰቦች ፤ ወገኖቻችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መረጃውን በማጋራት ስለሚተባበሩን ከወዲሁ እናመሰግናለን

👉የኮሌጁ ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት
።።። ጥቅምት 20/2018። ዓ.ም።።።

የሐዘን መግለጫ =====የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ፥ የስፔሻሊቲ ተማሪ ዶክተር አንዷለም ተመስገን በድንገት ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።ዶክተር አንዷለም ተመስገን የመ...
29/10/2025

የሐዘን መግለጫ
=====
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ፥ የስፔሻሊቲ ተማሪ ዶክተር አንዷለም ተመስገን በድንገት ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ዶክተር አንዷለም ተመስገን የመጀመሪያ ዓመት የውስጥ ዴዌ ሕክምና ስፔሻሊቲ ተማሪ የነበሩ ሲሆን ፤ ዛሬ ጥቅምት 19, 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በድንገት በሞት ተለዩ ።

የኮሌጁ አስተዳደር በዶክተር አንዷለም ተመስገን ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማውን ሐዘን እየገለፀ ፥ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው ባልደረቦች መጽናናትን ይመኛል ።

Address

Wolaita
Sodo

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram