
21/08/2023
ወቅቱን ጠብቆ የሚመጣዉን የኮሌራ ወረርሽኝና የወባ በሽታን ለመግታትና ለመቆጣጠር በጋራ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ
በሌ አዋሳ፤ ነሐሴ 15/2015 በበሌ አዋሳ ከተማ አስተዳዳር ጤና ዩኒቲ የኮሌራ በሽታና የወባ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያለመ ከተማዊ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የኮሌራ በሽታ እና የወባ በሽታ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚደርሰው ጉዳት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት የበሌ አዋሳ ከተማ አስ/ር የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር አባይነህ አጫ በሽታዉ እንዳይዛመት እና እንዳይስፋፋ የሁላችንም ሚና ከፍተኛ ልሆን ይገባል ብለዋል።
አክለዉም ዶ/ር አባይነህ አጫ አከባቢያችን ቆላማ ከመሆኑም አንጻር በስፋት የሚስተዋለዉን የወባ በሽታ ለመከላከል በህብረተሰቡ ዘንድ የአልጋ አጎበር አጠቃቀም ልስተካከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በሽተዉን ለመከላከል ከንጽህና ጉድለት ጋር የተያያዙ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ ያሳሰቡት ዶ/ር አባይነህ አጫ ምግብ ቤቶች፣ እንዲሁም መጸዳጃ ቤቶች በአግባቡና በንጽህና መጠቀም እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
የበሌ አዋሳ ከተማ አስ/ር ም/ከንቲባና ኢኮኖሚ ክለስተር አስተባባሪ አቶ ተመስገን ፎላ ወረርሽኙ በፍጥነት የሚዛመት ስለሆነ ቀድመን ለመቆጣጠርና ለመከላከል አስፈላጊውን ስራ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
አያይዘዉም አቶ ተመስገን ፎላ ከጤና የሚተላለፉ መልእክቶችን የመረጃ ፍሰትን በጠበቀ መልኩ በደንብ ማዳመጥና ተግባር ላይ ማዋል ብሎም ማህበረሰቡን መታደግ ይገባል ብለዋል።
በበሽታዉ በአንድ ግለሰብ ከተያዘ ከአንድ እስከ አራት ሳምንት ድረሰ ምንም አይነት ምልክት ላሳይ ስለምችል ህብረተሰቡ በሽታ አምጪ ናቸዉ ተብሎ በጤና ኤክስተሽን በኩል የሚሰጡ ትምህርቶችን ተግባራዊ በማድረግ በሽታዉን ልከላከል ይገባል ብለዋል።
ኮሌራን ጨምሮ የዘርፈ ብዙ ወረርሽኝ በሽታ መከላከል ግብረ ሃይል አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነትን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሰነዶች በጤና ዩኒቲ አቶ ተስፋዬ ኡርቼ ያቀረቀበ ስሆን ሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጎበት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም ዶ/ር አባይነህ አጫ የኮለራ በሽታንም ሆነ የወባ በሽታን የቅደመ መከላከል ተግባራት ከፈጸምን ምንም አይነት አስከፊ ጉዳት ሳይደርስ ልቆጣጠረዉ የምንችለዉ ነገር ስለሆነ ሁላችን ቅንጅታዊ አሰራርን በመዘርጋት በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል
በመድረኩ የከተማ አስተባባሪ አካላት፣ የከተማ እና የቀበሌ አመራሮች፣ የከተማ ጤና ዩኒቲ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንድሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።