Frie Drug Store

Frie Drug Store Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Frie Drug Store, Medical and health, Woldia.

❄️❄️ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡  ❄️❄️🎄🎄🎄 መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ የሁልጊዜ ቀዳሚ ምርጫችሁ የሆነው Frie Dru...
06/01/2025

❄️❄️ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ❄️❄️

🎄🎄🎄 መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ የሁልጊዜ ቀዳሚ ምርጫችሁ የሆነው Frie Drug Store,Woldia መልካም ምኞቱ ነው።🎄🎄🎄
Merry Christmas
🎄??🎄
Drug Store,Woldia

17/12/2024
+251912907027or+251960000899
14/12/2024

+251912907027
or
+251960000899

20/08/2024

ውሃ መጠጣት የሚያስገኛቸው የጤና በረከቶች

ብዙ ውሃ መጠጣት ለአጠቃላይ ጤንነት እና ደህንነት በጣም አስፈላጊ ነው። ውኃ መጠጣት ወይም እርጥበትን መጠበቅ አስፈላጊ የሆነባቸው ዘጠኝ ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:

1. የሰውነት ሙቀትን ይጠብቃል
ውሃ በላብ እና በትንፋሽ አማካይነት የሰውነትን ሙቀት ለመቆጣጠር ይረዳል።
ከመጠን በላይ በሚሞቅዎት ጊዜ ያቀዘቅዝዎታል እንዲሁም የሰውነትዎ ሙቀት እንዲረጋጋ ወይም እንዳይለዋወጥ ያደርጋል።

2. የምግብ መፈጨትን ይደግፋል
ውኃ ለምግብ መፈጨት በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምግብን ለመሰባበር እና ገንቢ ንጥረ-ነገሮች እንዲመጠጡ ለማድረግ ይረዳል። በተጨማሪም ሰገራን በማለስለስ እና መደበኛ የአንጀት እንቅስቃሴ እንዲኖር በማድረግ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል።

3. ገንቢ ንጥረ-ነገሮችን ለማጓጓዝ ይረዳል
ውኃ ዋነኛ የደም ክፍል ሲሆን፤ በሰውነታችን ውስጥ ለሚገኙ ሴሎች በሙሉ አስፈላጊ የሆኑ ገንቢ ንጥረ-ነገሮችን እና ኦክስጅንን ያጓጉዛል።

4. መርዛማ ንጥረ-ነገሮችን ያስወግዳል
ውኃ ኩላሊታችን ከደም ውስጥ ቆሻሻን በማስወገድ በሽንት በኩል ወይም በሽንት መልክ እንዲወጣ ይረዳል። ይህም በኩላሊት ጠጠር እና በሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን የመያዝ አደጋን ይቀንሳል።

5. የቆዳ ጤንነትን ያሻሽላል
ውኃ መጠጣት፤ የቆዳችንን የመለጠጥ ችሎታ ጠብቆ ለማቆየት፣ ድርቀትን ለመቀነስ እና ያለጊዜው የሚከሰትን እርጅና ለመከላከል ስለሚረዳ እርጥበትዎን መጠበቅ ቆዳዎ ጤናማ እንዲሆን ያደርገዋል።

6. አካላዊ እንቅስቃሴን ይጨምራል
ለአካላዊ ብቃት በተለይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት በትክክል ውሃ መጠጣት ወሳኝ ነው። መገጣጠሚያዎቻችን ለማለስለስ፣ ገንቢ ንጥረ ምግቦችን ለማጓጓዝ እንዲሁም የጡንቻ ድካምን እና መኮማተርን ለመከላከል ይረዳል።

7. የአንጎል ተግባርን ያሻሽላል
መለስተኛ ድርቀት እንኳን የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባር ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል። ይህም የትኩረት፣ የንቃት እና የአጭር ጊዜ የማስታወስ ችሎታ ችግርን ያስከትላል። በቂ ውሃ መጠጣት ትኩረትን ለመሰብሰብ እና የአዕምሮ ተግባርን ለማሻሻል ይረዳል።

8. ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል
ከምግብ ከመመገብዎ በፊት ውሃ መጠጣት የመጠገብ ስሜት እንዲሰማን በማድረግ የምግብ ፍላጎታችንን ለመቆጣጠር ይረዳል፤ ይህም የምንወስደውን የካሎሪ መጠንን ይቀንሳል። በተጨማሪም ውሃ ሜታቦሊዝምን በትንሹ ከፍ ሊያደርግ ይችላል።

9. የልብና የደም ዝውውር ጤናን ይደግፋል
በቂ ውሃ መጠጣት ልብዎ ደምን ለመርጨት ከአቅም በላይ መሥራት እንደማያስፈልገው ያረጋግጣል። ይህም ጤናማ የደም ግፊት መጠንን ለመጠበቅ እንዲሁም የልብ እና የደም ዝውውር ችግርን ለመቀነስ ይረዳል።

10. በሽታ የመከላከያ ስርዓትን ይደግፋል
እርጥበትዎን መጠበቅ የሰውነትዎን ሴሎች እና ቲሹዎች ጤና ለመጠበቅ ይረዳል፤ ይህም ለጠንካራ የበሽታ መከላከያ ስርዓት አስፈላጊ ነው። የሰውነት ፈሳሽን በትክክል መጠበቅ፤ ሰውነትዎ ኢንፌክሽንን በተሳካ ሁኔታ ለመዋጋት እና በሚታመሙበት ጊዜ በፍጥነት ለማገገም ያስችላል።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች፤ የሰውነታችንን የተለያዩ ተግባራት ለመደገፍ እና ጤንነትን ለመጠበቅ በየቀኑ በቂ ውሃ መጠጣት ለምን ወሳኝ እንደሆነ ያሳያሉ።



ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ጤና ቢሮ የመረጃ መረቦች ከታች ያሉ ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id
ቴሌግራም፡- https://t.me/AmharaHB
ዩቱዩብ፡- https://yout

15/08/2024

#እንድታውቁት

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) የተያዙ ህሙማን የሚያሳዩዋቸው ዋና ዋና ምልክቶች፦

- ትኩሳት፣
- ራስ ምታት፣
- የዕጢ እብጠት፣
- የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣
- ሽፍታ፣
- የቆዳ ቁስለት
- የአቅም ማጣት ናቸዉ።

እነዚህ ምልክቶች መከሰታቸው የተረጋገጠ እና በቅርቡ በሽታው ወደ ተከሰተባቸው ሀገሮች የጉዞ ታሪክ ያለዉ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና እንክብካቤ ማግኘት አለበት።

በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ ነው።

ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛዉም ሰው በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት ማድረግ ወይም በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲደረግ ጤና ሚኒስቴር ጠይቋል።

30/06/2024
Different   Dermatological Drugs!!Please visit Our institution!!
01/07/2021

Different Dermatological Drugs!!
Please visit Our institution!!

Recommendations!!!
16/04/2021

Recommendations!!!

Address

Woldia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Frie Drug Store posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram