woldia comprehensive specialized hospital

woldia comprehensive specialized hospital 62 years old

***የሳንባ ምች በምን ምክንያት ይከሰታል? ***                                                    የሳንባ  ምች(ኒሞኒያ) አብዛኛውን ጊዜ በኢንፌክሽን ምክንያ...
27/08/2025

***የሳንባ ምች በምን ምክንያት ይከሰታል? *** የሳንባ ምች(ኒሞኒያ) አብዛኛውን ጊዜ በኢንፌክሽን ምክንያት የሚመጣ የሳንባ መቆጣት ነው።

የበሽታው ምክንያት ከቀላል እስከ ከባድ የሚደርስ የሳንባ ኢንፌክሽን ሲሆን÷ ኢንፌክሽኖች በሳንባዎች ውስጥ የሚገኙትን የአየር ከረጢቶች በፈሳሽ ወይም በመግል ሲሞሉ ለመተንፈስ እና ኦክስጅንን ወደ ደም ውስጥ ለማስገባት አስቸጋሪ ያደርገዋል።

እድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት እና ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንቶች በተዳከመ የበሽታ መቋቋም ስርዓት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ ለሳንባ ምች ተጋላጭ እንደሆኑ በዘርፉ የተጠኑ ጥናቶች አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም እንደ የልብ ህመም፣ የስኳር በሽታ፣ የሳንባ በሽታ፣ በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክሙ እና አንዳንድ ካንሰሮችን የመሳሰሉ ሥር የሰደዱ የጤና እክሎች ያለባቸው ሰዎች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።

የሳንባ ምች በሳል እና በማስነጠስ ወቅት በሚኖሩ የፈሳሽ ጠብታዎች፣ ወይም እቃዎችን በመንካት እና ጀርሞችን ወደ ሰውነት በማስገባትና በሌሎች ምክንያቶች ሊሰራጭ ይችላል።

በሽታው በአብዛኛው ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል ከፍተኛ የሆነ ሳል፣ትኩሳት እና ላብ፣የድካም ስሜት፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ራስ ምታት፣ ለመተንፈስ መቸገርና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ ፡፡

የሳንባ ምች ከተከሰተበት ሁኔታ በመነሳት ሆስፒታል ለረጅም ጊዜ በመቆየት ምክንያት የሚከሰት የሳንባ ምች፣የሞቀ ሰውነት ከቅዝቃዜ ጋር ሲጋጭ የሚከሰት የሳንባ ምች፣ንጽህናውን ያልጠበቀ ምግብና መጠጥ በመውሰድና አልኮል አብዝቶ በመውሰድ የሚመጣ የሳንባ ምች ፣ጥንቃቄ በጎደለው መጠጋጋት የሚመጣ የሳንባ ምች ተብለው ይከፈላሉ ፡፡

በበሽታው እንደተያዘ የጠረጠረ ሰው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ የደም ምርመራ፣የደረት ኤክስሬይ፣በደም ውስጥ ያለውን የኦክስጅን መጠን በመለካት፣ የአክታ ምርመራ በማድረግ እና በሳንባ አካባቢ ፈሳሽ ቋጥሮ ከሆነ በመርፌ ናሙና ተወስዶ ምርመራ እንዲደረግለት በማድረግ መለየት የሚችል ሲሆን÷ የሳንባ ምቹ ካለበትም አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት እንደሚገባም ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

እንደ በሽታው ክብደት ሁኔታ ሲቲ ስካን እና ብሮንኮስኮፒም ሊታዘዝ እንደሚችልም የኤን አይ ዲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሳንባ ምች የተያዘ ሰው ተገቢውን ህክምና ካገኘ አብዛኛውን ጊዜ ሌላ ጉዳት ሳያስከትል በቀላሉ ሊድን እንደሚችልም ነው ጥናቶች የሚያረጋግጡት ፡፡

ስለ ኩፍኝ ምን ያውቃሉ?ኩፍኝ ማለት ሚዝልስ (Measles) በተባለ ረቂቅ ተህዋስ (ቫይረስ) አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ የሆነ በሽታ ነው። በዋናነት ክትባት ያልወሰዱ ህፃናት ላይ የሚከሰት ቢ...
27/08/2025

ስለ ኩፍኝ ምን ያውቃሉ?
ኩፍኝ ማለት ሚዝልስ (Measles) በተባለ ረቂቅ ተህዋስ (ቫይረስ) አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ የሆነ በሽታ ነው። በዋናነት ክትባት ያልወሰዱ ህፃናት ላይ የሚከሰት ቢሆንም አዋቂዎች ላይም ሊከሰት ይችላል።

የኩፍኝ በሽታ በዋናነት በትንፋሽ የሚተላለፍ ሲሆን ለበሽታው አጋለጭ ሁኔታዎችም፡-
 በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም፣
 በሽታው ካለበት ሰው ጋር ንክኪ መኖር፣
 የምግብ እጥረት
 እና የቫይታሚን ኤ እጥረት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡

የኩፍኝ በሽታ ዋና ዋና ምልክቶች፤-
 ከፍተኛ የሆነ ሙቀት፣
 አይን መቅላት
 ማሳል፣ ውሃ የመሰለ ንፍጥ፣
 ከራስ/ አንገት አካባቢ ጀምሮ ወደ እግር የሚሄድ ሽፍታ፣
 ማቅለሽለሽ፡
 የምግብ ፍላጎት መቀነስ
 እና ተቅማጥና ማስመለስ ናቸው፡፡
በኩፍኝ በሽታ ሊመጡ የሚችሉ ውስብስብ ችግሮች
• የሳንባ ምች፣
• የጀሮ ክፍል በሽታ፣
• አይነ ስውርነት፣
• የጉበት በሽታ እና
• የመድማት ችግር ናቸው፡፡

የኩፍኝ በሽታ ህክምና
 ፈሳሽ ነገር አብዝቶ መውሰድ፣
 ቪታሚን ኤ መስጠት
 የአይን ጠብታ/የሚቀባ መድኃኒት እና
 በሽታው እንዳይባባስ ተገቢውን ህክምና ማግኘት

የኩፍኝ በሽታ መከላከያ መንገዶች

 የኩፍኝ ክትባት ልጆቻችን(እህት ወንድሞቻችን) በወቅቱ እንዲወስዱ ማድረግ፣
 የግል እና የአካባቢን ንፅህና መጠበቅ
 በቂ እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና
 በበሽታው ከተጠቁ ውይም የኩፍኝ ምልክቶች ከታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ህክምና ማግኘት፡፡

ምንጭ፡- እናቶች፣ህፃናት እና አፍላ ወጣቶች ዳይሬክቶሬት
የክትባት ኬዝ ቲም

ትክክለኛ  የምጥ  ምልክት  በመጨረሻ  የእርግዝና ሳምትዎ  ሲያጋጥምዎ  ወይም  ከታች  የተጠቀሰው  እውነተኛ  የምጥ  ምልክቶችን  ሲያዩ  በፍጥነት  አቅራቢያዎ  ወዳለው  ጤና  ተቋም  በ...
27/08/2025

ትክክለኛ የምጥ ምልክት በመጨረሻ የእርግዝና ሳምትዎ ሲያጋጥምዎ ወይም ከታች የተጠቀሰው እውነተኛ የምጥ ምልክቶችን ሲያዩ በፍጥነት አቅራቢያዎ ወዳለው ጤና ተቋም በመሄድ ቸክ ያድርጉ!!
#የእውነተኛ #ምጥ #ምልክቶች
======
ነፍሰጡር እናቶች የሚከተሉትን ምልክቶች ካዩ በፍጥነት ሀኪምቤት መሄድ አለባቸው

✅ጠንካራ የማህፀን መኮማተር

✅የታችኛው ጀርባ ህመም ወይም ግፊት

✅በሆድ ውስጥ ወይም በሆድ አካባቢ ውስጥ ቁርጠት

✅በደረት ወይም በታችኛው የሆድ ክፍል ውስጥ የክብደት ስሜት

✅በደም የተበከለው የንፋጭ ፈሳሽ መፍሰስ

✅የእንሽርት ውሃ መፍሰስ

✅የጉልበት መዛል ወይም እረፍት ማጣት

ከላይ የተዘረዘሩት የምጥ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችል በመጨረሻ የእርግዝና ሳምንታት ላይ ያሉ ነፍሰጡር እናቶች ወድያው ሀኪም ቤት መሄድ አለባቸው።

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

በከፍተኛ  ሁኔታ  ሆስፒታላችን  ላያ  እየተሰራ  ያለው  መሰረተ  ልማት  ተጠናክሮ  እንዲቀጥልና  የሲቲስካኑን  ገጠማ  አፋጥኖ  ለማህበረሰባችን  የተሟላ  የህክምና  አገልግሎት  በመስጠ...
27/08/2025

በከፍተኛ ሁኔታ ሆስፒታላችን ላያ እየተሰራ ያለው መሰረተ ልማት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሲቲስካኑን ገጠማ አፋጥኖ ለማህበረሰባችን የተሟላ የህክምና አገልግሎት በመስጠት የጤናውን ፍላጎት የመለሰ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የሆስፒታሉ ማህበረሰብ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበኩሉን አስተዋፆ ማድረግ ይጠበቅብናል!! የተሻሻለ የጤና አገልግሎት ለሁሉም!!!!

ሁላችንም  ሸር  በማድረግ  ይሄን  መረጃ  አጋሩልን !!!         በአብክመ ጤና ቢሮ ግዥ ተፈፅሞ ለወልዲያ ሆስፒታል ገቢ ተደርጎ የነበረው ሲቲ ስካን ማሽን በጥሩ ሁኔታ ኢንስቶል ተደር...
27/08/2025

ሁላችንም ሸር በማድረግ ይሄን መረጃ አጋሩልን !!! በአብክመ ጤና ቢሮ ግዥ ተፈፅሞ ለወልዲያ ሆስፒታል ገቢ ተደርጎ የነበረው ሲቲ ስካን ማሽን በጥሩ ሁኔታ ኢንስቶል ተደርጎ የሙከራ ስራ ተሰርቶ ለባለሞያዎች አጭር ግንዛቤ ተፈጥሯል። በአጭር ቀን ሙሉ ስልጠና ተሰጥቶ ወደ ተሟላ አገልግሎት የሚገባ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለሶስት ታካሚዎች ሙከራ ተደርጎበት ደሴ ከመሄድ መዳን ችለዋል።የሆስፒታላችን ተገልጋዮቾ በአጭር ጊዜ ሙሉ አገልግሎ የሚጀምር መሆኑን እያሳወቅን እንኳን ደስ አላችሁ ይላል ወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ።

27/08/2025
ለሁሉም  የሆስቲፒታሉ  ተገልጋዮች  በሙሉ  ከዚህ  በሃላ  የታካሚዎችን  መብት  ከማክበር  እና  የመጡበትን  ከመፈፀምም  አንፃር  የታማሚ  ጠያቂዎችን  እንደሚከተለው  የመጠየቂያ  ሰአት...
27/08/2025

ለሁሉም የሆስቲፒታሉ ተገልጋዮች በሙሉ ከዚህ በሃላ የታካሚዎችን መብት ከማክበር እና የመጡበትን ከመፈፀምም አንፃር የታማሚ ጠያቂዎችን እንደሚከተለው የመጠየቂያ ሰአት ስለተመቻቸ በተገለፀው ሰአት በመምጣት አላስፈላጊ እንግልትን በጋራ እንከላከል እንላለን። ከታች ያለውን የሰአት ሽግሽግ አብዛኛውን ማህበረሰብ ይስተካከል ባላችሁን መሰረት አስተካክለናል።
የመጠየቂያ ስዓት
ጧት 12:00- 2:00 ከስዓት 6:00-8:00 ማታ 10:30-12:30 የተሻሻለ መሆኑን እንገልፃለን።

27/08/2025

ከዚህ በታች እንደሰፈረው አይነትን ችግር በጊዜ ለመቆጣጠር ነፍሰ ጡር እናቶች የእርግዝና ክትትል በጊዜ ወይም ከሶስት ወር በታች እያላችሁ መጀመር ለጤናችሁ ወሳኝ ስለሆነ ክትትል በጊዜ መጀመር አስፈላጊ መሆኑን ያስረዳል!! ይህ ከትንሿ ስሪንጅ💉 ያነሰ ቁመት ያለው የ 3 ወራት ዕድሜ ያለው ህፃን ልጅ [ፅንስ] ነው።

ልጁ ከማህፀን ውጭ የተፀነሰ ፅንስ [ectopic...]ሲሆን በቀዶ ህክምና የወጣ ልጅ ነው። በጊዜ ባይወጣ ኖሮ የእናትም የልጅም ህይወት ላይተርፍ ይችል ነበር ፤በየጊዜው የፅንስ ክትትል ማድረግ ዋና ጥቅሙ አንዱ ለዚህ ነው።

ከየት ተነስተን የት እንደ ደረስን ቆም ብለን ማየት እንችላለን፤ኩራት ለሰው ልጅ ፈፅሞ አይገባውም!

ፈጣሪ የፈለገውን እንደፈለገ አድርጎ መስራት ይችላል።

Eli Jah እንዳሰፈረው

27/08/2025

የእናቶችና የጨቅላ ሕፃናትን ሞት የመቀነስ የጤና ፖሊሲን አፈጻጸም ለማሻሻል የሚያስችል አጋዥ ስልጠና ማግኘታቸውን ሰልጣኞች ተናገሩ፡፡ (ወልድያ ከተማ)

በEngender Health አማራ ክልል ቅርንጫፍ ፕሮግራም ፊልድ ኦፊስ RMNCH+ ፕሮጀክት ለወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በእናቶችና ሕፃናት የሕክምና ዘርፍ ለተሰማሩ ሁሉም ባለሙያዎች የወላድ እናቶችን የድኅረ ወሊድ የደም መፍሰስን መከላከልና ማከም ትኩረት ያደረገ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

በዚህ ሥልጠና ከተሳተፉትና አስተያየታቸውን ካጋሩን መካከል በወልድያ ሆስፔታል የእናቶችና ሕጻናት ክፍል አስተባባሪ የሆኑት ካሳሁን ማርአበይ የድኅረ ወሊድ ደም መፍሰስ እናቶችን አንድም ለሞት ወይም ደግሞ ለረዝም ጊዜ በሆስፒታል በህክምና ድጋፍ እንዲቆዩ የሚያደረግ ከፍተኛ ችግር ነው፡፡ ይህን ችግር ለመፍታትም የድኅረ ወሊድን የደም መፍሰስ መጠንን የምንለካው በግምት ነበር፡፡ አሁን ግን Engender Health ፕሮግራም የፈሰሰውን የደም መጠን ግምታዊ ሥራ ያስቀረ የህክምና ቴክኖሎጅ ይዞ መጥቷል፡፡ ይህም ተገቢውን መድኃኒት በመስጠት የእናቶችንና የጨቅላ ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ የሚያስችል ከነበረው አሠራር አንድ ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ሌላኛዋ የሥልጠናው ተሰሳታፊና የሆስፒታሉ የዘርፉ ባለሙያ የሆኑት ወርቅነሽ ቢሰጥ ሥልጠናው የነበረንን ሙያ ማደስ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ነገሮችን ያገኘንበት ሥልጠና ነው፡፡ ካዋለድናት በኋላ እየደማች ያለችን እናት እንዴት አድርገን ማዳን እንዳለብን ከነበረን እውቀት ላይ አዳዲስ ሲስተሞችን አሳውቆናል ብለዋል፡፡

ባለሙያዋ አክለውም ሥልጠናው በአሳታፊነቱም ይለያል፡፡ ከአሁን በፊት የሚሰጡ ሥልጠናዎች ብዙ ጊዜ አንድ ወይም ሁለት ባለሙያ ተመርጦ ነበር የሚሰጠው፡፡ ይኽ ስልጠና ግን ሁሉንም የዘርፉ ባለሙያዎች ያሳተፈ በመሆኑ ለአተገባበር አያስቸግርም በማለት የሥልጠናውን አሳታፊነት አድንቀዋል፡፡

በEngender Health አማራ ክልል ቅርንጫፍ ፕሮግራም ፊልድ ኦፊስ RMNCH+ ፕሮጀክት ሲኒየር ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑትና ሥልጠናው የሰጡት አምባዬ ጥላሁን ፕሮጀክቱ የእናቶችንና ሕጻናትን ጤና አገልግሎት በማሻሻል ሞትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዛሬው ሥልጠናም በዓለም እንዲሁም በሀገራችን የመጀመሪያውና ቀዳሚው ለእናቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የድኅረ ወሊድ የደም መፍሰስ ሁሉም ባለሙያ ቀድሞ ለመከላከል፣ ለመለየትና አስተማማኝ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል ሥልጠና ነው ብለዋል የፕሮግራሙ አስተባባሪ፡፡

ለዚህ ፕሮግራም ውጤታማነትም ውስጣችንን በእናቶች ቦታ አድርገን ማሰብ አለብን፡፡ የእናቶች ጤና ትብብር ያስፈልገዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በየደረጃው ያለው የጤና ተቋማት መሪ እስከ ታችኛው አገልግሎት ሰጭ ባለሙያ ሁሉም መተባባር አለበት፡፡ የሰለጡኑ የሆስፒታል ባለሙያዎችም መሥራት ብቻ ሳይሆን በሥራቸው በሚገኙ ጤና ተቋማት ባለሙያዎችን ያገኙትን እውቀት ያጋሩ ሲሉ አቶ አምባየ አሳስበዋል፡፡

በሥልጠና መርሐ-ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ባልደረባ የሆኑት አቶ ይመር የሱፍ ሥልጠናው ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2030 የእናቶችንና የጨቅላ ሕጻናትን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀነስ ግብ አስተዋጽኦ ታላቅ ነው ብለዋል፡፡

Enigender Health Ethiopia PMNCH+ፕሮጀክት የ4 ዓመት ቆይታ ያለው፤ አማራ ክልልን ጨምሮ በ6 ክልሎችና በአጠቃላይ በዙር 900 አካባቢ የሚሆን ጤና ተቋማት የሚደግፍ፤ አሁን ላይ በአማራ ፕሮግራም ፌልድ ኦፊስ ሥር 189 ጤና ተቋማት በትግበ

በዛሬው ዕለት 04/08/2017 ዓ.ም የወልድያ አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ከአብክመ ጤና ቢሮ  ጋር በመተባበር   ከክላስተር ሆስፒታሎች ጋር የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት 4ኛው ዙር በመረጃ ...
13/04/2025

በዛሬው ዕለት 04/08/2017 ዓ.ም የወልድያ አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ከአብክመ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከክላስተር ሆስፒታሎች ጋር የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት 4ኛው ዙር በመረጃ ላይ የተመሰረተ የህክምና አሰጣጥ /EBC/ የ3ኛው ሩብ አመት የአፈፃፀም ግምገማ አድረጓል። በውይይቱም የሁሉም ሆስፒታል ስራ አስኪያጆች;ሜዲካል ዳይሬክተር:እቅድ ዝግጀትና የኳሊቲ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።
👉 የመወያያ ነጥቦችም :-
1,EHAQ -4th Cycle-EBC
2, EHSIG
3, Clinical Audit
4,SBFR
5,Diagnostic Service
6. Best Practice በአባል ሆስፒታሎችና በአስተባባሪ ሆስፒታሉ ሪፖርት ቀርቦ ጠንከር ያለ ውይይት ተካሂዷል። ውይይቱን የወልደያ አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ፍስሀ የኋላውና ሜዲካል ዳይሬክተሩ ዶር ቢሆን ደመወዝ የመሩት ሲሆን በውይይቱም እርስ በርስ የልምድ ልውውጥ የሚወሰድበት : የተሻሻሉ አፈፃፀሞች የታዩበት :እንደ ክላስተር የነበረው የግብአት ልውውጥ እንዲሁም የዋና ዋና አመላካቾች አፈፃፀም እያደጉ የመጡበትና የመረጃ አጠቃቀም የተሻሻለበት በመሆኑ ከዚህ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የየራሱን አሳይመንት እንዲወስድ ተደርጓል። በመጨረሻም
የክላስተር ተሳታፊዎች ብዙ ስራ እንደተሰሩ ገልፀው በጥንካሬ የተነሱ ስራዎች እንዳሉ ወስደን ነገር ግን በክፍተት የተነሱትን የድርጊት መርሀ-ግብር አውጥቶ መፍትሔዎችን በማስቀመጥ ለቀጣይ ከዚህ በበለጠ ስራ በጋራ እንደሚሰራ ተገልፆ ውይይቱ ተጠናቋል።🙏🙏🙏

Address

Woldia
Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when woldia comprehensive specialized hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category