APHI woldia Branch አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Woldia
  • APHI woldia Branch አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ

APHI woldia Branch አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ health institute

16/04/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

የስራ ቅጥር ማስታውቂያ
07/03/2026

የስራ ቅጥር ማስታውቂያ

06/02/2026
የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት  ወልዲያ ቅርንጫፍ  በተሻሻለው የአለማቀፍ የህክምና ላቦራቶሪ ጥራት ማስጠበቂያ  ስታንዳርድ (ISO 15189:2022) ላይ ያተኮረ ስልጠና  በወልዲያ ከተ...
17/12/2025

የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ በተሻሻለው የአለማቀፍ የህክምና ላቦራቶሪ ጥራት ማስጠበቂያ ስታንዳርድ (ISO 15189:2022) ላይ ያተኮረ ስልጠና በወልዲያ ከተማ በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ሰጠ።

የኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስማማው አመሸ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት በስልጠናው ፍሬያማ እውቀት ቀስማችሁ ስትንዳርዶችን ለመተግበር እና ጥራቱን የጠበቀ የላቦራቶሪ አግልግሎት ለማህበረሰቡ ማድረስን አላማ ማድረግና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠብቅ አሳስበዋል። የላቦራቶሪን ጥራትን ለማስጠበቅ ተቋማችን የተቻለዉን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ መልክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያም ከሰልጣኞች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ሰልጣኞቹም ይህንን አለም አቅፍ ስታንዳርድ መተግበርና የላቦራቶሪ ጥራትን በማስጠበቅ ትክክለኛ፡ ታማኝና ጊዜውን የጠበቀ የላቦራቶሪ ውጤት ማውጣት የሁላችንም ሃላፊነት ነው ብለዋል። አሰልጣኞቹ በበኩላቸው የሰለጠናችሁትን ተቋማችሁ ላይ ወደ ተግባር መለወጥ አለባችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ስልጠናው ከ02/042018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል
ለሕብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ!
05/04/2018 ዓ.ም

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ለወልድያ ቅርንጫፉ የአምቡላንስ ድጋፍ አደረገ።ወልዲያ:-ኅዳር 30/2018 ዓ/ም(ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን) የአማራ ክልል ጤና...
09/12/2025

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ለወልድያ ቅርንጫፉ የአምቡላንስ ድጋፍ አደረገ።

ወልዲያ:-ኅዳር 30/2018 ዓ/ም(ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የወልዲያ ቅርንጫፍን የሥራ እንቅስቃሴ ከቅርንጫፉ ሰረተኞች ጋር ጎብኝተዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ገስጥ ጥላሁን በጉብኝታቸው ወቅት በእቅድ ላይ ተመስራታችሁ ወደስራ መግባታችሁ የሚበረታታ ነው ብለው የሀብት አጠቃቃማችሁም ሰፊ ለውጥ የታየበትና በአነስተኛ ገንዘብ የተሻለ ስራ መስራታችሁ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ከዞኖች ጋር ያላችሁን ትስስርና ትብብር አጠናክራችሁ ቀጥሉ ያሉት ምክትል ኃላፊው የተቋሙን ችግር ወደፊት እየተነጋገርን እንድፈቱ ጥረት እናደርጋለን ብለዉ በዕለቱ 5 ሚሊዮን 316 ሺህ 484 ብር ወጭ የተደረገበትና አንቡላንስ ሲሉም ለቅርንጫፉ አስረክበዋል፡፡

በማኅበረሰቡ የሚከሰቱ የጤናና ጤና ነክ ችግሮችን በጥናትና ምርምር በመለየት የማኅበረሰቡን የጤና ችግር ለመፍታት በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወልድያ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሲስተር ሰላማዊት አያሌው ቅርንጫፉ በሰሜን ወሎ፣ በዋግኽምራ ዞን እና የወልዲያ ከተማን ጨምሮ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በችግር ውስጥም ሁነን የማኅበረሰቡን የጤና ችግር ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን ያሉት የቅርንጫፉ ዳይሬክተር ተቋሙ አሁን እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ይበልጥ ለማጠናከር በሰው ኃይልና በቁሳቁስ እንድሟላላቸውም ጠይቀዋል፡፡

የወልዲያ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዘላለም ጌታቸው በዚሁ ጉብኝት ተገኝተው የክልሉ ጤና ቢሮ በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ እያደረገልን ያለው ድጋፍ የሚመሰገን ነው ብለዉ በተቋሙ የሚታየውን የውሃ ችግር ለመፍታት እንደመምሪያ 10 ሺህ ሊትር ታንከር እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል፡፡

በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ በጤና እና ጤና ነክ ሥራዎች ላይ ምርምር በማድረግ ለውሳኔ ሰጭ አካል በማቅረብ፣ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮዓዊ የሚደርሱ የጤና አደጋዎችን ምላሽ በመስጠት እንዲሁም ጥራት ያለው የላቦራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወልዲያ ቅርንጫፍ በ2015 ስራ መጀመሩም ተገልጿል።

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶች
24/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶች

15/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንነት፣ መተላለፊያ መንገዶችና መከላከያ ዘዴዎች

ለሕብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመረጃ መረቦች ከታች ያሉ ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ዌብሳይት፡ http://www.aphi.gov.et/
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/HealthofInstitute
ቴሌግራም፡ https://t.me/anrsaphi
ዩቱዩብ፡ https://www.youtube.com
ትዊተር፡ APHI_anrs
ነፃ የስልክ መስመር፡ 6981

ለወረዳ  እና ለዞን TB officer ስለ ውጫዊ ጥራት ቁጥጥር  እና የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓት  የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሄደ።የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ ...
07/11/2025

ለወረዳ እና ለዞን TB officer ስለ ውጫዊ ጥራት ቁጥጥር እና የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሄደ።
የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ በስሩ ለሚገኙ የወረዳና ዞን ቲቢ ኦፊሰሮችን ሰብስቦ የውጫዊ ጥራት ቁጥጥር እና የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ቆይታ ያደረጉት ኦፊሰሮቹ ተቋሙ ይህንን የውይይት መድረክ በማዘጋጀቱ አመስግነው እያከናወናቸው ያሉ መጠነ ሰፊ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ወደፊት ስራዎችን አብረን ተቀናጅተን እንሰራለን የትሻለ ውጤትም እናመጣለን ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። ተሳታፊዎቹ አክለውም ጥራት ያለው የወባና የቲቢ ምርመራ ስርዓት እንዲኖር ባለሙያዎች ስልጠና ቢሰጣቸው፣ አፈጻጸማችንን በየሩብ አመቱ ብንገመግም ጥሩ ነው ብለውል።
በውይይቱ የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ ዋና ዳይሬክተር ሲ/ር ሰላማዊት አያሌው ተገኝተው በነበረው የውይይት መድረክ ለተሳታፊዎች ምስጋና አቅርበው ተገናኝቶ መወያየት ያሉብንን ክፍተቶች ለይተን ለቀጣይ ስራዎች የድርጊት መርሃ-ግብር/ action plan/ አውጥተን ወደ ስራ ለመግባት ይረዳናል ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም የውጭ ጥራት ቁጥጥር እና የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓትን ውጤታማ ለማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው ስለዚህ የሚለከተው አካል ተቀናጅቶ፣ በቁርጠኝነት፣ በመግባባትና በመመካከር የተሻለ ስራ መስራት አለብን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

28/10/2025
22/10/2025

3ኛው ዙር የፖሊዮ በሽታ (የልጅነት ልምሻ)መከላከያ ክትባት ዘመቻው ውጤታማ ኾኖ ተጠናቅቋል።

በዘመቻ ሲሰጥ የነበረው የፖሊዮ ክትባት ውጤታማ ኾኖ መጠናቀቁን በአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

‎በአማራ ክልል የፖሊዮ በሽታ በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ እና ጎንደር ከተማ አሥተዳደር በመገኘቱ ለወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ድረስ በዘመቻ ክትባት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

‎ክትባቱ በሽታው በተገኘባቸው እና አጎራባች በኾኑ አካባቢዎችም ተሰጥቷል፡፡ ጎንደር፣ ደብረ ታቦር፣ ባሕር ዳር እና ደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደሮች፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎጃም እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች ክትባቱ የተሰጠባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡
በእነዚህ ዞኖች በ58 ወረዳዎች ክትባቱ መሰጠቱን ከአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

‎በኢንስቲትዩቱ የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ቅኝት እና ምላሽ ቡድን አሥተባባሪ ፅጌረዳ አምሳሉ ክትባቱ በታቀደው ልክ መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

‎በክልሉ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች ለኾኑ ሕጻናት ክትባቱን ለመስጠት በዕቅድ ተይዞ 3 ሚሊዮን 591 ሺህ 778 ሕጻናት መከተባቸውን ገልጸዋል፡፡

‎የክትባት ዘመቻው ውጤታማ የኾነው ለክትባቱ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ በአግባቡ በመሠራቱ ነው ብለዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ለሥራው የሚኾኑ ኮሚቴዎችን ቀደም ብሎ በማዋቀር በየጊዜው እየተገመገመ በመከናወኑ እንደኾነ ነው የገለጹት፡፡

‎ለዘመቻ ሥራው አስፈላጊ ግብዓቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው በአግባቡ እንዲደርሱ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ የክትባት መድኃኒቶች ወደ ጤና ተቋማት በተገቢው ሁኔታ መድረሱንም ተናግረዋል፡፡
በክትባት ሥራው ላይ የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች፣ አሥተባባሪዎች እና ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላትም ቀደም ብሎ አስፈላጊው ሥልጠና መሰጠቱን አንስተዋል፡፡

‎በዘመቻው ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ አንዳንድ ወላጆች እና አሳዳጊዎች በግንዛቤ ችግር አናስከትብም የሚሉ ነበሩ፡፡ ይህንንም ባለሙያዎች የማስገንዘብ ሥራዎችን በመሥራት ልጆች እንዲከተቡ መደረጉን ነው የገለጹት፡፡

‎አሥተባባሪዋ የፖሊዮ ክትባት ለረጅም ዓመታት ሲሰጥ የቆየ በመኾኑ ኅብረተሰቡ ክትባት ሲሰጥ በፈቃደኝነት ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ፤ መረጃ ሲፈልጉም የጤና ባለሙያዎችን በመጠየቅ መረዳት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በፖሊዮ ክትባት ዘመቻው ትብብር ላደረጉ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ምጃው የአሚኮ ነው፡፡

ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም (ወልዲያ) የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ የተቀናጀ የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ።የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወ...
22/10/2025

ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም (ወልዲያ) የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ የተቀናጀ የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ።
የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ የተቀናጀ የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ። በስልጠናው ላይ ከሰሜን ወሎ፣ ከዋግህምራና ከወልዲያ ከተማ አስትዳደር የቲቢ ምርመራ( Gene Xpert sites) ከሚሰሩ የሆስፒታልና የጤና ጣቢያ ላቦራቶሪ ባለሙያዎች እንዲሁም ከዞን የቲቢ ኦፊሰርና ከፖስታ ቤት ተሳታፊዎች ነበሩ። ስልጠናው የሁለት ቀን ቆይታ የነበረው ሲሆን ሰልጣኞች በቆይታቸው ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኙበት ገልጸው የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓቱን በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸው በስራቸው ላይ ብዙ ችግሮዝም እንዳሉ አንስተዋል። በዋናነት ግን ለGene Xpert ማሽናችን UPS አለመኖርና የመብራት መቆራረጥ ለስራችን ትልቅ ተግዳሮት ፈጥሮብናል ብለዋል።
በማጠቃለያ መርሃግብሩ የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አስማማው አመሸ የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓቱን በተቀናጀ መንፈስ ሆነን ፣ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ተላብሰን፣ በቅንነትና የመረጃ አያያዝ ባህላችንን በማጠናከር ሁላችንም የተሰጠንን ሃላፊነት መወጣት አለብን ብለዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም ይህንን ስርዓት ለማጠናከር የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ፣ የሁሉም ዞን ኦፊሰሮች እና የፖስታ ቤት ተወካዮች አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when APHI woldia Branch አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share