Ayed Digital Healthcare

Ayed Digital Healthcare Let's digitalize our health system

08/08/2024
በአለም ዙሪያ በእድሜ የገፉ የህዝብ ብዛት መጨመር እና ወደኋላ የቀረ የጤና አጠባበቅ ስርዓቶች ምክንያት በጤና አጠባበቅ ላይ ቅልጥፍናን እና ጥራትን ማሻሻል አስቸኳይ ፍላጎት ሆኖዋል። የጤና ...
18/07/2024

በአለም ዙሪያ በእድሜ የገፉ የህዝብ ብዛት መጨመር እና ወደኋላ የቀረ የጤና አጠባበቅ ስርዓቶች ምክንያት በጤና አጠባበቅ ላይ ቅልጥፍናን እና ጥራትን ማሻሻል አስቸኳይ ፍላጎት ሆኖዋል።

የጤና አጠባበቅ ኢንዱስትሪው በመረጃ አሰባሰብ ላይ በማተኮር ለብዙ አሥርተ ዓመታት ዲጂታላይዜሽን ሲካሄድ ቆይቷል እና አሁን ደግሞ AIን በመጠቀም ከተሰበሰበው መረጃ ወሳኝ የሆኑ አመላካች ውጤቶች ማግኘት ተጀምሯል።

Generative AI የህክምናን ሸክም በመቀነስ ላይ ብዙ ስራ እየሰራ ይገኛል። በዚህ ወቅት በአለም ዙርያ በዚህ ጉዳይ በጣም ብዙ ምርምሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

Youtube
https://www.youtube.com/-digital-healthcare

ፒል ቦት - የሚዋጥ የኢንዶስኮፒ መመርመሪያ ሮቦትፒል ቦት በአፍ የሚወሰድ የመድኃኒት ኪኒን መጠን ያለው የኢንዶስኮፒ መመርመሪያ ሮቦት ሲሆን በጨጓራ እንዲሁም በአጠቃላይ የምግብ መፈጨት ሥርዓ...
15/07/2024

ፒል ቦት - የሚዋጥ የኢንዶስኮፒ መመርመሪያ ሮቦት
ፒል ቦት በአፍ የሚወሰድ የመድኃኒት ኪኒን መጠን ያለው የኢንዶስኮፒ መመርመሪያ ሮቦት ሲሆን በጨጓራ እንዲሁም በአጠቃላይ የምግብ መፈጨት ሥርዓት (Gastrointestinal) ላይ ምርመራ ለማድረግ ያስችላል። ኢንዲያትክስ በተባለ የሕክምና ቴክኖሎጂዎች አምራች ኩባንያ የተሰራው ይህ እጅግ አነስተኛ መመርመሪያ ሮቦት ካሜራዎች፣ ሴንሰሮች እና ገመድ አልባ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ ነው።

እንደ መድኃኒት የሚዋጠዉ ሮቦት ለ10 ደቂቃ በታካሚዉ ሆድ ቅኝት ያደርጋል፡፡ እንደ ኩባንያው መረጃ ሮቦቱ 13 ሚሊ ሜትር በ30 ሚሊ ሜትር መጠን ያለው ሲሆን ቪዲዮ የማስተላለፍ አቅሙም 2.3 ሜጋፒክስል በሰከንድ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ሮቦቱ የምርመራ ተግባሩን እንዳጠናቀቀም ተፈጥሯዊ ዑደትን ጠብቆ ከሰውነት ውስጥ ይወገዳል፡፡

በተለምዶ ኢንዶስኮፒ (EGD) በመባል የሚታወቀውን መመርመሪያ ማሽን ለመተካት የተሰራው ፒል ቦት ዶክተሮች ስማርት ስልክን በመጠቀም ምርመራ ማድረግ ያስችላቸዋል፡፡ በመሆኑም ወደ ሕክምና ቦታ መምጣት ለማይችሉ ታካሚዎች መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል።

የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የጤና እንክብካቤን ለማቅረብ የሚያስችለው የቴሌሜዲስን ቴክኖሎጂን ከኤ.አይ ጋር ያጣመረዉ ፒል ቦት የሆድ ካንሰርን የመሰሉ በሽታዎችን ለይቶ ለማወቅ ያግዛል።

ሮቦቱ ክሊኒካል ሙከራዎችን እያደረገ ሲሆን እንደ አውሮፓውያኑ በ2026 መጀመሪያ ላይ ለሽያጭ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኩባንያው መረጃ ያመለክታል፡፡

©️ EAII

Follow us be informed with the future
14/07/2024

Follow us be informed with the future

12/07/2024

ወጣት ነህ ወይስ አዛውንት ? የትኛውም ብትሆን ይህ መረጃ የግድ ያስፈልግሀል።

Address

Wolkite

Telephone

+952532098

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ayed Digital Healthcare posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram