Fennet Medium clinic, Wolkite

Fennet Medium clinic, Wolkite Fennet medium clinic, in Welkite well equipped and led by specialist Doctors

 በአቤም ማ/ጤ/አገልግሎት አክስዮን ስር ፌነት ክሊክ ወልቂጤ ትልማ፣ እንተጋገዝ በሚል ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ ባደረገ ጊዜ ይኸው 200,000 ብር በማበርከት አለሁ ወልቂጤን እናልማት ብሏል። ...
19/02/2025



በአቤም ማ/ጤ/አገልግሎት አክስዮን ስር ፌነት ክሊክ ወልቂጤ ትልማ፣ እንተጋገዝ በሚል ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ ባደረገ ጊዜ ይኸው 200,000 ብር በማበርከት አለሁ ወልቂጤን እናልማት ብሏል። በቀጣይም የከተማው እድገትን አንድ ደረጃ ከፍ የሚያስደርግ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል በመገንባት እና በጤናው ዘርፍ ሌሎች አገልጎሎቶች በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ይገልፃል።

እንደሚታወቀው ፌነት ቁጥር 2 በጉብሬ ክ/ከተማ Ethiochicken ፊት ለፊት ደረጃውን በጠበቀ ላቦራቶሪ ተደራጅቶ በስፔሻሊስት ሀኪሞች እየተመራ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል።

Abdulsemed Worku Nida
Tilahun Koyas
Riyad Ibrahim
Ibrahim Hussen
Aliy Rebi
Yirgalem Hailu

የመድኃኒት ደህንነት ማስጠንቀቂያየኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን  RELIEF የሚባል ሕገወጥ መድኃኒት (በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን  እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት ...
23/11/2024

የመድኃኒት ደህንነት ማስጠንቀቂያ

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን RELIEF የሚባል ሕገወጥ መድኃኒት (በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው ይገመታል) በኢትዮጵያ ገበያ እየተዘዋወሩ መሆኑን ተደርሶበታል።

ይህ መድኃኒት በሕጋዊ መንገድ በባለስልጣን መስሪያ ቤታችን ያልተመዘገበ በመሆኑ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ አይታወቅም።በተጨማሪም ፣ የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ተቅማጥ ፣ የሆድ ህመም ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ ድካም፤ የእይታ መዛባት፤ መፍዘዝ ፣ ራስ ምታት ፣ የቆዳ ሽፍታ ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመርና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የኩላሊት ጉዳትን ያጠቃልላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህንን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን መድኃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ እያሳሰብን መድኃኒቱን በአካባቢዎት ካገኙ በነጻ ስልክ ቁጥር 8482 ደውለው ለኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ባለስልጣን ወይም ለክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት እንዲጠቁሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።

  ለሥራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!   #በፌነት ክሊኒክ፤ ጉብሬ ቅርንጫፍ (ቁጥር 2):-ክሊኒካችን በቅርቡ በጉብርየ ፣ ወልቂጤ ለሚከፍተው ቅርንጫፍ ባሉት ክፍት መደቦች የተለያዩ ሰራተኞችን...
22/05/2024

ለሥራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!

#በፌነት ክሊኒክ፤ ጉብሬ ቅርንጫፍ (ቁጥር 2):-

ክሊኒካችን በቅርቡ በጉብርየ ፣ ወልቂጤ ለሚከፍተው ቅርንጫፍ ባሉት ክፍት መደቦች የተለያዩ ሰራተኞችን አወዳድሮ በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል፡፡በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ስራ ፈላጊዎች ከቀን 14/09/2016 እስከ ቀን 24/09/2016 ባሉት የስራ ቀናት ወልቂጤ በሚገኘው መስሪያ ቤታችን በአካል በመገኘት (የትምህርት ማስረጃቹ በመያዝ ) ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
1/ የስራ መደቡ መጠሪያ፤ የሂሳብ ባለሞያ
• የትምህርት ደረጃ፤ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ በአካውንቲንግ፤በኢኮኖሚክስ፤በማኔጅመንት ወይም ተያያዥነት ባላቸው የትምህርት መስኮች በዲፕሎማ/ዲግሪ የተመረቀ/ቀች
• የስራ ልምድ፤ 0 አመት
• የስራ ቦታ ፤ጉብሬ
• ፆታ፤አይለይም
• ደሞዝ፤ በስምምነት
• ብዛት፤1
• ከመንግስት መስሪያ ቤት ዋስ ማቅረብ የሚችል
• መሰረታዊ የኮምፒተር እውቀት ያለው
2/ የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ክሊኒካል ነርሲንግ
• የትምህርት ደረጃ፤ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ በነርሲንግ የትምህርት መስክ በዲግሪ የተመረቀ/ቀች
• የስራ ልምድ፤ 2 አመት እና ከዚያ በላይ
• የታደሰ ሞያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/ምትችል
• ደሞዝ፤ በስምምነት
• ስራ ቦታ ፤ ጉብሬ
• ብዛት ፤01
3/ ስራ መደቡ መጠሪያ፤ ላቦራቶሪ ቴክኒሻን/ቴክኖሎጂሰት
• የትምህርት ደረጃ፤ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ በላቦራቶሪ ቴክኒሻን/ቴክኖሎጂሰት ትምህርት በዲፕሎማ /በዲግሪ የተመረቀ/ቀች
• የስራ ልምድ፤ 2 አመት እና ከዚያ በላይ
• የታደሰ ሞያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/ምትችል
• ደሞዝ፤ በስምምነት
• ስራ ቦታ ፤ ጉብሬ
• ብዛት ፤02
4/ ስራ መደቡ መጠሪያ፤ የካርድ ክፍል ሰራተኛ
• የትምህርት ደረጃ፤ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ በኮምፒተር/አይቲ ትምህርት በዲፕሎማ የተመረቀ/ቀች
• የስራ ልምድ፤ 0 አመት እና ከዚያ በላይ
• ደሞዝ፤ በስምምነት
• ስራ ቦታ ፤ ጉብሬ
• ብዛት ፤02
• ፆታ፤ሴት
5/ ስራ መደቡ መጠሪያ፤ ረነር
• የትምርት ደረጃ፤10ኛ/12ኛ ክፍል ያጠናቀቀች
• ደሞዝ፤ በስምምነት
• ስራ ቦታ ፤ ጉብሬ
• ብዛት ፤01
• ፆታ፤ሴት
6/ ስራ መደቡ መጠሪያ፤ ጽዳት ሰራተኛ
• የትምርት ደረጃ፤8ኛ/10ኛ ክፍል ያጠናቀቀች
• ደሞዝ፤ በስምምነት
• ስራ ቦታ ፤ ጉብሬ
• ብዛት ፤02
• ፆታ፤ሴት
7/ ስራ መደቡ መጠሪያ፤ የጥበቃ ሰራተኛ (ብዛት 02)
• የትምርት ደረጃ፤10ኛ/12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ
• ደሞዝ፤በስምምነት
• እድሜው ከ25-40 አመት የሆነና ዋስ ማቅረብ የሚችል።

አድራሻችን:- ወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ/ቀይ መስቀል ፋርማሲ አጠገብ
ስልክ:- +251113659373

!!!

To all Muslim brothers and sisters across the globe, ❤❤❤❤!Abdulsemed Worku Nida
09/04/2024

To all Muslim brothers and sisters across the globe,
❤❤❤❤!
Abdulsemed Worku Nida

ሰላም ለውድ የፌነት ቤተሰቦች፤ከዚህ በፊት ከምነሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች በተጨማሪ ፣  #የሳይካትሪ፣  ፣  እንዲሁም  ፣  #የቆዳ እና   በየዘርፉ   ብቻ በተቋማችን በአዲስ መልኩ አጠ...
03/04/2024

ሰላም ለውድ የፌነት ቤተሰቦች፤
ከዚህ በፊት ከምነሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች በተጨማሪ
፣ #የሳይካትሪ፣ ፣ እንዲሁም ፣ #የቆዳ እና በየዘርፉ ብቻ በተቋማችን በአዲስ መልኩ አጠናክረን እየሰጠን መሆኑ ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው ።
ተቋማችን በሳምንት 7 ቀን/24 ሰኣት ክፍት ሆኖ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን በተጨማሪ ስፔሻሊቲዎች አገልግሎት ለማስጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑ እንገልፃለን።

!

"የህጻናት የደም ማነስ"- የደም ማነስ ምንድን ነው?የደም ማነስ ማለት የቀይ የደም ህዋስ ብዛት መቀንስ ሲሆን በተለይም የሄሞግሎቢን/ሄማቶክሪት ልኬት መጠን በላብራቶሪ ሲለካ ከእድሜ አቻ ህፃ...
06/08/2023

"የህጻናት የደም ማነስ"
- የደም ማነስ ምንድን ነው?

የደም ማነስ ማለት የቀይ የደም ህዋስ ብዛት መቀንስ ሲሆን በተለይም የሄሞግሎቢን/ሄማቶክሪት ልኬት መጠን በላብራቶሪ ሲለካ ከእድሜ አቻ ህፃናት ጋር ሲነፃፀር መጠኑ የቀነሰ ሆኖ ሲገኝ ነዉ።

- የደም ማነስ በህጻናት እድሜ
የደም ማነስ ህጻናት ላይ በጣም የተለመደ የህመም ምልክት ነው።

- የደም ማነስ ለምን ህጻናት ላይ ይከሰታል?
1. ህጻናት ፈጣን እድገት ስላላቸው አንጻራዊ እጥረት ያጋጥማል
2. ከእናት በጽንስ ጊዜ ከእትብት ያከማቹት የብረት ማእድን ከ4-6 ወር ጊዜ በኋላ የሚቀንስ መሆኑ
3. ለህጻናት በተለምዶ በቤት ውስጥ የሚጀመር ምግብ በቂ የብረት ማእድን የሌለው መሆን።
4. ያለ በቂ ግንዛቤ ተጨማሪ ምግብ መጀመር
5. ህጻናት እያደጉ ሲሄዱ የሰውነታቸው የብረት ማእድን ፍላጎት መጨመር
6. በተፈጥሮ የብረት ማእድን ከሰውነት ጋር ያለው ውህደት አነስተኛ መሆን።

የደም ማነስ የህመም ምልክት እንጅ ራሱን የቻለ ህመም አይደለም። መንስኤውም እንደ እድሜ ክልል የተለያየ መሆኑ ይሰመርበት። የህመም ምልክቶቹ እንደ በሽታው ክብደት ይለያያሉ። በመሰረቱ የህመም ምልክቶችን ለማሳየት መቅኔ፣ ጉበት እና ጡንቻ ውስጥ ያለው የብረት ማእድን እስኪቀንስ ድረስ ብዙ ሳምንታት የዘለቀ ጊዜ ይፈልጋል። ይህም ሰውነታችን የመጠባበቂያ የብረት ማእድን ስንቁ እስኪሟጠጥ ድረስ ከ2-3ወር የህመም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ።

በዚህም ምክንያት የደምን የልኬት መጠን ካልወሰድን ባለሙያው በቀላሉ የሚያውቅበት እና ወላጅም የሚጠረጥርበት አጋጣሚ አነስተኛ ነው። ሆኖም ይህንን ለመቅረፍ በተለይ ለደም ማነስ የተጋለጡ እስከ ሁለት ዓመት ያሉ ህጻናትን ቢያንስ ከ3-6 ወር ባለ የጊዜ ልዩነት ሙሉ የደም ቆጠራ (CBC) በማድረግ አስቀድሞ ማወቅ ይቻላል።

ሌላው ግን ለደም ማነስ አጋላጭ ምክንያት ላላቸው ህጻናት ክትትል በማድረግ የከፋ የደም ማነስ ሳይከሰት ማወቅ እና ማሳከም ይቻላል። ለደም ማነስ አጋላጭ የሆኑ ሁኔታዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

- የደም ማንስ ዋና መንስኤዎች
1. የቀይ ደም ህዋስ ምርት መቀነስ
2. የቀይ ደም ህዋስ ቶሎ ቶሎ መሞት
3. የደም መፍሰስ

- የደም ማነስ አይነቶች
፩. ብረት ማእድን አጠር ደም ማነስ
፪. በደም ህዋስ ቶሎ መሞት የሚከሰት ደም ማነስ
፫. ውልደታዊ ደም ማነስ፡ የቀይ ደም ህዋስ ቅርጽ መጠን እና ይዘት ከተለመደው ተፈጥሮ ውጭ መሆን
፬. የቀይ ደም ህዋስ ምርት አጠር ደም ማነስ
፭. የቀይ ደም ህዋስ ግዘፍ ደም ማነስ

- የደም ማነስ አጋላጭ ምክንያቶች
1.በጨቅላነት እድሜ
፩. ከእትብት የደም መፍሰስ
፪. ከወሊድ በፊት የእንግዴ ልጅ መድማት
፫. ሾተላይ
፬. የእናት እና የልጅ የደም አይነት አለመመሳሰል/የእናት ደም አይነት ኦ ሆኖ የጨቅላ ህጻን ደም ኤ ወይም ቢ ሲሆን
፭. የመወለጃ ጊዜው ሳይደርስ የተወለደ ጨቅላ ህፃን
፮. መንታ ከሆኑ ከአንድ ፅንስ ወደ ሌላኛው ፅንስ በደም ስር መወሳሰብ ምክንያት የደም መለጋገስ
፯. ተፈጥሯዊ የደም ቅርጽና መጠን መዛነፍ

2. በለጋነት እድሜ እና እስከ ሁለት አመት ድረስ አጋላጭ ምክንያቶች
፩. በእርግዝና ወቅት የእናት ብረት ማእድን ማነስ
፪. የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት
፫. መንትያ ህፃናት
፬. የብረት ማእድን ያነሰው ምግብ መመገብ
፭. በምግብ እጥረት የተጎዱ ህጻናት
፮. ረጅም ጊዜ የዘለቀ ውስጣዊ ህመም
፯. የደም ካንሰር፣ የመቅኔ ህመም
፰. ያልታወቀ ረጅም ጊዜ የዘለቀ የጨጓራ ቁስለት የአንጀት ቁስለት እና የምግብ ስርገትን የሚቀንሱ ህመሞች
፱. የላም ወተት አብዝቶ መጠቀም

- 3. ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናት ላይ የደም ማነስ አጋላጭ ሁኔታዎች/ መንስኤዎች
፩. በአደጋ የደም መፍሰስ
፪. በምግብ እጥረት መቀንጨር/የብረት ማእድን እጥረት
፫. ለረጅም ጊዜ የቆየ ውስጣዊ የሰውነት ህመም
፬. የደም ካንሰር፣ የመቅኔ ህመም
፭. ደም መጣጭ የአንጀት ተዋህስያን

- የደም ማነስ ስሜት እና ምልክቶች
ምልክቶች እንደ ደም ማነሱ መጠን የተለያዩ ሲሆኑ ከብዙ በጥቂቱ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ይመስላሉ።
1. የድካም ስሜት
2. የፊት ማላብ
3. የሰውነት መገርጣት እና መቀንጨር
4. የምግብ ፍላጎት መቀነስ
5. የልብ ምት መፍጠን
6.ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
7. የከፋ የደም ማነስ ሲኖር የሰውነት ማበጥ ሊኖር ይችላል።
8. የፀባይ መነጫነጭ
9. የእንቅልፍ መቀነስ
10. የራስ ምታት እና ማዞር

‐ የምርመራ አይነት
1. ሙሉ የደም ምርመራ
2. ምክንያት ተኮር ምርመራ
3. የደም ማነስ አይነትን ለማወቅ የሚረዳ ምርመራ
4. የመቅኔን ጤንነት ለማወቅ የሚደረግ ምርመራ

- የደም ማነስ ህክምና
ህክምናው እንደ ምክንያቶች የተለያየ ሲሆን።

እጅግ የቀነስ ከሆነ ደም በመለገስ እንዲስተካከል ይደረጋል። የደም ማነሱ መንስዔው የብረት ማእድን ወይም የፎሊክ አሲድ ዕጥረት ከሆነ የሚተካውን አስፈላጊ ማእድን በመስጠት ይስተካከላል። አጋላጭ ነገሮችን/ህመሞችን ማከም/ማቆም ይገባል።

- ስለ ደም ማነስ የተዛቡ እውነቶች
አንዳንዶች በተለምዶ ደም ማነስ የሰውነት የግፊት መጠን መቀነስ ይመስላቸዋል። ሌሎች ደግሞ ደም ማነስን ለማከም ቪምቶ ወይም ሚሪንዳ መጠቀም መፍትሔ ይመስላቸዋል።

- ደም ማነስን የመከላከያ መንገዶች

1. ያለ ቀናቸው ለተወለዱ እና ለደም ማነስ አጋላጭ ምክንያት ላለባቸው ህጻናት ጥብቅ ክትትል እያደረጉ ደማቸው እየታየ የብረት ማእድን እጥረት መከላከያ ፈሳሽ መድሃኒት እንዲወስዱ ማድረግ።

2. ከ4-6 ዎር እድሜ ያሉ ህጻናት የደም የሄሞግሎቢን ወይም ሄማቶክሪት መጠንን ማሰራት እና እጥረት ካለባቸው መድሃኒት እንዲውስዱ ማድረግ

3. ተጨማሪ ምግብ ሲጀመር በብረት እና መሰል ማእድናት እንዲበለጽግ ማድረግ

4.አንድ አመት ላልሞላው ህጻን የላም ወተት አለመስጠት። እንዲሁም የላም ወተት ሲጀምሩ በመጠን እና ልክ ማድረግ።

5. ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናት ባዶ እግር እንዳይሄዱ ማድረግ እና ከ3-6 ወር ልዩነት በመደበኛነት ጸረ ወስፋት ፈሳሽ መድሀኒት መስጠት።

6.ህጻናት የሚያድጉበትን አካባቢ ከአደጋ የነጻ ማድረግ።

7. የትንሹ አንጀት ቀዶ ህክምና ለተደረገለት ህጻን ወይም አጥቢ እናት ሙሉ ለሙሉ ከእንስሳት ተዋጽኦ የጸዳ ምግብ የምትመገብ ከሆነ ለህጻኑ የቫይታሚን ቢ 12 መተኪያ መድሀኒት መስጠት ያስፈልጋል! ከ@HakimEthio የተወሰደ!

!

    ህመም ወይንም ግላኮማ ምንድነው ?👉ግላኮማ ወይም በተለምዶ የዓይን ግፊት ህመም ተብሎ የሚጠራው የዓይን ህመም የዓይናችን ግፊት ከተለመደው በላይ በመጨመር መልዕክትን ከዓይናችን ወደ ኋለ...
11/07/2023


ህመም ወይንም ግላኮማ ምንድነው ?

👉ግላኮማ ወይም በተለምዶ የዓይን ግፊት ህመም ተብሎ የሚጠራው የዓይን ህመም የዓይናችን ግፊት ከተለመደው በላይ በመጨመር መልዕክትን ከዓይናችን ወደ ኋለኛው የአንጎላችን ክፍል (Occipital lobe) የሚያስተላልፈውን የዓይን ነርቭ (Optic nerve) በመጉዳት ሊመለስ ወደማይችል ዓይነስውርነት(irreversible blindness ) የሚዳርግ አደገኛ የዓይን ህመም ነው።

ግላኮማ ዓይነ-ስውርነትን በማምጣት ከዓይን ሞራ ህመም ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ይጠቀሳል። ግላኮማ በማነኛውም እድሜ ክልል፣ በጨቅላ ህፃናት ፣ በታዳጊዎች ፣ በአዋቂዎች እንዲሁም እድሜያቸው በገፋ ሰዎች ላይ ሊከሰት ይችላል።

በይበልጥ ለዚህ ህመም ተጋላጭ የሆኑት
👉እድሜያቸው ከ40ዓመት በላይ የሆኑ
👉 በቅርብ ዘመዶቻቸው (first degree relative) ማለትም በወላጅ አባት ወይም እናት:በደም ከሚተሳሰሩ እህት ወይም ወንድሞች መካከል የግላኮማ ህመም ወይም ምክነያቱ የልታወቀ ዓይነ ስዉርነት ካለ።

👉የቆየ የዓይን ኳስ ምት ወይም አደጋ ከነበረ
👉የተለያዩ የዓየይን ህመሞች ለምሳሌ የቆየና የልታከመ የዓይን ሞራ

👉ለተለያዩ ተጓዳኝ ህመሞች ተጠቂ ከሆኑ
👉የስኳር ህመም
👉 የደም ግፊት ህመም
👉 የልብ ህመም

👉ለረጅም ጊዜ steroid የሆኑ መድሐኒት የሚጠቀሙ ሰዎች። ለምሳሌ
👉የአስም ህመምተኞች
👉የመገጣጠሚያ ህመምተኞች

የግላኮማ ህመም ምልክቶች:-

ባጠቃላይ ሁለት ዓይነት የግላኮማ ህመሞች አሉ።
👉አጣዳፊ የዓይን ግፊት ህመም (Acute Glaucoma)
ይህ አይነቱ የዓይን ግፊት ህመም በወቅቱ እና በድንገተኛ ካልታከመ እይታችንን በሰዓታት እና በቀናት ውስጥ ሊነጥቀን ይችላል። አጣዳፊ የዓይን ግፊት በሚጨምርበት ወቅት የሚከተሉትን ምልክቶች ይከሰታሉ።
👉ከፍተኛ የሆነ የራስና የዓይን ህመም
👉የዓይን መቅላት
👉ብርሃን መፍራት
👉ማልቀስ፣መቆርቆር
👉የእይታ መቀነስ
👉ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ
👉እይታችን ላይ ቀስተደመና (halo) መታየተት

👉'ምልክት የሌለው'(Chronic glaucoma)
ይህ አይነቱ የዓይን ግፊት ህመም ምንም አይነት ምልክት የለለው፣ የዕይታ አድማሳችንን ከውጭ ወደ ውስጥ ቀስ በቀስ እያጠበበ የሚመጣና በመጨረሻም ማዕከላዊ የእይታ አድማስ የሚነጥቅ እና ሊመለስ የማይችል ዓይነ-ስውርነትን ያመጣል። በዚህ ባህሪዉ ይህ የግላኮማ አይነት ''ምልክት አልባ የዓይን ብርሀን ሌባ (silent thief of sight)' በመባል ይታወቃል።

የግላኮማ ህክምናው ምን ይመስላል?

👉የግላኮማ ህመም ህክምና መከላከልን መሰረት የደረገ ነው።ይህም ማለት በግላኮማ ህመም ምክንያት የተከሰተውን የእይታ ጉዳት መመለስ የማይቻል ሲሆን ነገር ግን የዓይናችንን ግፊት በተለያየ መንገዶች በመቀነስ ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን ተጨማሪ የዕይታ ጉዳት መከላከል /ማስቆም ነው።

እድሚያቸው ከ40አመት በላይ የሆነ እንዲሁም በቤተሰብ የዓይን ግፊት ታሪክ ያለበት ሰው የዓይን ግፊት ልኬት እና የዓይን ነርብ ጤንነት ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ይመከራል።

ታድያ ለዚህና መሠል የአይን ህመሞች መፍትሄ አለኝ ይላል::
በአይን እስፔሻሊስት ሀኪም ከተሟላ ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሳምንታት አስቆጥሯል፤ በርካቶችም ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል።

ፌነት ክሊኒክ!

 #ሰበር ዜና በፌነት ክሊኒክ  ( )ውድ የፌነት ክሊኒክ ቤተሰቦች፣ የተገልጋዮቻችንን ፍላጎት ለማሟላት በመትጋት የቆየ ዘወትር  #ሰኞ እና  #ሀሙስ  ከሰኣት ጀምሮ የተሟላ የአይን ህክምና አ...
05/06/2023

#ሰበር ዜና በፌነት ክሊኒክ
( )

ውድ የፌነት ክሊኒክ ቤተሰቦች፣ የተገልጋዮቻችንን ፍላጎት ለማሟላት በመትጋት የቆየ ዘወትር #ሰኞ እና #ሀሙስ ከሰኣት ጀምሮ የተሟላ የአይን ህክምና አገልግሎት መስጠት መጀመራችን ስናበስራቹ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው። ህክምናው ዘመኑ ባፈራቸው ዘመናዊ መሳርያዎች( እንደነ Slit Lamp...etc) እና በተሟላ ላቦራቶሪ የታገዘ፣ በOphtalmologist
የሚመራ ነው።
#የህክምና ቀንና ሰኣት:-
ዘወትር #ሰኞ እና #ሐሙስ ከሰኣት

አድራሻ:- ፌነት ክሊኒክ፣ ወልቂጤ።

!
Abdulsemed Worku Nida
Tilahun Koyas
Riyad Ibrahim
Yirgalem Hailu
Ibrahim Hussen
Aliy Rebi

 በክሊናካችን ተቋርጦ የነበረው /  አገልግሎት   ጀምሮ የምንጀምር ሲሆን ከነገ ጀምሮ   ቀናት   በ3D ከለር ዶፕለርኢኮካርድዮግራፊ ማሽን በመታገዝ   አገልግሎት መስጠት እንደጀመርን ለውድ...
26/04/2023


በክሊናካችን ተቋርጦ የነበረው
/ አገልግሎት ጀምሮ የምንጀምር ሲሆን ከነገ ጀምሮ ቀናት በ3D ከለር ዶፕለርኢኮካርድዮግራፊ ማሽን በመታገዝ አገልግሎት መስጠት እንደጀመርን ለውድ ደንበኞቻችን እናበስራለን።
Abdulsemed Worku Nida
Dr. Abdulsemed Worku Nida

!

Address

Wolkite
07

Telephone

+251911658074

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fennet Medium clinic, Wolkite posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Fennet Medium clinic, Wolkite:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram