Yaadama Mo'ata

Yaadama Mo'ata Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yaadama Mo'ata, AIDS Resource Center, Nekemte, London.

26/02/2025
Gudda Namaf Guddinii itti fufaa!!!! Jabadhaa Kabajamo Obbo Namarra!!!!
12/08/2024

Gudda Namaf Guddinii itti fufaa!!!! Jabadhaa Kabajamo Obbo Namarra!!!!

13/07/2024
ድሮም እኮ ባለቤት እንጂ ተከራይ ቤት አሳምሮ አያቅም ጉድ ነው አዲስ አበባ ።
13/07/2024

ድሮም እኮ ባለቤት እንጂ ተከራይ ቤት አሳምሮ አያቅም ጉድ ነው አዲስ አበባ ።

11/06/2024
07/06/2024

አፍንጫችንን ይዘን ያለፍንበትን ጎዳና አፋችንን ከፍተን አየነው።
አፈር ስሆን ይሄንን አለማድነቅ ይቻላል?
***
(ተስፋዬ ዘ ሸገር)

አዲስ አበባ ስሟ እንጂ መልኳ እኮ ሌላ ነበር። አሁን እንደ አዲስ አበባ ፒያሳ ለኑሮ የማይመች ለጤና መከራ የነበረ ቦታ ትጠቁሙኛላችሁ? ወዴት ወዴት የተሰራማ ስናደንቅ ካድሬነት አይደለም። ዱባይ ታምራለች የምንለው የንጉሡ ካድሬ ሆነን ነው እንዴ? ወደድንም ጠላንም ከተማዋ ለሚመጣው ትውልድ ምቹ ሆናለች። የሰሩ እጆች ታሪክ ያመሰግናቸዋል።

አፈር ስሆን አሁን ይሄንን አለማድነቅ ይቻላል? ትናንት ቦታውን ለሚያውቅ ሰው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊማር ክልል የሄደ ሰው መልሶ ሳይመጣ አልቆ የጠበቀው ፕሮጀክት እኮ ነው።

ማድነቅ የሚተናነቀን ሁሉንም በፖለቲካ መነፅር ስለምንመለከተው እኮ ነው። እንደሰውማ ብናየው ቱቦው እየገማ አላሳልፍ ያለን መንገድ ፏውንቴን ሲደንስበት በተደሰትን?

በልማት ኮሪደር ስራው ታሪካቸው ከተቀየረ አካባቢዎች አንዱ ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ ሙሐሙድ ሙዚቃ ቤት ያለው ጎዳና ነው። ሰንብቶ የመጣ ይሄ ሀገሬ ነው? ብሎ መጠየቁ አይቀርም።

ድሮ ድሮ ከገጠር የመጡ ሰዎች አዲስ አበባ ታደናግራቸዋለች ሲባል ሳቄ ይመጣል። ሀዋሳ እና ባህር ዳር ኒውዩርክ የሆኑባት ዋና ከተማ እኮ ናት። አስባችሁታል ከፎቁ ብዛት በስተቀረ መቀሌ ጫፍ ላይ የማትደርስ ከተማ ገጠሬውን አደናገረችው ሲባል።

መች ከተሜነት ነበራት፤ አንተዋወቅም እንዴ? ሽንት ቤት ሳይኖራት "መሽናት በሕግ ያስቀጣል" የሚል ለጥፋ አምስት ብር ስትሰበስብ አልኖረችም። ጋሽ አበራ ሞላ ላጽዳሽ ሲላት አላላገጠችም። የዛች ከተማ ሕይወት እኮ ነው የተቀየረው።

ከአራት ኪሎ እስከ ራስ መኮንን ያለውን ጎዳና አይቼዋለሁ የፈረሰችው ፒያሳ ተገንብታ ሳታልቅ አሁን እራሱ ድባቧ ሌላ ሆኗል። እሪ በከንቱ ስራ በሌሊቱ እየተባለ ሃያ አራት ሰዓት ሆ ተብሎበታል። መንግስት ይሄንን በሰላሙም በኢኮኖሚውም እንዲደግመው መመኘት እንጂ የልጆቻችን ከተማ ሲሰራ መቅናት ልክ አይደለም።

የሚጠላውን እንጥላ እንጂ የሚወደደውንማ መውደድ ነው። እንዲህ ባማረች ከተማ መኖር ምኑ ይጠላል? እንደውም ትዝ አለኝ ድሮ ድሮ የቆሻሻ ገንዳ እና የአትክልት ተራ ብስባሽ እያሳየ የተቀረፀ የሙዚቃ ክሊፕ ነበረን። ሙዚቃው ምን ይላል?
"አማረች አዲስ አማረች
የአፍሪቃ ህብረት መዲና ሆነች" ይገርማል እኮ።
አዲስ አበባ ስሟን እየመሰለች የመጣችውስ አሁን ነው? አሁንም ገና ምኑ ተነክቶ ገና ብዙ ስራ ይቀራል ግን ያንን መቀየር መጀመር የሚያስመሰግን ነው።

አንድ ጊዜ የአፍሪካ አንድነት ወደ ህብረት ተቀይሮ ዋና ከተማ ሲመረጥ ደርባን በተባለች የደቡብ አፍሪካ ከተማ ስብሰባ ተደረገ። የሊቢያው መሪ ጋዳፊ የህብረቱን መቀመጫ ወደ ትሪፖሊ መውሰድ ፈለጉ። የክርክራቸው አንድ ነጥብ የአዲስ አበባ ቆሻሻነት ነበር። ቆሻሻ ይፀዳል በሚል ሙግት የልባቸውን ተናግረው አቶ መለስ ዜናዊ የጋዳፊን ምኞት አከሰሙት። ይሁን እንጂ የአፍሪካ መዲናም ተብላ ንፁህ ነገር ይደፋሻል የተባለች እስኪመስል በዚያው ቀጠለች።

ፅዳትና ውበት የሚባል ቢሮ ነበረን። ፅዳት ግን ባህላችን አይመስልም መሃል ከተማው ቆሻሻ መጣያ ሆኖ ነበረ። አሁን ቆሻሻው ሲነሳ ሁሉንም እረሳነው። ከአትክልት ተራ እስከ አራዳ የትናንቱን መንገድ አስቡት። እውነቱን ነው ያ ዘፋኝ "የነበር ሲያወጉት ይመስላል ያልነበር" ያለው።

ዛሬ ቅርስ ውርስ የምንላቸው ሕንፃዎች በዘመኑ ለዘመኑ ሰው ቅንጦት እንጂ ተአምር አልነበሩም። ነገ ሁሉንም ይፈርዳል እስከ ነገ ግን በጥሩ ከተማ መኖራችንን እንቀጥላለን።

Address

Nekemte
London

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yaadama Mo'ata posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share