
03/09/2022
በቤት ውስጥ ጅን ስለመኖሩ ምልክቶች!
ከዶክተር አቡ ፈርሃን ጥናታዊ መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡
እናንተ ሰዎች ሆይ በቤቶቻችሁ ስር ጅኖችን በምታስተውሉ ወቅት የሶስት ቀን ማስጠንቀቅያ ስጧቸው ያም ሸይጧን ከሆነ ከቤት ውስጥ አይወጣም ሙእሚን ጅን ከሆነ ግን ይወጣል፡፡ በናንተም ውስጥ ድንበር አላፊዎችን አሏህ አይወድምና የተባለውን ነብያዊ ሃዲስ አስታውስ፡፡ አሏህ ለሁሉም እኩሊታ ነው፡፡ ሁሉንም በእኩል የሚዳኝ ፍትሃዊ ጌታህ ነው፡፡ ቤትህ ውስጥ ሲህር ካለ በስቃይህ ለይ ጅን ካለ ግን በነኚህ ለይ፡፡
ክፍል 2
ምልክቶች
1.የተቃጠለ ነገር ማሽተት፡፡ ምሳሌ ክብሪት ሲቃጠል አይነት ሽታዎችን በተለምዶ ቤት ውስጥ በብዛት ማሽተት፡፡
2.ድንገት የበሮች ብርግድ ብሎ መከፈት አልያም በሃይል መዘጋት (የንፋስ ዝውውር ሳይኖር፡፡)
3.የሰው ድፅ የሚመስሉ መጣራቶች አልያም መንሾካሾኮች መኖር፡፡
4.ቤት ውስጥ ከሌላው ግዜ የበለጠ ጭቅጭቅና ጥል መኖር፡፡ በቤተሰብ ውስጥ በየቀኑ ጥል ፈጣሪዎች ናቸው፡፡
5.ቤት ውስጥ አባወራ አልያም ቤት የሚያስተዳድረው ሰው ኪሳራ ውስጥ መግባት
6.ከኋላ የሚከተለን ያለ አካል እንዳለ ስሜት መሰማት፡፡ ከኋላ ከበድ ያለ ትንፋሽ መስማት፡፡
፡-በቤት ውስጥ ያለ ጅን አስከፊ ሲሆን
7.ሴቷ ሚስት ብታረግዝም ቶሎ ቶሎ ያስወርዳታል፡፡
8.ህፃናት ወይም ጨቅላዎች ባልታወቀ ምክንያት ቶሎ ይሞታሉ፡፡ አልያም ሰውነታቸው ይበላሻል፡፡
9.በቤት ውስጥ ጅኑ እንደ ጥቁር ውሻ ሁኖ መታየት አልያም ድመት ሁኖ መታየት ብሎም እባብና ታይቶ የማይታወቅ ትልቅ ሸረሪት ሆኖ ብቅ ብሎ መጥፋት ይጀምራል፡፡
10.ቤት ውስጥ ድንገተኛ አስደንጋጭ ነገሮች ያደርጋሉ፡፡ ከባባድና ሰው መጣል የማይችላቸውን እቃዎች ይጥላሉ ፍሪጅ ይጥላሉ፡፡ በሮችን በሙሉ ይከፍታሉ፡፡ ብሎም ጣራ ይገነጥላሉ፡፡ መስታዎቶችን ይሰብራሉ፡፡
ከዚህ አይነት ሲህሮች በአሏህ ሃይል እንጠበቃለን፡፡ ከሸይጧን ጭፍሮችም ሸር እንዲሁ! በርሶ ላይ ማንኛውም አይነት ህመሞች ሲኖሩ በሲህርና በአለማዊ በሽታዎች ሲጠቁ አሏህም ካለ በኢስላማዊ እውቀት ብቁ የሆኑ የሩቅያህ ዶክተሮችን አለማዊ የሜዲካል ዶክተሮችን የሳይካትሪስት ዶክተሮችን ብሎም የሃዲስ ምሩቆችን እና የሸሪአ ምሩቅ ምሁሮችን ወደሚያገኙበት ወደ ቀልብ ዶክተር ቻናል በማምራት ዶክተር ወይም ኡስታዝ ብለው በማናገር ህክምናዎን በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መንገድ ብቻ ያግኙ፡፡ ለሁላችሁም ከልብ አፊያን ተመኘሁ ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ!!
https://t.me/Qallbdoc