
05/04/2025
https://www.facebook.com/share/p/19wSEW4wnV/?mibextid=WC7FNe
አጭር የህይወት ታሪክ
(የቀጠለ.....)
ሆስፒታል ማቋቋም ብቻውን በዘርፉ ያለውን ችግር መቅረፍ እንደማይችል በማመን በርካታ የህክምና ባለ ሙያዎችን በራሳቸው /በዶ/ር ፍቅሩ/ ወጪ ስዊድን ድረስ በመላክ በልብ ህክምናው ስፔሻላይዝድ ያደረጉ እውቅ ሀኪሞችን በማፍራት የሰለጠነውን አለም የህክምና ሙያ ወደ ሀገር በማምጣት ለእውቀት ሽግግር ብርቱ ዋጋ ከፍለዋል። በዚህም በሰለጠነው አለም ብቻ ይሰጥ የነበረውን ውስብስብ የተባለ የልብ ህክምና ወደ ሀገራችን በማምጣት ጉልህ ሚና የተጫወቱ የሀገር ባለውለታ ናቸው, ካርዲዮሎጂስቱ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ፡፡ ለወትሮው ህክምናውን ፍለጋ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ውጪ ይደረግ የነበረውን ጉዞ በማስቀረት ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ሀገሪቱ ልታወጣ የምትችለውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት አሻራቸውን ያኖሩት ዶ/ር ፍቅሩ፤ በአዲስ ካርዲያክ የማይሰጡ የልብ ህክምናዎች የሚደረግበትን ታዝማ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ልዩ ህክምና ማዕከልንም በመመስረትና አሁን ለደረሰበት ደረጃ
በማብቃት ዛሬ በርካታ ህፃናትና ወጣቶችን በልብ ህክምና እጦት ምክንያት ከሚነጥቀው ሞት መታደግ የቻሉ ታላቅ የሃገር ባለውለታ ናቸው።በጥቁር አንበሳ የሚሠጠውን የልብ ህክምና ለማዘመን ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት ዶ/ር ፍቅሩ በተለያዩ ጊዜያት በውድ ዋጋ የሚገዙ አላቂ የህክምና መሳሪያዎችን በእርዳታ በማቅረብ በርካታ አስተዋፆ አበርክተዋል።የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲመሠረት በወቅቱ በነበሩት የጤና ሚኒስቴር ተመርጠው በተጣለባቸው ሃገራዊ ኃላፊነት መሠረት የግል የጤና ተቋማትን በማስተባበር ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዲሰበሰብ በማድረግ ደማቅ አሻራቸውንም አኑረዋል። በጦርነቱ ወቅት የተጎዱ ት/ቤቶችንና ተቋማትን ለማገዝ በሚደረግ ርብርብ ውስጥ ሰፊ አበርክቶ የነበራቸውም ታላቅ ሰው ነበሩ።''በሀገርና በህዝብ ቂም የለም'' የዶ/ር ፍቅሩ ፅኑ እምነት ነው።ለሃገራቸው ፅኑ ፍቅር ያላቸው ዶ/ር ፍቅሩ ባለፈው ስርዓት በተለያየ ወቅት ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ታድያ ስርዓተ ለውጡን ተከትሎ ከእስር ቤት ሲወጡ ዜግነት ወዳላቸው ስዊድን ሀገር ለህክምና ይጓዛሉ። በዛን ወቅት ተመልሰው አይመጡም ተብሎ ብዙ ሲናፈስ እርሳቸው ግን በጥቂት ሳምንታት ነበር ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የገቡት። 'ይሄ ሁሉ በደል ደርሶብዎ እንዴት ወደ ሀገርዎ ሊመለሱ ቻሉ?' ተብለው ሲጠየቁ ምላሻቸው አጭርና ግልፅ ነበር '' በሀገርና በህዝብ ቂም የለም" ነበር ምላሻቸው።
ላለፉት አስራ ዘጠኝ አመታት በኪራይ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውን አዲስ የልብ ህክምና በዘርፉ የሀገሪቱ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ከነበራቸው ጥልቅ ፍላጎት በመነሳት ለመኖሪያነት በገዙት መሬት ላይ ደረጃውን የጠበቀ ባለ ስምንት ወለል ህንፃ በመገንባት በቅርቡ ሆስፒታሉን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር ሂደት ላይ ነበሩ።
ነገር ግን ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በስዊድን ሀገር ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በተወለዱ በ74 አመታቸው ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።
ካርዲዮሎጂስት ዶ/ር ፍቅሩ ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት እንዲሁም የአራት የልጅ ልጆች አያት ነበሩ።
የዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የቀብር ስነ-ስርዓት በስዊድን ሀገር የሚፈፀም ሲሆን በሀገር ውስጥ ሀዘን መካፈል ለሚፈልጉ አዲስ አበባ ጃክሮስ እግዚአብሔር አብ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ - ከቪዥን ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መድረስ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ቤተሰቦቻቸው፣አዲስ የልብ ህክምና ሆስፒታል ማኔጅመንትና ሰራተኞች፤ታዝማ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ልዩ ህክምና ማዕከል ማኔጅመንትና ሰራተኞች ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ