02/16/2026
እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም ደስምአለን መዝ 126:3
የእርቅና የአንድነት የእንካን ደስ አላችሁ መልእክት::
የተከበራችሁ የቤተክርስቲያን መሪዎች የተከበራችሁ የቤተክርስቲያን ምእመናን እንዲሁም በፍሎሪዳ ጃክሰንቪል የምትኖሩ ቅዱሳን በሙሉ እግዚአብሔር ለዚህ ታላቅ የደስታ ቀን ስለአደረሰን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን እንካን ደስ አላችሁ እንካን ደስ አለን ::
ላለፉት ጥቂት የማይባሉ አመታት በከተማችን ባለች የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በጃክሰንቪል በወቅቱ በነበሩ በፓስተር ሚካኤል አረጋ እና በመሪዎች (በሽማግሌዎች) እንዲሁም በህዝብ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በመሀከል ትልቅ ክፍተት እና መለያየት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወቃል ::
ዛሬ በአምላካችን በእግዚአብሔር ቸርነትና እርዳታ ንዲሁም በሁለቱም ቤተክርስቲያን መሪዎች በኩል በታየው ታዛዥነት እና የፍቅር ልብ ,የይቅርታ መንፈስ በአካል በመገናኘት በመነጋገር እንድንኖርለት እና እንድንሞትለት በእጃችን ለተሰጠን ወንጌል ቅድሚያ በመስጠት እርስ በእርስ በፍፁም ይቅርታ እና በእውነተኛ ወንድማዊ ፍቅር በመተቃቀፍ ችግሩ እንዲፈታ ተደርጎዋል::
ስለሆነም ይህ የእርቅ መዕድ ወደ ግባኤ ወደ ቤተክርስትያን እንዲደርስ እና ቅዱሳን ሁሉ የዝህ ደስታ ተካፋዮች እንድትሆኑ ብሎም ለከተማችንም ታላቅ የምስራች አዋጅ ለጠላታችንም ለሴጣን ውድቀት እንዲሆን ይህን ብሥራት ለማብሰር በፊታችሁ ቆመዋል (ናል):: በመቀጠልም በቤተክርስትያን በተፈጠረው ችግር ምክንያት ልባችሁ ያዘነ የእግዚአብሔር ቤት ቅናት ግድ የሚላችሁን ሁሉ በጌታ ፍቅር ይቅርታ እንጠይቃለን::
የተከበራችሁ መሪዎቻችን
* ፓስተር ሚኪ አረጋ
* መባ ይልማ
* ቸርነት ዳና
* ሻዎል እጅጉ
* አዎት ፈትውር
*ተመስገን አበራ
ስለአሳያችሀን ታላቅ ትህትና እና እሺ ባይነት እግዚአብሔር እምላካችን ዘመናችሁን አገልግሎታችሁን ይባርክ እያልን ይህ ተግባራችሁ ለይቅርታ ለሰላም ለፍቅር ያላችሁ ትኩረት ልበ ክርስቶስ እንዳላችሁ አስገንዝቦናል :: እንዲሁም ይብዛም ይነስም በኃላችሁ ለሚከተላችሁ ትውልድ የማይጠፋ ደማቅ አሻራ ያለው እና የምትመሰሉ ምሳሌዎች እንድትሆ hiኑ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን የሚያጠራጥር አይደለም::
ስለሆነም እግዚአብሔር በሰጠን ቀጣይ ዘመን እና እድሜ እጅ ለእጅ በመያያዝ
ለእግዚአብሔር መንግስት እንደሚሰራ ሰው የውንጌል ማህበርተኛ በመሆን እግዚአብሔር በሰጠን ራእይ በየቤተክርስትያናችን በመትጋት ከተማችንን ጃክሰንቪልን በወንጌል ለመጠቅለል የምንሰራበት ዘመንያድርግልን ::
እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስለአገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለላቸው የደረጋችሁትን ስራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ አመፀኛ አይደለምና:: ዕብ 6:10
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
አሜን!