Ethio Hakim

Ethio Hakim ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት ፔጃችንን like እና follow በማድረግ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!

👉🏻ጥያቄያችን ከህግ አንፃር፤ ሕጋዊ ስራ የማቆም አድማ vs ሕገ ወጥ ስራ የማቆም አድማ።የጤና ባለሞያዎች  ስራ የማቆም አድማ በህግ የማያስጠይቅ ስለመሆኑ ይናገራል።ጥያቄያችን በተሰጠው 2 ወ...
13/08/2025

👉🏻ጥያቄያችን ከህግ አንፃር፤ ሕጋዊ ስራ የማቆም አድማ vs ሕገ ወጥ ስራ የማቆም አድማ።

የጤና ባለሞያዎች ስራ የማቆም አድማ በህግ የማያስጠይቅ ስለመሆኑ ይናገራል።

ጥያቄያችን በተሰጠው 2 ወር ውስጥ ካልተመለሰ የስራ አድማችን ይቀጥላል። ስለዚህ የስራ አድማ በሚደረግበት ጊዜ በህግ ያስጠይቀናል ወይስ በምን አይነት መልኩ አድማ ብናደርግ አያስጠይቀንም የሚለውን ከህግ ባለሙያው።

👉የህግ ባለሞያው
👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻

👉🏻ጥያቄያችን ከህግ አንፃር፤ጥያቄያችን በተሰጠው 2 ወር ውስጥ ካልተመለሰ የስራ አድማችን ይቀጥላል። ስለዚህ የስራ አድማ በሚደረግበት ጊዜ በህግ ያስጠይቀናል ወይስ በምን አይነት መ...

]☞ #የኩላሊት እና   ኢንፌክሽን!❞✅የሽንት ቧንቧ ከኩላሊታችን እስከ ሽንት መዉጫ ያሉት ሁሉንም የሽንት ቱቦዎች እና ማጠራቀሚያወችን የሚያካትት ሲሆን የሚይዛቸዉ➡️ኩላሊትን፣➡️ዩሬተር (ከኩ...
13/08/2025

]☞ #የኩላሊት እና ኢንፌክሽን!❞

✅የሽንት ቧንቧ ከኩላሊታችን እስከ ሽንት መዉጫ ያሉት ሁሉንም የሽንት ቱቦዎች እና ማጠራቀሚያወችን የሚያካትት ሲሆን የሚይዛቸዉ
➡️ኩላሊትን፣
➡️ዩሬተር (ከኩላሊት ወደ ሽንት ማጠራቀሚያ ፊኛ ሽንት የሚያስተላልፍ ቱቦ ነዉ)፣
➡️የሽንት ማጠራቀሚያ ፊኛ እና
➡️ዩሬተር (የዉሃ ሽንት ማስወገጃ ቱቦ) ናቸዉ።
•---•---•

?
✅የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የምንለው ከኩላሊት እስከ የውሃ ሽንት ማስወገጃ ጫፍ ድረስ የሚከሰተውን የኢንፌክሽን ዓይነት ነው፡፡
በአብዛኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚያጠቃው የውሃ ሽንት የሚከማችበት የሽንት ፊኛ በመባል የሚታወቀውን የአካል ክፍላችንን ነው፡፡
•---•---•

?
✅በአብዘሀኛዉ ወጣት ሴቶች ላይ የሚከሰት ነዉ። ምክንያቱም በተፈጥሮ የሴቶች ሽንት ማስወገጃ ቱቦ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር በማጠሩ ነዉ። ስለዚህ ከወንዶች ይልቅ ተጠቂነታቸው እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በሽታን የመከላከል አቅማቸው የቀነሰ እንደ የስኳር ሕመምተኞች እና እርጉዝ ሴቶች ላይም በብዛት ይከሰታል፡፡
•---•---•

?
✅ባክቴሪያ ከሽንት ማስወገጃ ጫፍ ወደላይኛው የሽንት ቧንቧ አካል ሲገባ እና ይህም ሊከሰት የሚችለው በአካባቢው የሚገኘው የሠገራ ማስወጫ በባክቴሪያ የተበከለ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም
➡️በምንፀዳዳበት ጊዜ የግል ንጽህናን ባለመጠበቅ (ባለመታጠብ)፣
➡️በግብረሥጋ ግንኙነት ጊዜ እና
➡️በተለያየ ምክንያት ሽንትን ለማስወገድ የሽንት ቱቦ በሚገባበት ወቅት ሊከሰት ይችላል፡፡

✅ሌለኛዉ መከሰቻ መንገድ ደግሞ በደም ስር የሚዘዋወሩ ባክቴሪያወች በተበከለዉ ደም አማካኝነት ኩላሊት ጋ ሲደርሱና ኢንፌክሽን ሲፈጥሩ ነዉ፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች ኢንፌክሽን ለመፍጠር የሚያፋጥኑ ነገሮች የኩላሊት ጠጠር እና የፕሮስቴት እጢ ያሉት ሕመሞች ተፈጥሮአዊ የሆነውን የውሃ ሽንት አወጋገድን በማስተጓጎል ወይም በመከልከል ለባክሪቴያዎቹ መራባት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ለኢንፌክሽን ሊዳርጉ ይችላሉ፡፡ በደም ውስጥ የሚገኝ ባክቴሪያም ይህንን ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል፡፡
•---•---•

?
➡️የውሃ ሽንት በምንሳወግድበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት መሰማት፣
➡️የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት፣
➡️ከእንብርት በታች የሕመም ስሜት መሰማት፣
➡️ደም የቀላቀለ ወይንም መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት መኖር፣
➡️ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ስሜት መሰማት፣
➡️የማቅለሽለሽ ስሜትና ማስመለስ ናቸው

✅እነዚህ ምልክቶች በተለይ የስኳር ሕመምተኛ ፣ እርጉዝ ሴት ፣ የኩላሊት ሕመም ተጠቂ የሆኑ እና በእድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ከተከሰቱ ጉዳታቸዉ የከፋ ስለሆነ ጊዜ ሳይሰጡ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ያስፈልጋል፡፡
•---•---•

?
➡️በብዛት ፈሳሽ መውሰድ ባክቴሪያ በሽንት ቧንቧ ውስጥ እንዳይቀመጥ በማድረግ ይከላከላል፣
➡️ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ እና ከተፀዳዱ በኋላ የግል ንጽሕናን መጠበቅ እና
➡️ምልክቶቹ ከተከሰቱ ፈጥነዉ አካባቢዎ በሚገኝ የህክምና ማዕከል መታከም ነዉ።

___________
ሀኪም መረጃ!!

••●◉
ከወደዱት ፔጃችንን & ያድርጉ!
🔎fb.me/Hakim.Mereja🔍

••●◉
#በተጨማሪም በቴሌግራም ቻናላችን ይከታተሉን
👉 https://t.me/joinchat/RaXORKxvrnU5M2Q0

ቲክቶከር ወገኔ አበበን የማያውቅ የለም። የሀኪሞች ድምፅ በመሆን video በመሥራቱ ምክንያት በወላይታ ሶዶ እስር ቤት ነው። መንግስት ለኛ ድምፅ የሆኑን በሙሉ በማሰር ድምፃችንን ለማፈን ብዙ...
12/08/2025

ቲክቶከር ወገኔ አበበን የማያውቅ የለም። የሀኪሞች ድምፅ በመሆን video በመሥራቱ ምክንያት በወላይታ ሶዶ እስር ቤት ነው። መንግስት ለኛ ድምፅ የሆኑን በሙሉ በማሰር ድምፃችንን ለማፈን ብዙ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

ሁሉም ሸር በማድረግ ለወንድማችን ድምፅ እንሁን። ከጎናችን ለነበሩ ሁሉ ድምፅ ለሆኑን ሁሉ ከጎናቸው መሆን ግደታችን ነው። ይህም አንዱ የትግላችን አካል ነው።

ሸር ይደረግ።

የሴት ብልት ፈሳሽ፡ ማወቅ የሚገባዎ ጠቃሚ መረጃ 🌸የሴት ብልት ፈሳሽ አብዛኛውን ጊዜ የጤናማነት ምልክት እንጂ የችግር አይደለም። ሰውነታችን ብልትን ለማፅዳት፣ እርጥበት ለመስጠት እና ከኢንፌ...
12/08/2025

የሴት ብልት ፈሳሽ፡ ማወቅ የሚገባዎ ጠቃሚ መረጃ 🌸

የሴት ብልት ፈሳሽ አብዛኛውን ጊዜ የጤናማነት ምልክት እንጂ የችግር አይደለም። ሰውነታችን ብልትን ለማፅዳት፣ እርጥበት ለመስጠት እና ከኢንፌክሽን ለመከላከል የሚጠቀምበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የፈሳሹ ቀለም፣ ሽታ ወይም መጠን መቀየር የጤና እክል ምልክት ሊሆን ይችላል።

የሴት ብልት ፈሳሽ ከማህጸን ጫፍ (cervix) እና ከብልት ግድግዳዎች (vaginal walls) የሚመነጭ የንፋጭ እና የፈሳሽ ድብልቅ ነው። ዋና ስራው የሞቱ ሴሎችን እና ባክቴሪያዎችን በማስወገድ ብልትን ንጹህ እና ጤናማ ማድረግ ነው።

የፈሳሽ አይነቶች እና ባህሪያት (Classification and Characteristics)

ፈሳሽን በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች መክፈል እንችላለን፦

✅ ጤናማ (የተለመደ) ፈሳሽ

ይህ ፈሳሽ ሰውነትዎ በትክክል እየሰራ መሆኑን ያሳያል። ባህሪያቱ፦

• ቀለም: ነጭ ወይም ወተት መሰል ነጭ ሊሆን ይችላል።
• ሽታ: ምንም አይነት መጥፎ ሽታ የለውም ወይም በጣም ቀለል ያለ ሽታ አለው።
• መጠን: እንደ ወር አበባ ኡደትዎ ይለያያል። ለምሳሌ፣ እንቁላል በሚመረትበት ጊዜ (ovulation) ላይ ቀጭን፣ ተለጣጭ እና እንደ ጥሬ እንቁላል ነጭ ክፍል ይሆናል።
• ስሜት: ማሳከክ፣ ማቃጠል ወይም ምቾት ማጣት አያስከትልም።

❎ ጤናማ ያልሆነ (ያልተለመደ) ፈሳሽ

ይህ አይነቱ ፈሳሽ የኢንፌክሽን ወይም የሌላ የጤና ችግር ምልክት ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ይፈልጋል።

የጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ ምልክቶች (Symptoms of Abnormal Discharge)

የሚከተሉት ምልክቶች ከታዩ የጤና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል፦

• የቀለም ለውጥ: ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ግራጫ ወይም ደም የቀላቀለ መሆን።
• የሽታ ለውጥ: እንደ ዓሳ ያለ መጥፎ (አስቀያሚ) ሽታ መኖር።
• የይዘት ለውጥ: በጣም መወፈር (እንደ ጎጆ አይብ መምሰል) ወይም አረፋማ መሆን።

ተጨማሪ ምልክቶች:
• በብልት አካባቢ ማሳከክ ወይም ማቃጠል።
• የብልት መቅላትና ማበጥ።
• በሽንት ጊዜ ወይም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ህመም መሰማት።
• የሆድ ወይም የዳሌ ህመም።

ሊሆኑ የሚችሉ መንስኤዎች (Possible Causes)

ያልተለመደ ፈሳሽ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦

የእርሾ ኢንፌክሽን (Yeast Infection / Candidiasis):

• ምልክት: ወፍራም፣ ነጭ፣ እንደ እርጎ ወይም የጎጆ አይብ ያለ ፈሳሽ እና ከባድ ማሳከክ።
• መንስኤ: በብልት ውስጥ ያሉ "ካንዲዳ" የተባሉ ፈንገሶች ከልክ በላይ መራባት።

ባክቴሪያል ቫጃይኖሲስ (Bacterial Vaginosis):

• ምልክት: ግራጫማ ወይም ነጭ፣ ቀጭን ፈሳሽ እና ጠንካራ የዓሳ ሽታ (በተለይ ከግንኙነት በኋላ)።
• መንስኤ: በብልት ውስጥ ባሉ "ጥሩ" እና "መጥፎ" ባክቴሪያዎች መካከል ያለው ሚዛን መዛባት።

ትሪኮሞኒያሲስ (Trichomoniasis):

• ምልክት: ቢጫ ወይም አረንጓዴ፣ አረፋማ እና መጥፎ ሽታ ያለው ፈሳሽ። ማሳከክ እና ህመምም አለው።
• መንስኤ: በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ፓራሳይት (ጥገኛ ተውሳክ) ነው።

ሌሎች ምክንያቶች:

• በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ሌሎች በሽታዎች (ለምሳሌ፡ ጨብጥ፣ ክላሚዲያ)።
• የማህጸን ጫፍ ብግነት (Cervicitis)።
• ለሳሙና፣ ለሎሽን ወይም ለኮንዶም አለርጂክ መሆን።
• የተረሳ ታምፖን (tampon)።

ህክምና (Treatment)

⚠️ ማስጠንቀቂያ: ምልክቶችን አይተው በራስዎ ህክምና አይጀምሩ!

ትክክለኛውን ህክምና ለማግኘት በመጀመሪያ መንስኤውን ማወቅ ያስፈልጋል።

ሐኪም ያማክሩ: የጤና ባለሙያ የፈሳሹን ናሙና በመውሰድ ወይም ምርመራ በማድረግ ትክክለኛውን መንስኤ ይለያል።

መድሃኒት:

ለእርሾ ኢንፌክሽን ፀረ-ፈንገስ (antifungal) ክሬሞች ወይም ኪኒኖች ይታዘዛሉ።

ለባክቴሪያል ቫጃይኖሲስ እና ትሪኮሞኒያሲስ አንቲባዮቲክ (antibiotic) ኪኒኖች ወይም ጄሎች ይታዘዛሉ።

ህክምናውን መጨረስ: ሐኪምዎ ያዘዘልዎትን መድሃኒት ምልክቶቹ ቢጠፉም እንኳን ሙሉ በሙሉ ወስደው ይጨርሱ።

6. የመከላከያ መንገዶች (Prevention Mechanisms)

ጤናማ የብልት ፈሳሽን ለመጠበቅ እና ኢንፌክሽንን ለመከላከል የሚከተሉትን ቀላል መንገዶች መተግበር ይችላሉ፦

🌬️ የጥጥ የውስጥ ሱሪዎችን መልበስ: ሰው ሰራሽ ከሆኑ ልብሶች ይልቅ አየር የሚያስገቡ የጥጥ የውስጥ ሱሪዎችን መጠቀም ይመረጣል።

💧 ትክክለኛ ንፅህና: የብልት አካባቢን በንጹህ ውሃ ወይም በጣም ለስላሳ (ሽታ በሌለው) ሳሙና ብቻ ማጠብ። ከፊት ወደ ኋላ ማጽዳት/መጥረግ።

❌ ዶሺንግን (Douching) ማስወገድ: የብልትን ውስጠኛ ክፍል በውሃ ወይም በሌላ ፈሳሽ ማጠብ ተፈጥሯዊ የባክቴሪያ ሚዛንን ስለሚያዛባ ለኢንፌክሽን ያጋልጣል።

🌿 ከኬሚካሎች መራቅ: ሽታ ያላቸው ሳሙናዎችን፣ ፓዶችን፣ ስፕሬዮችን እና ሎሽኖችን ከመጠቀም መቆጠብ።

👫 ጥንቃቄ የተሞላበት ግንኙነት: ኮንዶም መጠቀም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ይጠብቃል።

👖 ጠባብ ልብሶችን መቀነስ: በጣም ጠባብ የሆኑ ሱሪዎች ሙቀት እና እርጥበት በመፍጠር ለኢንፌክሽን ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ።

ሰውነትዎ የሚሰጥዎትን ምልክት ማዳመጥ ብልህነት ነው። ስጋት ወይም ጥያቄ ካለዎት የጤና ባለሙያን ለማማከር በፍጹም አያመንቱ::

ከዚህ መረጃ ጋር ተያይዞ ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ በቻናላችን መጠየቅ እና በባለሙያ ምላሽ የምታገኙ መሆኑን እንገልፃለን!!

Ethio Hakim

አኗኗራችን የኩላሊታችንን ጤና ሊጎዳ እንደሚችል ያውቃሉ?እነዚህን ጥንቃቄዎች በመውሰድ የኩላሊታችንን ጤና መጠበቅ እንችላለን◈ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ለሃኪም ሳያማክሩ በተደጋጋሚ ይወስዳ...
12/08/2025

አኗኗራችን የኩላሊታችንን ጤና ሊጎዳ እንደሚችል ያውቃሉ?

እነዚህን ጥንቃቄዎች በመውሰድ የኩላሊታችንን ጤና መጠበቅ እንችላለን

◈ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ለሃኪም ሳያማክሩ በተደጋጋሚ ይወስዳሉ?

በተለይ NSAIDS የተባሉት እንደነ ኢቡፕሮፊን እና ዳይክሎፌናክ ያሉ የህመም ማስታገሻዎችን ያለ ሃኪም ትእዛዝ ደጋግመው የሚወስዱ ከሆነ ኩላሊትዎን እየጎዱ ስለሆነ በቶሎ ሊቆጠቡ እና ሃኪም ሊያማክሩ ይገባል

◈ ጨው አብዝተው ይመገባሉ?

ጨው ገበታን ያጣፍጣል ለጤናም ይጠቅማል። ጨውን አብዝቶ መጠቀም ግን ለኩላሊት ህመም የመጋለጥ እድልዎትን ይጨምራል

◈ የታሸጉ ምግቦችን ያበዛሉ?

የታሸጉ ምግቦች ኩላሊትን ሊጎዱ የሚችሉ ኬሚካሎችን ይይዛሉ እናም የታሸጉ ምግቦችን ባለማብዛት ተጋላጭነትዎን ይቀንሱ

◈ ውሃ በበቂ ሁኔታ አይጠጡም ወይም ሽንትዎትን ቶሎ አይሸኑም?

በተለይ የስራ ሁኔታዎ ለጸሃይ የተጋለጠ፣ ውሃ እና መሸዳጃ ቤት በቀላሉ የማያገኙበት ከሆነ ሊጠነቀቁ ይገባል። በቀን ውስጥ ቢያንስ ከ1.5 እስከ 2 ሊትር ዉሃ መጠጣት ይመከራል

◈ እንቅልፍዎን በበቂ ሁኔታ አይተኙም?

አዎ! እንቅልፍም ከኩላሊት ይገኛል። በቂ እንቅልፍ ካልተኙ ኩላሊትዎ በቂ እረፍት ባለማግኘት ይጎዳል

◈ ስጋ መመገብ ያበዛሉ?

በስጋ ውስጥ ብዙ ፕሮቲን ይገኛል ይህንንም ማጣራት የኩላሊት ስራ ነው። ብዙ ስጋ መመገብ ኩላሊት ላይ ጫና በማብዛት እንዲጎዳ ያደርጋል

◈ ስኳር ያላቸው ምግቦችን ያበዛሉ?

ስኳር ማብዛት ከኩላሊት በዘለለ የልብንም ጤና ስለሚያውክ በጣም በጥቂቱ መጠቅምን ልማድ ማድረግ ለጤና ጠቃሚ ነው

◈ የአካል እንቅስቃሴ አያደርጉም?

በቀን ውስጥ የ30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ እንኳን በኩላሊት ጤናዎ ላይ በጎ ለውጥ ያመጣል

◈ የአልኮል መጠጦችን ይጠቀማሉ?

የአልኮል መጠጦችን ሲጠቀሙ በብዙ እጥፍ በኩላሊት ህመም የመጠቃት እድልዎትን ይጨምራሉ

◈ ሲጋራ ያጨሳሉ?

ሲጋራ ማጨስ የተለያዩ መርዛማ ኬሚካሎች ወደሰውነታችን እንዲገቡ ያደርጋል እነዚህም ኩላሊትን ጨምሮ ሳንባ እና ልብን ይጎዳሉ

10/08/2025

"አንድም አመራር በአምቡላንስ እጦት አይሞትም "
--------------------------------------
Concerned anonymous health professional

ለመላው የጤና ሙያተኞች በሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያላችሁ
በኢትዮጵያ የጤና ስርዓት ግንባታ ወቅት ብዙ ሙህራን ተሳትፈዋል;ስርዓቱም አንድም እናት በወሊድ ምክንያት አትሞትም በሚል በሁሉም ወረዳዎች የአምቡላንስ አገልግሎት ተስጥቶ።ሞት ቀንሷል;ትውልድ አፍርቷል።በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሁሉም አምቡላንስ አገልግሎት የሚሰጡት ከወረዳ እስከ ዞን ላሉ አመራሮች ነው።ስርዓቱ ተቀይሮ አንድም አመራር በአምቡላንስ እጦት አይሞትም የሚል ይመስላል ።ስለሆነም እኛ የጤና ሙያተኞች ትግላችን የጤና ስርዓት ለውጥ እንጅ በአንዷ ጥያቄ ብቻ ተነስቶ እንቅስቃሴውን ማድበስበስ ትክክለኛ አስተሳሰብ አይደለም።የጤና ሙያተኛው ጥያቄ ደመውዝ ብቻ ሳይሆን የተዛባውን የጤና ስርዓት ሪፎርሞች ትግበራ ላይ ጽኑ አቋም ይኑረን የሚል ነው።
፨በጽናት መታገል ያስፈልጋል
ሁሉም ሸር በማድረግ የማይመለስ ንቅናቄያችን ይደግፍ።
ሁሉም ሙያተኛ ለሁሉም ማህበረሰብ የሚደርስ የጤና ስርዓት ግንባታ ላይ ይረባረብ

በሕክምና ሙያቸው ወጣቶችና ሕፃናትን እየታደጉ ያሉት ፕሮፌሰሮቹ ጥንዶች*****************ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ እና ፕሮፌሰር ወርቅአበባ አበበ ላለፉት 25 ዓመታት በትዳር አብረው ኖ...
09/08/2025

በሕክምና ሙያቸው ወጣቶችና ሕፃናትን እየታደጉ ያሉት ፕሮፌሰሮቹ ጥንዶች
*****************

ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ እና ፕሮፌሰር ወርቅአበባ አበበ ላለፉት 25 ዓመታት በትዳር አብረው ኖረዋል።

ጥንዶቹ የተዋወቁት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ሳሉ ነበር። ይህ ትውውቃቸው አድጎ በኋላ ላይ በጋብቻ ተጣመሩ።

በትዳራቸው ስኬታማ የሆኑት ጥንዶቹ በተለይ በልጅ አስተዳደጋቸው ለብዙ ወላጆች ምሳሌ መሆን መቻላቸውን የሚያውቋቸው ይናገራሉ።

ፕሮፌሰር ሰለሞን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ሕክምና ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር ሲሆኑ፤ የሬናሰንት የአዕምሮ ሕክምናና ተሃድሶ ማዕከል መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅም ናቸው።

ፕሮፌሰር ወርቅአበባ አበበ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሕፃናት ሕክምና ዲፓርትመንት ሃላፊ እና የሕፃናት ተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ስፔሻሊስት ናቸው።

ሬናሰንት የአዕምሮ ሕክምናና ተሃድሶ ማዕከል በአልኮል እንዲሁም በተለያዩ አደንዛዥ እና አነቃቂ እጾች ሱስ የተጎዱ ሰዎች የሚታከሙበት ነው።

ማዕከሉን እንዲመሰርቱ ምክንያት የሆናቸው የቤተሰባቸው ታሪክ እንደሆነ የሚናገሩት ፕሮፌሰር ሰለሞን፤ አያይዘውም ወላጅ አባታቸው ከአልኮል ሱስ ጋር በተያያዘ በገጠማቸው ሕመም ሕይወታቸው ማለፉን ይገልፃሉ።

ታላቅ ወንድማቸውም በተመሳሳይ ችግር በወጣትነቱ እንደተቀጠፈ ያወሱት ፕሮፌሰሩ፤ በዚህ ምክንያት የናሰንት የአዕምሮ ሕክምናና ተሃድሶ ማዕከል መታሰቢያነቱ ለወላጅ አባታቸው እንዲሆን ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ማዕከሉ ከተቋቋመ 2 ዓመት ከመንፈቅ ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ500 በላይ በሱስ የተያዙ ሰዎች በማዕከሉ ታክመው ወደ ጤንነታቸው መመለሳቸውን ጠቅሰዋል።

አሁን ላይም በርካታ ወጣቶች በማዕከሉ ከሱስ የማገገም ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑን ፕሮፌሰር ሰለሞን ተናግረዋል።
#ፕሮፌሰሮቹጥንዶች #የሱስሕክምና #የሕፃናትሕክምና

09/08/2025
ውሸትም ልክ አለው። የኛን ህይወት ሲኦል አድርገው ለውጥ አስመዘገብን ማለት አይከብድም። ህዝብ የተሻለ አገልግሎት ሳያገኝ በግል ህክምና እየተበዘበዘ ባለበት በዚህ ጊዜ ለውጥ አመጣን ማለት ስ...
09/08/2025

ውሸትም ልክ አለው። የኛን ህይወት ሲኦል አድርገው ለውጥ አስመዘገብን ማለት አይከብድም። ህዝብ የተሻለ አገልግሎት ሳያገኝ በግል ህክምና እየተበዘበዘ ባለበት በዚህ ጊዜ ለውጥ አመጣን ማለት ስላቅ አይሆንም።

09/08/2025
ከዐርባ ቀን በኋላ የዐርባ ቀን ዕድልህን እንዳትረግም።ከዐርባ ቀን በኋላ የዐርባ ቀን ዕድልህን እንዳትረግም ከጎኔ ቁም ባለቤትህ  ፔሬዷ ስለቀረ ከአንዱ ፋርማሲ ሂዳ ትገዛና የሽንት ምርመራ ታ...
06/08/2025

ከዐርባ ቀን በኋላ የዐርባ ቀን ዕድልህን እንዳትረግም።
ከዐርባ ቀን በኋላ የዐርባ ቀን ዕድልህን እንዳትረግም ከጎኔ ቁም


ባለቤትህ ፔሬዷ ስለቀረ ከአንዱ ፋርማሲ ሂዳ ትገዛና የሽንት ምርመራ ታደርጋለች፣ እርግዝና ሆኖ ታገኘውና ወደ ሕክምና ማእከል ደርሳ በአልትራሳውንድ ማረጋገጥ ወይም ክትትል መጀመር ትፈልጋለች፣ ግን ሐኪም ቤቶች ውስጥ የሚገኙት የፌዴራል ፖሊሶች እንጂ ሐኪሞች አይሆኑም።


ልጅህን ያተኩሰዋል፤ ምግብ መብላት ያስጠላዋል፤ መጫወት መረበሹን ትቶ ማልቀስ ይጀምራል፣ እሱ ሲጨነቅ አንተንም ይጨንቅሀል፣ ሰማይ እና ምድር ይደበላለቁብሀል፤ ወደሐኪም ቤት ይዘኸው ብትመጣ ሐኪሞች የሉም። ቤተሰባችውን ለማስተዳደር የማያስችላቸውን ሙያ ስለተውት ልጅህን እያየኸው ልታጣው እንደኾነ ይሰማህና ትረግማለህ። ግን ምንም ለውጥ አታመጣም። ረፍዷል በቃ።


መንገድ ላይ ድንገት በደረሰ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን ይዘህ ብትመጣ በደም ተጨማልቆ የሚያክመው ሐኪም የቀን ጉርሱን ለማግኘት ጫማ መጥረግ ስለጀመረ ውድ የሆነው የሰው ልጅ ነፍስ ከእጅህ ላይ እንደውሃ ፍስስ ይላል። እያየኸው ዓይኖቹ ትንሽ ተስለምልመው ላይመለሱ ይዘጋሉ። ከደቂቃዎች በፊት ሲያወራህ የነበረውን ውድ ጓደኛህን ወይም ዘመድህን ታጣዋለህ። ያኔ የዐርባ ቀን ዕድልህን ትረግማለህ፤ ግን ረፍዷልና ምንም አታመጣም።


የልብ እና የሳንባ ችግር ያለበት አጎትህ ባፍ እና ባፍንጫው ደም ሲተፋ ታየዋለህ። ወደሐኪም ቤት ይዘኸው ስትመጣ ግን ያ በእጆቹ መዳፍ ሕይወትን የሚዘራው ሐኪም የቤት ኪራይ መክፈል የሚያስችል ደሞዝ ስለሌለው ጸጉር አስተካካይ ሆኗል ይሉሃል።


ምጥ ላይ የሆነች ሚስትህ ምጧ ቢረዝም፣ አምጣ መውለድም ባትችል በሰርጀሪ የሚያዋልዳት ሐኪም ልጆቹን ለመመገብ ሲል ሕክምናውን ትቶ ንግድ ስለጀመረ ውድ የሆነችዋን ባለቤትህን እያየሀት ታጣታለህ። ያኔ የዐርባ ቀን ዕድሌ ነው ብትል እኔ ግን የዐርባ ቀን ዕድልህ ሳይሆን የዐርባ ቀን ስንፍናህ፣ ግድ የለሽነትህ ነው ብየ እመልስልሀለሁ። ይህ እንዳይፈጠር ድምጽ ትኾነኝ ዘንድ ዐርባ ቀን ሰጥቸሀለሁ።

ከዐርባ ቀን በኋላ የዐርባ ቀን ዕድልህን እንዳትረግም ከጎኔ ቁም። ይህን ባታደርግ እኔ ካርባ ቀን በኋላ በልቼ ለማደር ስል #ቲክቶከር ስለምሆን በነጻ ድምጽ መሆን የከበደህን ያክል ከፍለህ online አክምሀለሁእና ቲክቶክ አካውንቴን ፎሎው ማድረግህን እንዳትረሳ። መንግሥት የሠራሁበትን እንዲከፍል ስጠይቅ ካልተባበርህ አንተ ራስህ ከፍለኸኝ ትታከማለህ። ከዐርባ ቀን በኋላ ሳይከፈለኝ አልሠራም፤ ጥያቄው "አንተ ትከፍለኛለህ ወይስ መንግሥት እንዲከፍለኝ ጫና ታሳድራለህ?" የሚል ነው!!!
____ ፍቅር ይሻለናል
Fikrazepam

#ፍቅራዜፓም

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Hakim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category