
04/19/2025
የሐርረ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ከናታን የጋብቻና የቤተ ሰብ ማማከር አገልግሎት ጋር በመተባበር " ጤናማ ትዳርና ቤተ ሰብ ለጤናማና ለጠንካራ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ! " በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ደረጃ መሠረታዊ የክርስቲያን ማማከር አገልግሎት ከሚያዚያ 7-9,2017 ዓ. ም የተዘጋጀውን የአሠልጣኞች ስልጠና በመልካም መንፈስ ተጠናቀቀ ::
ስልጠናው በከተማ ላሉ መጋቢዎች ወንጌላውያን ሽማግሌዎችና የትዳርና የቤተሰብ አማካሪዎች ያካተተ ነበር ::
ስልጠናውን ለሦስት ቀን እንደሚገባ ተከታተልው ላጠናቀቁ የምስክር ወረቀት ተሠጥዎቷል::
ስልጠናውን በማስተባበር ለተባበሩ ለከተማው አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መሪዎች ቦታ በመፍቀድ የአካዳሚ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ እንዲሁም ትራንስፖርት ለተባበሩን ለታላቁ ተልዕኮ አገልግሎት ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው :: ጌታ ይባርካቹህ እላለሁ!
በወቅቱ ለ100 ለሚሆኑ ለከተማው አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች 9ኛው መፅሐፌ " የለውጥ ባለራእይ!" የሚለውን ለእያንዳንዳቸው በስጦታ መልክ ተበርክቶላቸዋል! ይህን መፅሐፍ ለአገልጋዮች በሙሉ እንዲደርስ ስፖንሰር ያደረጉ በከተማው ሲያገለግሉ የነበሩና አሁንም ለከተማው ሽክም ያላቸው መጋቢ ዘማሪ ዳንኤል አምደሚኬል መጋቢ መክብብ በቀለ መጋቢ አንበሱና ወንድም በሃይሉን ጌታ አብዝቶ ይባርካቹህ ማለት እወዳለሁ!!
በነገር ሁሉ የረዳን አቅርቦቱን ላልከለከለን እግዚብአሔር ስሙ የተባረከ ይሁን!!