25/07/2025
ከአንድ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች ተወጣጥቶ የተጻፈ ነው። ስም ና ቦታ አትቀሱ
ለሁሉም ጤና ባለሙያ ይደመጥ! ! በአሁኑ ጊዜ የሚናገር እንጅ የሚሰማ የለም እንጅ ማሸነፍ ከፈለግን ብንደማመጥ መልካም ይመስለኛል ። ከታች የፃፍኩትን 8 መመሪያ ከተገበርነው መንግስትን አፍንጫውን ይዘን ማሸነፍና መብታችንን ማስከበር እንችላለን ። እንደሚታወቀው የጤና ባለሙያ የሆነ ሁሉ "የተሻለ አእምሮ ያለው, ኢለመንታሪና በሀይስኩል ቆይታው በትምህርቱ አካዳሚካሊ ጎበዝ የነበረ ,ከሁሉም ቀዳሚ አስተሳሰብና ጭንቅላት ያለው ነው ,ብዙ የሀገር ችግር የሚፈታ ተብሎ እምነት የተጣለበት የምሁር ስብስብ እንደሆነ ይታመናል ። አይደለም እንዴ? እሽ ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እንዴት እነዚህን ከላይ ሆነው ሀገር የሚያውኩ, የጤና ስርዓቱን ያበላሹ, የአስተሳሰብ ድክመት ያለባቸውን ሰዎች ይህ የምሁር ስብስብ እነሱን በአስተሳሰብ በልጦ በመገኘት በየትኛውም ዘዴ ተጠቅሞ እንዴት እነሱን ማኮላሸትና መብቱን ማስከበር እንዴት አቃተው? ? ራሳችንን ደጋግመን መጠየቅ አለብን ። ምሁርነት ወይስ ድንቁርና ያሸንፋል? ስሙኝ ልንገራችሁ በስሜት በመነዳትና ዝም ብሎ እንደቁራ በመጮህ ለውጥ አናመጣም ተነጣጥሎ ከመበላት በቀር ። ስለዚህ በተግባር ስራ እንስራ! ! የምናሸንፍበትን መንገድና ዘዴ ደግሞ እኔ በዚህች ባለችኝ አእምሮየ ተጠቅሜ ልንገራችሁ ; ( እንዴት የእኛ ጭንቅላት የካድሬን ጭንቅላት በአስተሳሰብ በልጦ ማሸነፍ ያቅተናል? ) እደግመዋለሁ በተግባር ስራ ጀምሩ አሁኑኑ ። ስለዚህ ማሸነፍ ከፈለግን ሁሉም የጤና ባለሙያ የሚከተሉትን ዘዴዎች በፍጥነት ይተግብር! !!
1ኛ. ማነኛውም የጤና ባለሙያ ሳትውሉ ሳታድሩ ከነገ ጀምራችሁ ትንሽም ብትሆን መዋያና የአእምሮ ማሳረፊያ ስራ ፍጠሩ! ! ( Don't Worry how much income you earn monthly, Just Start it! !) , ዋና ማሸነፊያ መንገዱ ይህ ነው! ! እንደምንም ብላችሁ የፈለገው አነስተኛ ገቢ ይሁን ብቻ መዋያ ቦታ አዘጋጁ! ! ), ለምሳሌ እኔ ጀምሬዋለሁ ። አሁን ባለኝ ሁኔታ በቃ ስራ ለቅቄ ብወጣ ምንም አይነት የፍርሀት ስሜትም ሆነ የይርበኛል ስሜት አይሰማኝም ።
2ኛ. በየትኛውም የጤና ተቋም የትኛውም ዲፓርትመንት አንድነት ይኑራችሁ! ! በመሀል ንፋስ አታስገቡ ; ከእርስበርስ መጠላለፍ ውጡ! ! ለመለያየትና ለመከፋፈል የሚሞክሩ ባለሙያዎችን ስምና መረጃ ,ስ.ቁ ,ሙሉ አድራሻ መዝግቡና ያዙ ተከታተሏቸው ,እንደአባጨጓሬ ቁጠሯቸው ከባድ ተግሳፅ ስጧቸው ።
3. ማነኛውም ሲኒየር ሀኪምም ይሁን የትኛውም ዲፓርትመንት በየትኛውም የሀላፊነት ቦታ ይቀመጥ ; ጤና ባለሙያው ስራ አቁሞ እያለ ስራ ለማስቀጠል የሚንደፋደፍና የሚያክም ቢገኝ ለሚደርስበት ችግርና ጥቃት ሀላፊነቱን ራሱ ሊወስድ አሳውቁት! ! ከዚያም ስራ የምታቆሙበትን ቀን ውስጥ ለውስጥ ወስኑና በድንገት ሁሉም ከቤቱ ይቅርና ወደ አዘጋጀው ቦታ ሄዶ ስራውን ይስራ! ! ወደ ሆስፒታል እመለሳለሁ የሚል ተስፋ ለጊዜው አትያዙ! !
4ኛ. ሁሉም ጤና ባለሙያ ወሬ ይቀነስና ወደተግባር ይግባ! ! 10,000 ወሬ ከማውራትና አንዱንም ሳይሰሩ ከመቅረት, ምንም ሳያወሩ 1 ስራ መስራት ይበልጣል! ! ስለዚህ ከዚህ ወዶ ገብ ከሆነ ማረሚያ ቤት ሙያ ለመውጣት ወሬ ቀንሰን በተግባር ስራ እንጀምር !!
5ኛ. በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል, በየትኛውም ዲፓርትመንት, የትኛውም የጤና ባለሙያ ችግር ሊደርስበት አይገባም! ! ሲርበው, ሲቸግረው, ሲታመም መደገፍ መታገዝ አለበት! ! ስለዚህ ይህንን ለማድረግ እጅግ ታማኝ የሆኑ, የሰው ገንዘብ የማይፈልጉ, ፈጣሪያቸውን የሚፈሩ, 3 የጤና ባለሙያዎች ይመረጡና ሳያውሉ ሳያድሩ ለዚህ አላማ የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ ያመች ዘንድ በጋራ የሚንቀሳቀስ አካውንት ይክፈቱልን ; ከዚያም ከዲያስፖራው, ከራሱ ከጤና ባለሙያው, ከባለሀብቶችና ከረጅ ድርጅቶች የሚገኘውን ገቢ በመሰብሰብ ታላቅ የገንዘብ ክምችት በመፍጠር የጤና ባለሙያውን በዘላቂነት የመንግስት የኢኮኖሚ ጥገኛ ከመሆን መታደግ ይቻላል! !
6ኛ. የትኛውም ባለሙያ በግሉ ለክፉ ጊዜና ለትግል ጊዜ የሚሆን መጠባበቂያ ገንዘብ ትንሽም ብትሆን በየአካውንቱ ማስቀመጥ አለበት! እንድንፈራ የሚያደርገንና ለመብታችን እንዳንሟገት የሚያደርገን የኢኮኖሚ ችግር ነው ። ስለዚህ የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ ከአሁኑኑ ጀምሩ ።
7ኛ. በዚህ 2 ወር ውስጥ አማራጭ የስራ ቦታ የማያዘጋጅና ስራ ለማቆም የማይወስን የሚወላውል የጤና ባለሙያ አንዳይኖር አደራ! ! በቀረ ከንቱ የቁራ ጩኸት ጩሆ መቅረት ነው የሚሆንብን ።
8ኛውና የመጨረሻው ከላይ የተዘረዘሩትን መመሪያዎችን የሚቃወም, የማይተገብር, የማይተባበር, ወይም አላማችንን የሚያደናቅፍ ቢኖር እሱ ወይ ሌባ ነው, አለያም ጥቅመኛ ነው, ወይም ደግሞ የመንግስት ፍርፋሪ ለቃሚና የኑሮ ችግር ያልገጠመው ወንበዴ ስለሆነ በምንም ታምር ልንግባባ ስለማንችል በምንም መስፈርት ,በየትኛውም አመክንዮ ልንታገሰው እንደማንችል በእግርም በፈረስም አሳውቁት! ! "ብዙ ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል ነው ነገሩ " ዳይ ! ወደ ስራ ጀምሩ ..........