Ethiomedical

Ethiomedical https://linktr.ee/ethiomedical1
Educational purposes only (not a medical advice for your conditions ). Always consult your provider before decision.

ማንኛውም ሰው ጤናን የተመለከተ መረጃ እንድቀርብለት ከፈለገ መልክት ያስቅምጥልን ፤ ባለሙያም ሆኖ አብሮን መስራት የሚፈልግ ካለ መቀላቀል እና የራሱን ድርሻ ማበርከት ይችላል፡፡ በምናቀርበው መረጃ ላይም የምትሰጡት ገንቢ አስተያየትም ሆነ ቅሬታም እንቀበላለን ፤ ለማስተካከልም እንሞክራለን፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ በታች የተጻፉትን ዓይነት አስተያየቶች እንዳይስተናገዱ እናደርጋለን፡፡
• ሌሎችን የሚያስቀይሙና ስሜትን የሚጎዱ
• ብሔርን ፡ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥላቻ፣
• ወሲብ ቀስቃሽ ወይም መልካም ክብርና ዝናን የሚያጠፉ
• በጨዋ ቋንቋ ያልተጻፉ ወይም ስድብን የያዙ ቃላት ወይም ቅያሜ ሊያመጡ የሚችል ቋንቋ ያላቸው
• ንግድ

ን የሚያስተዋውቁ፡ አትራፊ ለመሆን ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ የሚፈልጉ
• የጤና ስነ ምግባር የማይፈቅደውን ሀሳብ ለማራመድ የሚፈቅዱትን
• የሌሎችን ደህንነት እና ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉና መሰል ተግባራትን የሚያበረታቱ

06/05/2026

Nourish your organ

03/05/2026

Women - Here is your Cervical cancer screening schedule


Let’s know our numbers before too late
03/05/2026

Let’s know our numbers before too late


02/05/2026

Well said 💯

29/04/2026

Stay Hydrated Naturally!

Did you know some fruits are over 90% water?
Eating them helps keep your body cool, energized, and refreshed 🌿

🍉 Watermelon – 92% water
🍓 Strawberries – 91% water
🍈 Cantaloupe – 90% water
🍑 Peach – 89% water
🍍 Pineapple – 86% water
🍊 Orange – 86% water

✨ Hydration doesn’t only come from water—eat it too!

✔️ Supports skin glow
✔️ Boosts energy
✔️ Helps digestion

👉 Save this post & add these fruits to your daily routine!

Diabetic diet good vs bad
28/04/2026

Diabetic diet good vs bad

NSAIDs use & it’s complication  - pain killers        Common complication of pain killer- kidney injury- Gastritis, ulce...
28/04/2026

NSAIDs use & it’s complication - pain killers


Common complication of pain killer

- kidney injury
- Gastritis, ulcer & bleeding

High risk people
- elderly, people with kidney or Gastric issue, high dose or prolonged use of pain killer.

Prevention
- use low dose for short term, take with food, stay hydrated, monitor kidney function on risky patient, ask your doctor before taking by self

Healing start with smart choice
26/04/2026

Healing start with smart choice

08/01/2025

  diabetics
04/01/2025

diabetics

የእርግዝና ወቅት ስኳር ምንድነው?የስኳር ህመም ከቋሚ ህመሞች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን የኢንሱሊን ሆርሞን እጥረት ወይም በትክክል አለመስራት ምክንያት የሚከሰት ነው። የአይን ፣ የኩላሊት...
04/01/2025

የእርግዝና ወቅት ስኳር ምንድነው?

የስኳር ህመም ከቋሚ ህመሞች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን የኢንሱሊን ሆርሞን እጥረት ወይም በትክክል አለመስራት ምክንያት የሚከሰት ነው። የአይን ፣ የኩላሊት ፣የ ልብና የነርቭ ችግሮች የሚያስከትል ህመም ነው።

ስኳር በአራት ዋናዋና አይነቶች ያሉት ሲሆን የእርግዝና ወቅት ስኳር አራተኛው አይነት ስኳር በመባል ይታወቃል።

✨የእርግዝና ወቅት ስኳር (GDM) ምንድነው?

የእርግዝና ወቅት ስኳር በእርግዝና ሰዓት የሚከሰት የስኳር አይነት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የምርመራ የሚገኝ ነው።

በአብዛኛው ከ28 ሳምንት እስከ ወሊድ ብሎም ስድስት ሳምንት ድህረወሊድ ድረስ ይቆያል።
በእርግዝና ሰዓት ከሚገኙት የስኳር አይነቶች 90% የሚሆነው የስኳር አይነት ሲሆን ከእርግዝና በኋላ የሚጠፋ አይነት ነው።

በአብዛኛው የሚታዩ ምልክቶች ባይኖሩትም ከፍተኛ ተጋላጭነት ካለ በምርመራ ሊታወቅ ይችላል።

⚡️ምልክቶቹስ?

• የውሃ ጥም
• የሽንት መብዛት
• የምግብ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር
• የልጅ መፋፋት
• የእንሽርት ውሃ መብዛት
• የፅንስ ያፈጣጠር ችግር

💥አጋላጭ ሁነቶች (risk factors)

• የቤተሰብ የስኳር ህመም
• ያለቅጥ ውፍረት
• የበፊት እርግዝና ስኳር
• የደም ግፊት
• የኮሌስትሮል መብዛት
• በርግዝና ወቅት ያላግባብ ክብደት መጨመር እና ወዘተ...

⛄️እንዴት ይታወቃል?

ሃኪሞችሽ አጋላጭ ሁነቶችሽ ካዪ በኋላ ከ24-28 ሳምንት የስኳር ምርመራ ያደርጉልሻል። ይህም ጣፋጭ ስኳር (40% glucose) በአፍሽ ከወሰድሽ በኋላ በየአንድ ሰዓት ልዪነት የደም ስኳር መጠንሽ በመለካት የእርግዝና ስኳር እንዳለ እና እንደሌለ ይነግሩሻል።

በሌላ የምርመራ ዘዴ (HgA1C) በመመርመርም ማወቅ ይቻላል።

ባደጉ አህጉራት ማንኛውም ነፍሰጡር እናት ለስኳር ምርመራና ልየታ የምታደርግ ሲሆን በታዳጊ አገራት የተወሰኑ ነፍሰጡሮች አጋላጭ ባህሪያቸው ታይቶ የሚመረመር ይሆናል

👉ምክንያቱ ምንድነው?

• የእርግዝና ወቅት ስኳር ለምን እንደሚከሰት በትክክል ምክነያቱ ባይታወቅም ብዙ ሳይንሳዊ ሠላምቶች አሉ።

• የሆርሞን አለመመጣጠን በእርግዝና ወቅት የእንግደልጅ እጅግ በጣም ብዙ ሆርሞኖችን የሚያመነጭ ሲሆን ከእነዚህም PLG (plasental lactogen )አንዱ ነው። ይህም ሆርሞን ኢንሱሊን በህዋሳት ወስጥ እንዳይሰራ በማደናቀፍ የደም ውስጥ ስኳር እንዲጨምር ያደርጋል። ስቴሮይድ ሆርሞን እና የእድገት ሆርሞን እንደዚሁ በተመሳሳይ የኢንሱሊን ስራን በማስተጓጎል እንደ ምክነያት ይነሳሉ።

• አካባቢያዊ ተፅኖ በእርግዝና ወቅት የክብደት መጨመር ህዋሳቶች ለኢንሱሊን ሆርሞን እንዳይታዘዙ ሊያደርግ ይችላል የሚል ሌላ መላምትም አለ።

🤹🏽‍♀️ለመጀመሪያ ጊዜ በርግዝና ወቅት የታወቀ ስኳር የቆየ መሆኑ አለመሆኑ እንዴት ይታወቃል?

• ከሃያ ሳምንት በፊት የተከሰተ ስኳር
• HgA1C ከ7% በላይ ከሆነ
• የረጅም ጊዜ የስኳር ህመም ውስብስ ችግሮች ካሉ ለምሳሌ የአይን ችግሮች ፣ የኩላሊት ህመም የመሳሰሉት
• የልጅ የአፈጣጠር ችግር ካለ
የቆየ ስኳር አመላካቾች ስለሆኑ በድህረ ወሊድ ጊዜ በድጋሚ ክትትል ያሻል።

🎗ውስብስብ ችግሮች

የእረግዝና ወቅት ስኳር በእናትና በፅንስ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል

እናት ላይ
• ፅንሱ በመመፋፋቱ ምክንያት ለኦፕራሲዮንና ለመሳሪያ ወሊድ መጋለጥ
• የምጥ መርዘም
• ለልብ ችግር ተጋላጭነት መጨመር
• በወሊድ ወቅት ደም መፍሰስ
• የእንግደ ልጅ መቅደም

ፅንሱ ላይ
• የፅንስ መፋፋት
• ያለጊዜ መወለድ እና የአተነፋፈስ ችግር
• የስኳር ማነስ (hypoglycemia)
• የፅንስ መታፈን
• ሆድውስጥ መጥፋት
• ተደጋጋሚ ውርጃ
• የጨቅላ ቢጫነት
• የጨቅላ ሙቅት መውረድ (hypothermia)

🎟 ህክምናውስ?

• የአኗኗር ዘዬ መቀየቀር ፦ ማለትም በእርግዝና ወቅት የሚፈቀዱ መጠነኛ እንቅስቃሴዎችን መድረግ፣ ጣፋጭ ምግቦችን በመተው አልያም በመቀነስ የደም ስኳርን መቆጣጠር ይቻላል።

• መድሃኒት፦ የአኗኗር ዘዴ በመቀየር ካልተስተካከለ ወይም በሃኪምሽ ከታመነበት መርፌ (insulin) ወይም ኪኒን (oral hypoglycemic agent) በመጠቀም የደም ስኳርሽ ማስተካከል ይቻላል።

• የስኳር ህመም ውስብስብ ጉዳቶች እንዳይከሰቱ ቁርስ ከመብላትሽ በፊትና በማንኛውም ጊዜ ምግብ ከበላሽ ከሁለት ሰዓት በኋላ የስኳር መጠንሽን መለካት አትርሺ

• መለካት ብቻ በቂ ስላልሆነ የለካሽውን በመመዝገብ በክትትልሽ ወቅት ለሃኪሞችሽ በማሳየት የመድሃኒትሽ መጠን ለማስተካከል ይረዳል።

• ከፍተኛ የስኳር መጠን ካለሽ ደግሞ ሆስፒታል ተኝተሽ ጥብቅ የፅንስ ክትትል እና የስኳር ልኬት ሊደረግልሽ ይችላል።

☔️🍦እንዴት መከላከል ይቻላል?

አጋላጭ ሁነቶችን በመቀየር ማለትም ከእርግዝና በፊት ክብደት ማስተካከል፣ ጤነኛ የአኗኗር ዘዴን መከተል ፣ ስፓርት እንቅስቃሴ መስራት ፣ ጭንቀት ማስወገድ ፣ አደገኛ አመጋገብ በማስቀረት (ጣፋጭ ፣ አልኮሆል፣ ጮማ እና ጨው) በመተው ፣ በቂ ውሃ በመጠጣት እና በቂ እረፍት በማድረግ) ስኳር እና ሌሎች ቋሚ ህመሞችን መከላከል ይቻላል።

በወቅቱ የእርግዝና ክትትል በማድረግ የስኳር ምርመራ በማድረግ በወቅቱ መታከም።

የወደፊት እጣፈንታውስ?

• የእርግዝና ወቅት ስኳር በአብዛኛው ከወሊድ በኋላ የሚጠፋ ሲሆን የተወሰነው ግን ወደሁለተኛው የስኳር አይነት ሆኖ ሊቀጥል ይችላል።

• የወደፊት የስኳር ህመም ፣ የደም ግፊት እና የልብ ህመሞች ተጋላጭነትን ይጨምራል።

• የወደፊት የእርግዝና ወቅት ስኳር እና አለቅጥ ውፍረትን ያጋልጣል።

• ስለዚህ ድህረ ወሊድ ከስድስት ሳምንት በኋላ የስኳር መጠን በመለካት እና በየ ጊዜው በመመርመር ቋሚ የስኳር ህመም እንደሌለሽ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ዶ/ር ነጋልኝ መቻል ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiomedical posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category