RUH Clinic/ENT,Head & Neck Clinic

  • Home
  • RUH Clinic/ENT,Head & Neck Clinic

RUH Clinic/ENT,Head & Neck Clinic Committed to provide the best specialized medical and surgical ENT/Head & Neck care!!!

RUH ENT and Surgical Center, Hawassa
24/09/2025

RUH ENT and Surgical Center, Hawassa

208 likes, 17 comments. “ሩህ ከአንገት በላይ እና ቀዶ ህክምና ማዕከልን ጠቅለል አድርገን እናሳያችሁ፡፡ አድራሻ፡ ሀዋሳ ትሩፋት ከአድማስ ሞል ፊትለፊት ብለው ቅያስ 50 ሜትር ገባ ብሎ”

03/05/2025

I confess that I don't normally write posts on linkedin. I decided to make an exception today to write about an exceptional doctor, Dr. Muluken Bekele, ENT Surgeon and Otologist/Neurotologist @ RUH ENT & Surgical Specialized Clinic. He made me realise that this belief that we need to go abro...

The story of my colleague and school mate from GCMSየኦስትቶክሌርሲስ ( Ostoclerosis) ህክምና በሀዋሳ ሩህ የአንገት በላይና ቀዶ ጥገና ማዕከልበቅድሚያ O...
13/03/2025

The story of my colleague and school mate from GCMS

የኦስትቶክሌርሲስ ( Ostoclerosis) ህክምና በሀዋሳ ሩህ የአንገት በላይና ቀዶ ጥገና ማዕከል
በቅድሚያ Ostoclerosis ምንድነው?
👉 በመካከለኛው የጆሮ ክፍል በሚገኙ ጥቃቅን አጥንቶች ላይ በተለይም ስቴፕስ በሚባለው አጥንት ዙሪያ የተዛባ የአጥንት ክምችት ሲኖር የሚከሰት እና የመስማት ችግር የሚያስከትል የጆሮ ህመም ነው።
👉በዘረመል ወይም በቤተሰብ የሚተላለፍ በመሆኑ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቤተሰብ አካል ሊያጠቃ ይችላል።
👉ከወጣትነት እስከ መካከለኛው የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን ያጠቃል።
♦️ ምልክቶቹም
🔵 ከጊዜ ወደጊዜ እየባሰ የሚሄድ የመስማት ችግር
⚫️ የጆሮ ማቃጨል ወይም መጮህ
♦️የህክምናው አማራጭ
🔵 የጆሮ መስሚያ መርጃ መሳሪያ መጠቀም
⚫️ በ (Stapedotomy) ቀዶ ህክምና አልንቀሳቀስ ያለውን የስቴፕስ አጥንት አርተፊሻል (prosthesis) መቀየር ሲሆን

👉በሀዋሳ ሩህ የአንገት በላይና ቀዶ ህክምና ማዕከል ሰሞኑን ይህንን ህክምና ያገኘ ግለሰብን ተሞክሮ እነሆ፦

♦️ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ነርስ ነኝ ። ባለትዳርና የ3 ልጆችም አባት ነኝ። ላለፉት 5 እና ከዚያ በላይ አመታት ጆሮዬ አይሰማልኝም። በዚህም ምክንያት
👉ትምህርቴን መቀጠልና ማሻሻልም አልቻልኩም
👉በቤትም ሆነ በማህበራዊ ኑሮዬ ፣ በስራ ቦታዬም ለመግባባት እቸገራለሁ።
👉 በተለይ በስራ ቦታ በጽሁፍ የተላለፈልኝን መልዕክት ካልሆነ የተነገረኝን መስማት ባለመቻሌ ከባልደረቦቼ እና ታካሚዎች ጋር ከፍተኛ የመግባባት ችግር እየተፈጠረብኝ ቆይቷል።
👉 እንደ ጤና ባለሙያነቴ ምርመራ አድርጌ ችግሬን ተረድቻለሁ። ዋናው ችግር ግን ቀደም ሲል ህክምናው ወደ ውጭ ሪፈር በመደረግ የሚገኝ ስለነበር በእኔ አቅም የሚታሰብም አልነበረም።
👉 መስማት ባለመቻሌ እና ሰዎችም ስለማይረዱኝ ስነልቦናዬ ተጎድቶ ነበር፣ መግባባት ባለመቻሌ ማህበራዊ ግንኙነቴ ዝቅተኛ አድርጎብኛል። ትምህርቴን ማሻሻል ባለመቻሌ በስራ ዕድገትና በገቢም መሻሻል አልቻልኩም። ብቻ ለአመታት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እያለፍኩ ነበር።
🙏 ከዚህ ሁሉ በኃላ ዶ/ር ሙሉቀን በቀለ በሆስፒታላችን ሲኒየር የአንገት በላይ ስፔሻሊስት እና የጆሮ ሰብ ስፔሻሊስት እንደመሆኑ ይሄንን ህክምና እያደረገ መሆኑን በማወቄ ና 100% የምተማመንበት ጠንቃቃ ባለሙያ መሆኑን ስለማውቅ ቀርቤ ችግሬን አወራሁት ። እርሱም ያለሁበትን ሁኔታ ስለተረዳኝ ምንም እንኳን ውድ ህክምና ቢሆንም አርተፊሻል የስቴፕስ አጥንት( prosthesis)ም በውጭ ምንዛሬ እንደሚገዛና እንደሚገባ ባውቅም ያለ አንዳች ክፍያ ቀዶ ህክምናውን በራሱ የህክምና ማዕከል ለዚህ ቀዶ ህክምና የተሟላ ቁሳቁስ ባለበት ሩህ የአንገት በላይና ቀዶ ህክምና ማዕከል በማምጣት ሰርቶልኛል።
👉 የሚገርመው ደግሞ ለውጡ እዚያው እየሰራልኝ እያለ ማወቅ መቻሌ ነው አስተካክሎ ተነስቶ ከማሸጉ በፊት ሲያናግረኝ መስማት ችዬአለሁ። ክብር ለአምላኬና ለጥበበኛው ዕጅ ለዶ.ር ሙሉ ቀን በቀለ ከእንግዲህ ወደ ኃላ የቀረሁባቸውን ነገሮች ሁሉ ማሳካት እንደምችል አምናለሁ!
♦️እንደ እኔ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ እያለፋችሁ ያላችሁ በሙሉም በዚህ እጀ ወርቅ ሀኪም እንድትጠቀሙበት እመክራለሁ🙏
፨ ይህ ጽሁፍ በታካሚው ሙሉ ፍቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የቀረበ ነው።
ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!
አድራሻችን :- ሀዋሳ ከትሩፋት ወደ አቶቴ በሚወስደው ትራፊክ መብራት አለፍ ብሎ አድማስ ሞል ፊት ለፊት 100ሜ ገባ ብሎ።
ስልክ :- +251 462121952
+251 462125086
+251 918999393

My interview on የጆሮ ኢንፌክሽን ምንነት on Fana tv
12/03/2025

My interview on የጆሮ ኢንፌክሽን ምንነት on Fana tv

Del dine videoer med venner, familie og verden

04/03/2025

ተገልጋዮቻችን ምን ይላሉ?
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#አቶ ተመስገን ደርሶ እና ወ/ሮ ቅድስት ላቀው ከባሌ ጊኒር አረዋ ከሚባል ቦታ ነው የመጡት ። እዚህ እንዲገኙ ምክንያት የሆናቸው ነገር ደግሞ የልጃቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ የጆሮው መስማት መጠን እየቀነሰ መምጣት እና ከዚህም ጋር ተያይዞ በትምህርቱ፣ በማህበራዊ ኑሮው ከዕድሜ ዕኩዮቹ ጋር ያለው ግንኙት መቀነስ ብሎም በተፈጠረበት የስነልቦና ቀውስ የባህሪይ ለውጥ የነበረው መሆኑን ይናገራሉ።
ልጃቸው ብርሃን ተመስገን የ16 አመት ልጅ ይሁን እንጂ የ8ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ይህም የሆነበትን ምክንያት ሲገልፁ ከጆሮው ህመም ጋር የተገናኘ መሆኑን ያሰምራሉ።
👉 የጆሮ ህመም ሲባል ለካ የጆሮ ህመም ብቻም አይደለም ብዙ ይዞት የሚመጣ መዘዝና ጉዳት አለው ሲሉም በልጃቸው ከደረሰው በመነሳት ይገልፃሉ።
🙏በዚህ አጋጣሚ የልጃቸውን ጆሮ ለማሳከም ከአካባቢአቸው ጀምሮ ሀዋሳ በሚገኙ ትልልቅ ሆስፒታሎች ጭምር ያልደረሱበት የህክምና ተቋም እና ያልጨረሱት ገንዘብ እንደሌለ መረጃ ያለመኖር እንዴት እንደሚጎዳ በቁጭት ይናገራሉ።
♦️ ዛሬስ ? አሁንማ ከስንት መንከራተት በኃላ ትክክለኛው ቦታና ባለሙያ ያለበትን ስፍራ በማግኘታቸው በመጡ ዕለት ምርመራውን ጨርሰው የልጃቸው የጆሮ ችግር ቀዶ ህክምና የሚያስፈልገው ደረጃ መድረሱ ስለታወቀ በማግስቱ ሊሰራለት መቻሉን ስለልጃቸው የጆሮ ችግርም ባልተድበሰበሰ መልኩ በግልጽ መረጃውን አግኝተውና አምነውበት ሊያሳክሙ ችለዋል።
👉 ለሌሎች በዚህ ችግር ውስጥ ላሉ ግለሰቦችና ቤተሰቦች መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉም ፦ እኔና ቤተሰቤ በመንከራተትና በወጪ የከፈልነውን ዋጋ እንዳትከፍሉ ወደትክክለኛው ስፍራ በመሄድ ከጤናችሁም፣ከጊዜአችሁም፣ ከገንዘባችሁም እንድታተርፉ ይሁን🙏
በዚህ አጋጣሚ ሀዋሳ የሩህ አንገት በላይና ቀዶ ህክምና ማዕከል ሠራተኞችና ሀኪሞችን በጠቅላላ ከበር ጀምሮ አልጋ ይዘን በህክምና እስከቆየንበት ጊዜ ላሳያችሁን ፍቅርና ትህትና የተሞላበት እንክብካቤ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ🙏 ልጃችንን ወልዳችሁ እንደሰጣችሁን ነው የምቆጥረው ብለዋል።
♦️ለማንኛውም የጆሮና ተያያዥ ችግሮች ወደ ማዕከላችን በመምጣት የአንገት በላይ ስፔሻሊስት እና የጆሮ ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሙን ዶ/ር ሙሉቀን በቀለን ያግኙ!
ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!
አድራሻችን :- ሀዋሳ ከትሩፋት ወደ አቶቴ በሚወስደው ትራፊክ መብራት አለፍ ብሎ አድማስ ሞል ፊት ለፊት 100ሜ ገባ ብሎ።
ስልክ :- +251 462121952
+251 462125086
+251 918999393

World Hearing Day, March 3, 2025.Make ear and hearing care a reality for all!!የ ጆሮ ህክምናን ለ ሁሉም እንዲደርስ  እውነታ እናድርግ!!!
02/03/2025

World Hearing Day, March 3, 2025.
Make ear and hearing care a reality for all!!
የ ጆሮ ህክምናን ለ ሁሉም እንዲደርስ እውነታ እናድርግ!!!

ክፍት የስራ ቦታ
24/01/2025

ክፍት የስራ ቦታ

Address

Turufat Traffic Light, Hawassa ,Ethiopia

Telephone

+251935979196

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when RUH Clinic/ENT,Head & Neck Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to RUH Clinic/ENT,Head & Neck Clinic:

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram